ሀገራት ሊደርቁ የተጋለጡ ኃይቆቻቸውን እንዴት ታደጓቸው? ?

? እስሌማን ዓባይ – የዓባይ ልጅ

አደጋ የተጋረጠባቸውን የውሀ አካላት ለመታደግ ከአለማቀፍ አጋሮች በትብብር መስራት ውጤት አምጥቷል። በዋናነት ደግሞ በ Ramsar ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ቁልፍ ርምጃ ነው።

ራምሳር የውሀ አካላትን አደጋ ለመቅረፍና ለመንከባከብ በ UN ደረጃ የተቋቋመና 1975 ወደስራ የገባ ነው። አገራትና አለማቀፉን ማህበረሰብ አስተባብሮ ርጥበታማ ቦታዎችን የመንከባከብ ተግባርን ያሳልጣል።

“በአካባቢው ነዋሪዎች ርጥበታማ ቦታዎች ለወባ ትንኝና ለሌሎች በሽታዎች መፈጠሪያ እንደሆነ ተደርገው ይወሰዳሉ። ለተፈጥሮ ሚዛን፣ ለብዝሀ ህይወት፣ ለሀይቆች እንዲሁም ለውሀ አካላት ያለውን ፋይዳ አልተረዱትም። መንግስትም ግንዛቤውን አልፈጠረም…” ያለው ምኑየለት መንግስቴና ኢብራሂም ሙሀመድ የተባሉ ምሁራን 2018 ላይ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ያቀረቡት ምርምር ነው። ጥናቱ “የአካባቢን ጉዳይ የሚመሩ ባለስለሰጣናትም ስለ ርጥበታማ ቦታዎች ፋይዳ እውቀቱ የሌላቸው ናቸው” ሲል ይጨምራል።

እውነታው ግን ጥቂቱን የአለማችንን ቆዳ ስፋት የሚይዙት ርጥበታማና ረግረጋማ ቦታዎች 40 በመቶውን የአለም ስነ ምህዳር የሚፈጥሩት እነሱ ናቸው። ያለነሱ ብዝሀ ህይወት፣ የሀይቅና ወንዞች ኦርጋኒክ ይዘት፣ ለም ማዕድናት ወዘተ… አይታሰቡም።

በ Ramsar wetland site ዝርዝር ውጥ መካተት የቻሉ የውሀ አካላ ታዲያ የድጋፉ ተጠቃሚ ሆነዋል። እስከ 2018 ድረስም 2,231 የራምሳር ሳይቶች ተመዝግበው የጥበቃና እንክብካቤ ፕሮጀክት አግኝተዋል። ሳይቶቹ 169 አገራት የሚገኙ ሲሆኑ በድምሩም 2.1 ሚሊዮን ስኩ.ኪ.ሜትር ስፋት የሸፈኑ ርጥበታማ ቦታዎች ናቸው። ራምሳር wetland ብሎ የሚለያቸው ሀይቆች፣ ወንዞች፣ ረግረጎች፣ የባህር ዳርቻዎች፣ ሰው ሰራሽም ሆኑ የተፈጥሮ የውሃ አካላት ሲሆኑ ባላቸው ማህበረ ኢኮኖሚና የአካባቢ አበርክቶ ካለባቸው የስጋት መጠን ጋር ተለክቶ ይመረጣሉ።

የጣና ሀይቅም ይህን የራምሳር መስፈርት እያሟላ ነገር ግን በአለም ከ 2300 በላይ ሳይቶች ውስጥ እንዲመዘገብ አልሆነም። በአለም ላይ ከተመዘገቡት ከ 2300 በላይ ሳይቶች 40 በመቶው በአፍሪካ ናቸው። ጎረቤት ኬንያን ብንጠቅስ 6 ሳይቶችን አስመዝግባለች። የውሃ ማማ የባለችው ኢትዮጵያ በአየር ንብረት አለማቀፍ ዘመቻው ላይ የአፍሪካ እንደራሴ ብትሆንም አንድም የውሃ አካልን ማስመዝገብ አልቻለቸፈችም። ለምዝገባው የሚያስፈልገው የውሀ አካላትን መረጃ ሰንዶ ለራምሳር ሪፖርት ማድረግ ነው። ከዚህ ጎን ለጎን ከ ramsar convention ጋር የሚጣጣም ህቅ አርቅቆ ማፀሸደቅ ነው። ነገር ግን እስካሁን አልተደረገም።

በኢትዮጵያ ሰፊ ርጥበታማ ሀብቶችአሉ።” Forum for Environment 2009 ላይ ያወጣው ሪፖርት 22,600km2 ርጥበታማ ቦታ ነበራት። የአገሪቱን 2 በመቶ የቆዳ ስፋት የሚሸፍን። ነገርግን ያሉበት ሁኔታና የአደጋ ተጋላጭነት በውል አልተሰነደም። በስምጥ ሸለቆና ደቡባዊ የአገሪቱ ክፍል 43 ቦታዮች ተሰንደዋል። ጣናን ጨምሮ የሰሜኑ ይዞታዎች አልተካተቱም። ይህ ባለመሠራቱም ከ 1983 እስከ 2013 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 52 በመቶው የርጥበታማ ቦታዎች ይዞታ ወደ ደረቅ መሬትና የርሻ ቦታነት ተለውጧል።

