
የዓባይ፡ልጅ ✍️
በፀረ-አማፂ ዘመቻ ወቅት ርዳታው እንዴት እንደሚዳረስ ማወቅ ተፋላሚዎቹን ለማወቅ ሁነኛው መንገድ ነው። ምዕራባዊያን በሚታወቁበት ‘militarization’ of humanitarian aid” ዙሪያ ከተደረጉ ጥናቶች መካከል በአፍጋኒስታን ተተኳሪነት የተሰራው እንዲህ ይለናል፤ “In Afghanistan, many US commanders saw humanitarian organizations as essential components of the counter-insurgency equation.” ርዳታን እንዲህ የግራጫ hybrid ጦርነት ወሳኙ የማሸነፊያ መሳሪያ ካደረጉት አመታት ተቆጥረዋል።
ኒዮርክ-ታይምስ ጋዜጣ አሜሪካዊ ኮሎኔል ስለ ርዳታ ድርጅቶች/ሰራተኞች የተናገሩትን ጠበመጥቀስ “Those [AID workers, Aid agencies] are going to win it for us …” በማለት አስነብቧል።
ሌላኛው አሜሪካዊ ሜ/ጀነራል ማይክል ታከር፣ የ ISAF እና በአፍጋኒስታን የአሜሪካ ጦር አዛዥ፤ “በአሜሪካ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ውስጥ ሰብአዊ ርዳታ ቁልፍ መደለድላችን ነው። ከወታደራዊ ዘመቻው ጋር እጅና ጓንት ሆነው ይተገበራሉ። ሰብአዊ ርዳታን በመጠቀም አማፂ ኃይሎችን አቅም/ህልውና ማሳጣትና ከህዝቡ እንዳይጣበቁ አይነተኛው ስትራቴጂ ነው” ሲሉ ነው የተናገሩት። ይህ አማፂውን ሃይል ሲዋጉ የሚከተሉት ሲሆን መንግስትን የሚዋጋ አማፂ ሲሆን ደግሞ ሰብአዊ ርዳታ በተቃራኒው በአማፂው ተጠቃሚነት ላይ ተማክሎ ሲዳረስ መቆየቱን ነው ጥናቶቹ ያስቀመጡት። ለምሳሌ በሶሪያ ጦርነት ውስጥ የምዕራባዊያን ሰብአዊ ርዳታ ለአማፂያኑ ተሰጥቶ ነበር ሚዲያዎች በተገኙ ወቅት ሲያከፋፍሉ ቀረፃ ይደረግላቸው የነበረው። በተመሳሳይ የህወሃት ሽብር ቡድንም የምዕራባዊያን ርዳታ ዋነኛው “የጭካኔ መሳሪያ” ይሆነው ዘንድ እስከዛሬ ድረስ ይህን ሲተገብሩት ነው የቆዩት።
ይሁንና፣ በትናንትናው ዕለት ተመድ በ OCHA-ኢትዮጵያ በኩል የተናገረው ተግባራዊ ከተደረገ የህወሃት “የጭካኔ ጦር መሳሪያ” መከነ ማለት ነው። አማፂያን ሰብዓዊ ርዳታን እንደ መሳሲያ ሲጠቀሙ ይስተዋላል። የህወሃት ተግባር የተለዬ የሚያደርገው ገፅታ ቢኖረውም..። አማፂዎች አቅም ከሚያገኙባቸው መሰረታዊ ሁኔታዎች ውስጥ በመረጃ ረገድ በሚገኝበት አካባቢ ሕዝባዊ የመረጃ ወገንተኝነት/ድጋፍ(ወዶም ይሁን ተገዶ)፣ የውጭ ድጋፍ እና ከውጭ ኮሪደር የሚያገናኝ ኮሪደር ማግኘት ቀዳሚ ናቸው።
ህወሃት ከላይ የተጠቀሱትን(ከኮሪደር በስተቀር) ሲያገኝ መቆየቱ ሶስተኛ ወረራ እስከማድረግ አራምዶታል።
የትግራይ ሕዝብ ግን ከዚህ ወዲያ ሊቀጥል አስቸጋሪ ሆኖበታል። በዚህ የተነሳም በትግራይ የነበረው ሕዝባዊ የመረጃ ድጋፍ ጠፍቶ ለመከላከያ ሰራዊቱ ሆኗል። የሚቀረው መሳሪያው የውጭ አገራት ድጋፍ ሲሆን ከልዩልዩ አሁናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር ተዳምሮ ይህኛውም የህወሃት እስትንፋስ እየተዘጋበት ይመስላል። የህወሃትን መርዶ በኢዜአ በኩል ያሰሙት የ UN OCHA ማስተባበሪያ ቢሮ ዳይሬክተር ሚሼል ሳድ መከላከያ ሰራዊቱ ነፃ ባወጣቸው አካባቢዎች ሰብዓዊ አቅርቦቶችን ተደራሽ ላደርግ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
“መንግስት ከህወሃት ነፃ ቀወጡ አካባቢዎች የሰብዓዊ አቅርቦቶችን ተደራሽ ለማድረግ የጀመረው ጥረትና ለሰብዓዊ ድርጅቶች ያቀረበው ጥሪም የሚደነቅ ነው” በማለት የገለፁት ዳይሬክተሩ “የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲዳረስ በመንግስት የተጀመረውን ጥረት በመደገፍ አብረን እንሰራለን። ቢሯቸውም ከፌራል መንግስትና በተዋረድ ካሉ ባለድርሻዎች ጋር ድጋፉን ማሳለጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሲመክር ቆይቷል” ብለዋል።
ከህወሃት ነጻ በወጡ የትግራይ ከተሞች ርዳታ ተደራሽ እንዲሆን በመንግስት የተቋቋመ ኮሚቴ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል። በሌላ በኩል ደግሞ የሽብር ቡድኑ ከትግራይ ተረጂዎች ጉሮሮ ነጥቆ ለወታደሮቹ ደብቆ የነበረው ርዳታ በመከላከያ ሰራዊቱ ለህዝብ ሲከፋፈል ነበር። ሰብአዊ ርዳታ በራሴ ኮሚቴ ካልሆነ ሌላ ተዋናኝ እንዲገባ አልፈቅድም” በማለት አቋሙን መግለፁም አይዘነጋም።
ይመስለኛል ህወሃት ከመጥፋቷ በፊት የክህደት አጋሮቿ ፈረንጆች ቀድመው መጥፋት ጀምረዋል!