
የዓባይ፡ልጅ
~ዓባይ ዓለም አቀፍ ወንዝ ነውና ሀገራት መደራደር፣ መስማማት ሲጀምሩ ቀዳሚው ጥያቄ ‘ምን ያህል ውሃ አለ? የሚል ይሆናል’~
ስለ ዓባይ ከዚህ ቀደም የነበሩ ጥናቶች ያሰፈሯቸው አሃዞችን ያስቀየሩ አዳዲስ ጥናታዊ መረጃዎች በኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን ትኩረታቸው የሆኑት ደግሞ
▪️ከነጭ ዓባይ የውሃ መጠን 50 በመቶው በሱዳን ረግረጋማ ቦታ ገብቶ ይቀራል” እና
▪️ ወደ አስዋን ግድብ ይገባል የተባለው ትክክለኛው የውሃ መጠን ላይ ነው። በዚህ ዙሪያ የኢትዮጵያዊ ምሁራን ጥናታዊ ግኝቶች የቀድሞ ጥናቶችን መደምደሚያ ያስቀየረ፤ አዳዲስ ሀቆችን ወደ አደባባይ ያመጣ ሆኗል፡፡
መቀመጫቸውን በአሜሪካ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን የጂኦፊዚካል ባለሙያዎች በየዓመቱ ወደ አሜሪካዊቷ ካሊፎርኒያ ይተምማሉ፡፡ በዚያ መደበኛ ስብሰባ አላቸው፡፡ ከስብሰባቸው ጎን በቡድን ቡድን ሆነው ሲጨዋወቱ ሁሌም የማይቀር አጀንዳ ይነሳል፡፡ ከውሃ ጋር የተያያዙ ጥናቶችን የሚካሄዱ ሶስት ኢትዮጵያውያን አንድ ጥናት በትብብር ለማካሄድ ወሰኑ፡፡ ጥናቱ ከኢትዮጵያ የውሃ ሀብቶች ከፍተኛውን ቦታ በሚይዘው አባይ ላይ ትኩረት እንደሚያደረግ ተስማሙና ስራ ጀመሩ፡፡
ጥናቱን የማስተባበሩን ሚና ኮሎራዶ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ውስጥ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ገብርኤል ሰናይ ወሰዱ፡፡ እንደ ዶ/ር ገብርኤል ሁሉ መነሻቸው ከአለማያ ዩኒቨርስቲ የሆነው ዶ/ር ዮናስ ካሳ ጥናቱን ለማካሄድ ያነሳሳቸው ሌላ ተጨማሪ ምክንያት እንዳለ በመግለፅ “የአባይን ውሃ አጠቃቀም አስመልክቶ በግብጽ እና በሱዳን መካከል እንደ ጎርጎሮሳዊው 1959 የተፈረመው ስምምነት መሰረት ያደረገው በግብጽ አስዋን ግድብ ላይ የተለካ የውሃ መጠን እንደሆነ ያስታውሳሉ፡፡ በወቅቱ በነበረው ልኬት 84 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ ወደ አስዋን ግድብ ይገባል፡፡ በዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ዮናስ ጥናታቸውን ለማድረግ ሲነሱ ይህን ልኬት እንደገና ለመፈተሽ እንዳሰቡ ይናገራሉ። በጥናታቸውም ተከታዮቹ ግኝቶች እውን መሆን ቻሉ።
(ይህን ጉዳይ ከሶስት አመታት በፊት ዶይቼ ቨለ ካስደመጠው የመራረጥኩትን ወደ’ናንተ እላለሁ።)
የመጀመሪያው ወደ ረግረጋማው ቦታ ገብቶ በዚያው ወደ ከርሰ ምድር የሚዘልቀው የነጭ አባይ የውሃ መጠን 85 በመቶ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ሁለተኛውና ለኢትዮጵያ ይበልጥ የሚጠቅመው የተመራማሪዎቹ ግኝት ዶ/ር ዮናስ ቀደም ብለው ያነሱት ወደ አስዋን ግድብ ይገባል የተባለው የውሃ መጠን ጉዳይ ነው፡፡ ግኝቱ እንደሚያትተው ወደ አስዋን የሚገባው የውሃ መጠን ቀድሞ ከሚታሰበው ከፍ ያለ እና በዓመት 97 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የሚደርስ ነው፡፡ ዶ/ር ገብርኤል ያብራራሉ፡፡
