የሩሲያ አየር ኃይል ፓይለት የነበረው ኩዝሚኖቭ ከ 6 ወራት በፊት ነበር የሀገሩን ጦር ሄሊኮፕተር ጠልፎ ለዩክሬን አሳልፎ የሰጠው። ፓይለቱ የሀገር ክህደቱን ይፈፅም ዘንድ የዩክሬን ዜግነት እና ከዜለንስኪ መንግስት የ 500,000 ዶላር የክህደት ሽልማት ለመቀበል በመነጋገር ነበር። ይሁንና ዩክሬይን የገባችለት ቃል ሳይፈፀም መቅረቱ ነው የመረጃ ምንጮች የጠቆሙት።
በዚህም ኩዝሚኖቭ M-8ን የተሰኘውን የሀገሩን ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ዝቅ አድርጎ እና የራዲዮ ግንኙነቱን በማቋረጥ ኮቴወን አጥፍቶ ወደ ዩክሬይን ኮብልሏል። በወቅቱ ሁለት ፓይለት ባልደረቦቹ በሄሊኮፕተሩ ውስጥ አብረውት የነበሩ ሲሆን፤ ልክ ኪየቭ ደርሶ እንዳረፈም ሁለት ባልደረቦቹ ላይ ግድያ ፈፅሞባቸዋል፤ ባልደረቦቹን የገደለበት ምክንያት ማስረጃ ባይገኝለትም ዩክሬይን ቃል የተገባችለትን የጉቦ ገንዘብ ለብቻው ለማድረግ ከማሰብ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።
ሳይፈፀም ከቀረው የ 500 ሺህ ዶላር የክህደት ሽልማቱ በተጨማሪ ዘለንስኪ የሚመራው የዩክሬይን ደህንነት መስሪያ ቤት ለራሱም ሆነ ከሩሲያን ለቀው ለሚወጡ ወላጆቹ ጭምር የደህንነት ዋስትና ልታቀርብለት ቃል ተገብቶለት ነበር።
መጨረሻው በስፔን ተገድሎ መገኘት የሆነው ፓይለቱ ጭንብል የለበሱ ሰዎች በ12 ጥይቶች ደብድበው፤ ሁለት ጊዜ ደግሞ በመኪና ዳምጠውታል።
“ከሃዲ” በሆነው ፓይለት ዙሪያ በስፔን የአካባቢ ነዋሪዎች እንደተናገሩት፣ ኩዝሚኖቭ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአልኮል እና ከአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነት ጋር የተያያዘ ችግር ውስጥ ገብቶ ነበር።
የኩዝሚኖቭ ታሪክ የሁሉም ባንዳዎች የህይወት ዲያሪ ይመስላል!
▪️የዓባይልጅ EslemanAbay