በስድስት ሀገሮች በተከሰቱ ጦርነቶች በ30 አመታት ምን ያህል ጤና ተቋማት ጥቃት እንደደረሰባቸው የመረመረ ጥናት ተደርጎ ነበር።
በጥናቱ የተዳሰሱ ሀገራት ዬመን (ከ2015-አሁን)፣ ሶሪያ (ከ2011-አሁን)፣ ኢራቅ (2003–2011)፣ ቼቺኒያ (1999–2000)፣ ኮሶቮ (1998–1999) እና ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና (1992–1995) ናቸው።
የጥናቱ ባለድርሻ ተቋማት Doctors Without Borders፣ Monitoring Violence against Health Care፣ PHR Physicians for Human Rights ናቸው።
በግምቦት 2018 ይፋ የተደረገው የጥናቱ ውጤት ተከታዮቹን ቁጥሮች አስቀምጧል።
▪️በሶሪያ በ7 ዓመት 315 ጤና ተቋማት ወድመዋል።
▪️ዬመን 93
▪️ኢራቅ 12
▪️ቼቺኒያ 24
▪️ኮሶቮ 100
▪️ቦስኒያ 21
▪️በWHO የቱርክ ጤና ክላስተር በኋላ ላይ ጤና ተቋማት ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን በሚከታተለው Monitoring Violence against Health Care MVH, የ135 ተጨማሪ ተቋማት ጥቃቶችን ሪፖርት አርጓል።
በድምሩ 700 ጤና ተቋማት ላይ ጥቃት ደርሷል።
ህወሃት ወዳደረሰው የጤና ተቋማት ውድመት ስንመጣ የጤና ምኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ETV ላይ ቀርበው እንደገለፁት እስካሁን ባለ መረጃ ከ2219 በላይ ጤና ተቋማት በህወሃት ውድመት ደርሶባቸዋል።
ልብ በሉ፤ 6 ሀገሮች/ግጭቶች በሰላሳ አመታት ውስጥ ሲደረጉ በቆዩ ጦርነቶችና ግጭቶች ውስጥ 700 የጤና ተቋማት ላይ ነው ጥቃት የተሰነዘረው። ጥናቱ ጥቃት ላይ ቢያተኩርም የህወሃት ጥፋት ከጥቃት ባለፈ በውድመት ደረጃ የተመዘገበው ነው። ገና ያልሰበሰቡ መረጃዎች በሚቀሩበት ዛሬ ላይ ብቻ 2,219 ጤና ተቋማት ላይ ውድመት ፈፅሟል።
በመቀጠል የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር
ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ያቀረበው ሪፖርት በአማራ ና አፋር የወደሙ የጤና ተቋማትን ተጨማሪ አሃዝ ይፋ አድርጓል።
በአማራ እና አፋር ክልሎች በአሸባሪው ህወሃት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ከ36 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑን ነው ጤና ሚኒስቴር በየካቲት ወር የገለጸው፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአንደኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባው የጤና ሚኒስቴርን ግማሽ በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም በገመገመበትና የጤና ሚኒስቴር የ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ፤ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት ማብራሪያ በአማራና አፋር ክልሎች 42 ሆስፒታሎች፣ 523 ጤና ጣቢያዎች፣ 2 ሺህ 359 ጤና ኬላዎች በአሸባሪው ህወሃት ዘረፋና ውድመት ተፈፅሞባቸዋል ብለዋል።
በዚህም ምክንያት በአካባቢው ለማህበረሰቡ ይሰጥ የነበረው የጤና አገልግሎት መስተጓጎሉን ገልጸዋል።
የጤና ተቋማቱን ዳግም ስራ ለማስጀመር በተደረገው ርብርብ የጤና ሚኒስቴርና የተለያዩ ተቋማት ከ772 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የመድሃኒት፣ የህክምና መሳሪያዎችና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።
እንደ አጠቃላይም በአማራ እና አፋር ክልሎች በአሸባሪው ህወሃት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ከ36 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑን ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።
▪️Esleman Abay የዓባይ፡ልጅ
ሙሉ ጥናቱን ለማግኘት በሊንኩ ይግቡ ⬇️
https://eslemanabay.com/tplf-attacks-health-care-facilities-in-6-conflicts/