ግብፅ እና ሱዳን ግን ድሮ ሲስማሙ ሰነዱ እንደሚያሳየው መጠኑ 84 [ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ] ነው ብለው ነው፡፡ ልዩነቱ 13 ቢሊዩን ሜትር ኪዩብ ነው፡፡ ይሄ ምን ማለት ነው? በኪሎሜትር ሲለካ 13 ኪሎ ሜትር ኪዩብ ማለት ነው፡፡ የአዲስ አበባ የቆዳ ስፋት 520 ስኩዌር ኪሎሜትር አካባቢ ነው፡፡ ያንን ሁሉ [ሸፍኖ] አዲስ አበባን በ25 ኪሎሜትር ያጠልቃታል ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ስናስበው የጣና ሀይቅ 28 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ነው፡፡ የዚያን ግማሽ ማለት ነው”
ይህ እስካሁን በስሌት ውስጥ ሳይገባ የቀረው የውሃ መጠን ከኢትዮጵያ ሌሎች ወንዞች መጠን ጋርም ሲወዳደር ከኦሞ ውሃ ፍሰት ከ15 እስከ 20 ቢሊዮን ሜትር ኪዮብ ይሆናል።
ሱዳን ከአባይ የምትወስደው ውሃ መጠን 18.5 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ሲሆን በየዓመቱ ወደ አስዋን ሳይታወቅ ይገባ የነበረውን የውሃ መጠን ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ጥቅም ላይ ከምታውለው ውሃ ጋርም ሲነፃፀር 2016 ፋኦ ኢትዮጵያ 10.5 ቢሊዩን ሜትር ኪዩብ ውሃ ተጠቅማለች፡፡ ከዚያ ውስጥ 85 በመቶ ለመስኖ ሰባት በመቶው ለቀንድ ከብቶች ነው፡፡ ስምንት በመቶው ደግሞ ለመጠጥ እና ለኢንዱስትሪ የሚሆን፡፡ እንግዲህ የአባይ ውሀ ውስጥ ጠፋ የሚባለው ውሃ 13 ቢሊዮን ነው፡፡ የኢትዮጵያን ይህን ሁሉ የውሃ ፍላጎት የሚያሟላ ነው፡፡ ከዚያም በላይ ይተርፋል”
ከስምንት ዓመት በፊት በታዋቂ የምርምር መጽሔት ላይ የወጣው ይህ የተመራማሪዎቹ ጥናት አዲስ ነገር ይዞ ቢመጣም ኢትዮጵያ ተጠቅማበት እንደማታውቅ ሁለቱ ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡ ዶ/ር ገብርኤ ስለጥናታቸው ፋይዳ ተከታዩን ብለዋል፡፡ “እንዴት ነው የሚጠቅመው ብለን ስናስበው ለድርድር ይመስለኛል፡፡ ዓባይ ዓለም አቀፍ ወንዝ ስለሆነ ሀገሮች ተገናኝተው መደራደር፣ መስማማት ሲጀምሩ የመጀመሪያው ጥያቄ ‘ምን ያህል ውሃ አለ?’ የሚል ይሆናል፡፡ ውሃውን ለማስተዳደር የምንችለው የውሃውን መጠን ካወቅን በኋላ ነው፡፡ በተሳሳተ ቁጥር ለሀብቱ አስተዳደርም ሆነ ውጤታማ ዕቅድ ለመንደፍ አይቻልም፡፡ [ጥናቱ ] ሐብቱን ለማስተዳደር፣ ለመደራደር እና ለስምምነትም ይጠቅማል።”