በጣና ጉዳይ ከዚህ በፊት ባቀረብኩት ፅሁፍ ላይ በ UNESCO ምክትል ዋ.ዳይሬክተርና የቻድ ሀይቅን ለመታደግ 60 ቢሊዮን ዶላር ከአለማቀፉ ማህበረሰብ ፈንድ ሲሰበሰብ ባለድርሻ የነበሩት ኢትዮጵያዊ Getachew Engida ሀሳባቸውን እንዲጠቁም ጠይቄያቸውም ነበር። እሳቸው በአጭሩ “የፖለቲካ ቁርጠኝነት ነው ዋናው የመፍትሄ ቁልፍ፤ በበኩሌ አገሬን ለመርዳት ዝገሸጁ ነኝ…” ነበር ያሉት።

የኬኒያ ተሞክሮ የሚያሳየንም ይህንኑ ነው። አገሪቱ ከ RAMSAR CONVENTION ጋር የተጣጣመ ህግ አፀደቀች። 6 ሳይቶችን አስመዘገበች። ከ 120 ሺህ ሄክታር በላይ ርጥበታማና የውሃ ሀብቷንም በአለማቀፍ ፈንድ እየተንከባከበች ትገኛለች። ተጨማሪ ሳይቶችን ለማስመዝገብም እንቅስቃሴ ላይ ነች።

ጣናም ሆነ ሌሎች 43 የውሃ አካላት ዙሪያ ያሉን ርጥበታማ ቦታዎች የራምሳር መመዘኛን የሚያሟሉ ናቸው። በተለይም ጣናን ramsar ካስቀመጣቸው መስፈርቶቹ አኳያ እንደሚከተለው እንመልከት።

መስፈርት 1. የተደቀነው አደጋ አሳሳቢነት

ጣና 3672 .ኪ.ሜ ስኩዌር ስፋት ነበረው። አሁን ወደ 3000 ወርዷል። ማለትም የሐዋሳና የዘዋይ ሐይቆች ተደምረው የሚያክል የሃይቁ ክፍል ወደ የብስነት ተቀይሯል።
ርጥበታማው ክፍሉ የሀይቁን 2.1 በመቶ ይሆናል። ( ከ 3 አመት በፊት በወጣ ሪፖርት መሠረት የሀይቁ 24 ሺ ሄክታር የውሀ ክፍል በእምቦጭ አረም የተወረረበት ወቅትም ይታወሳል) እምቦጩን በሰውና በማሽን ማስወገድ አደጋውን ለመቀነስ ወሳኝ ነው። ይሁን እንጂ የማስወገድ ዘዴው ምህዳሩን ከማስጠበቅ ጋር አብሮ ካልተከናወነ የሁልጊዜ አዙሪት ሆኖ ይቀጥላል። ስነ ህይወታዊ ጥፋትም እየተከሰተ ይሄዳል። – ባለሙያዎች ደጋግመው የሰጡት ምክረ ሐሳብ ነው።

?? መስፈርት 2. ከ 20 ሺህ በላይ አዕዋፋትን የያዘ ከሆነ፣
° የጣና ሐይቅ ከ 217 በላይ የአእዋፍ ዝርያዎች አሉበት። ሀያ ሺ የሚደርስ አሐዝ ያላቸው አእዋፋትም በሐይቁ ዙሪያ ይገኛሉ፡፡

?? መስፈርት 3. አደጋ የተደቀነባቸው የእንስሳትና ዕፀዋት ዝርያዎች መኖሪያ ከሆነ እንዲሁም
° በበመስፈርት 2 እንደተገለፀው 217 ዝርያዎችና ሀያ ሺ የሚደርስ ቁጥር ያላቸው አእዋፋት መኖሪያ የሆነው (በመስፈርት 1) የተገለፀው ከፍተኛ አደጋ የተደቀነበት የጣና ሐይቅ ዙሪያ ነውና አእዋፋቱ ላይም ከፍተኛ የአደጋ ስጋት ይፈጥራል፡፡

?? መስፈርት 4. የዓሳ ብቸኛ ዝርያና ንዑስ ብቸኛ ዝርያ መገኛ ከሆነ
° ሐይቁ ከ 67 በላይ የአሳ ዝርያዎች (ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆኑት በሀገር ውስጥ ብቻ የሚገኙ)፡፡

የጣና wetland ቦታዎች በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው። ጉና፣ ግሽ አባይ፣ ፎገራ፣ ጮቄ፣ ደምቢያ፣ ርብ፣ መገጭ ከመገኛዎች ውስጥ ዋናዎቹ ሲሆኑ ባጠቃላይም በ 3 ዞኖችና 29 ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ጣና በምናውቀው ደረጃ አደጋ ተደቅኖበታልና የተቀናጀ መፍትሄ በአስቸኳይ ይፈልጋል። ዘላቂ መፍትሄ የሚገኘውም የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ነው እላለሁ። በዚህም ከ Ramsar Convention የተጣጣመ አገራዊ ህግ ማፅደቅ። ለዚህም ምሁራን ባለስልጣናት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አለማቀፍ ተቋማት እንዲሁም በአሜሪካና አውሮፓ ያሉ በጣና እና አካባቢ ጥበቃ ላይ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ተቀናጅተው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል። ጊዜው ግን በጣም አሁን ነው።

መንግስት የ #RAMSAR ሕግ ያፀድቅ ዘንድ እያንዳንዳችን ድምፃችንን እናሠማ።

    Esleman Abay የዓባይ ልጅ

firat publiahed on August 2020 and june 2021 ⬇️

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2324223471041846&id=100003626461788

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2061617930635736&id=100003626461788

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories