ለፈርዖን ብክነት ዘመናት የተፈረደበት የዓባይ ውሃ ▪️የዓባይ፡ልጅ ✍️ እስሌማን፡ዓባይ

ናይል በግብፆች ውብ ስነ-ቃል እየተነገርለት በተግባር ግን አሳዛኝ በደል ይፈፀምበታል። እዚጋ በትነት፣ በቆሻሻ፣ በኬሚካል፣ በውሃ-ፈጂ ግብርና፣ ለውጭ አገራት ኢንቨስተሮች በርካሽ በመሸጥ ወዘተ የሚደረግበትን በደሎች እናቆያቸው (በቀጣይ እመጣበታለሁ)። አስቡት! ግብፅ ለቅንጦት የጎልፍ ሜዳዎቿ በያመቱ የምታባክነው የናይል ውሃ በጣሙን ያስገርማችኋል።

ግብፃዊው ጋዜጠኛ (ዋሊድ ሰላም) ሳይቀር ለጎልፍ መጫወቻ ስለሚባክነው ውሃ እንዲህ ብሏል “ፕሮጄክቱ የሚያስገርመው ይፋ በተደረገበት ወቅት “ራሱ አልሲሲ ኢትዮጵያ ዓመታዊ የውሃ ድርሻችንን ልትቀንስብን ነው በሚሉበት ሰሞን መሆኑ ነው።

ግብፅ ለአዳዲሶቹ 40 ጎልፍ ሜዳዎች 40 ሺህ ሄክታር መሬት መድባለች። እነዚህ ሜዳዎች በአመት 1 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ያፈስሳሉ። ግብፃዊያኑ የሚባክነው ውሃ ለአንድ ሚሊዮን የግብፅ ህዝብ ለመጠጥና እና ለመስኖ የሚበቃ ነው ይላሉ።

በግብፅ ከመቶ በላይ የጎልፍ ሜዳዎች አሉ። New Cairo በሚባለው 2016 ላይ በአል-ሲሲ በተመሰረችው ከተማ በሰሜን ዳርቻ፣ በደቡብ ሲና፣ በቀይ ባህር፣ በካታሜያ እና በሌሎች ተጨማሪ 40 የጎልፍ መጫወቻዎች ግንባታ ተጀምረዋል።

የራሳቸው የግብፅ የቀድሞ መስኖ ሚኒስትር ዶ.ር ናስር አላም
“የጎልፍ ሜዳዎቹ የአንድ ሄክታር ውሃ ፍጆታ ከሁለት ሄክታር የሩዝ ማሳ ፍጆታ ጋር እኩል ሲሆን የስንዴ እርሻ ከሚወስደው በስድስት እጥፍ ይበልጣል” ነው ያሉት። በዚህም አንድ ሄክታር ሩዝ እንደ ዝርያውና እንደ ጥንቃቄው እስከ 15 ሺህ ሜ.ኩብ እንደሚፈጅ መረጃ ቢኖርም እኛ አማካይ በሚባለው 13 ሺህ በሄክታር አስሉት። ለ 40 ሺው የጎልፍ ሜዳ ከ 1 ቢሊየን ሜ.ኩብ በላይ ይሆናል።

እንግዲህ ከእንግሊዝ የቅኚ ዘመን አንስቶ በግብፅ ጎልፍ ሜዳ በብዛት ይገኛል። ቁጥራቸው መቶ እና በላይ እንደሚሆን የተመለከትኩት መረጃ አለ። እኛ 40 ብቻ አድርገን እናስላው። ሌላ 1 ቢሊዮን ኩብ ውሃ ይባክናል። 2 ቢሊዮን ደረሰ። ይህ ብክነት ለጎልፍ ብቻ ነው። የራሳቸው ገበሬ ተቸገሩ ሲሉ የሚደመጡት የላክንላቸውን ውሃ ቀምተው ለቱሪስት መዝናኛ እየሰጡ ነው ይላሉ የራሳቸው ሙያተኞች።
መረጃውን አክቲቪስት ሳይሆን ምሁራንና ተንታኞች ናቸው በማስረጃ ያቀረቡት። ለአብነትም የግብፅ የውሃ ፕሮፌሰርና የቀድሞው የመስኖ ሚኒስትር አማካሪ ዶ ር መጋሪዋ ሸሃታ፣ በአል-አዛር ዩኒቨርስቲ የአካባቢ ሳይንስ ኦርጋኒክና ዘላቂ ግብርና ፕሮፌሰር ዶር ካሌድ ጋኔም፣ የግብፅ ብሔራዊ የርቀት ዳሰሳ ጥናት ባለሥልጣን ሰነዶች፣ በካይሮ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር ዶ ር ጋማል ሲያም በዚሁ ዙሪያ የተለያዩ ጥናታዊ ምክረ ሐሳብ አቅርበውበታል።
(አላምንም የሚል ግብፃዊ ካለ ሰነዶችን ላደርሰው እንደምችል በአጋጣሚው ይወቅልኝ)

በተመሳሳይ የግብፅ ቱሪዝም በ 2000 ለመጡለት 8 ሚሊዮን ገደማ ጎብኝዎች 30 ሚሊዮን ሜ.ኩብ ውሃ ደፍቷል። በ 2020 ዓ.ም 20 ሚሊዮን ጎብኝዎችን በመሳብ ተሳክቶልናል ሲሉ አልሲሲ ተደምጠዋል። ይህን አሀዝ ወደ ውሃ ወስደን ስናጥበው በአመት 100 ሚሊዮን ኩብ ተደፋፍቷል ማለት ነው።
2016 ግምባታውን ያስጀመሩት ኒውካይሮ የተባው መዲና ምን ያህል ውሃ ይጠይቅ ይመስላችኋል? በዬቀኑ 650 ሺህ ሜትሪክ ኩብ ንፁህ ውሃ። በአመት 240 ሚሊዮን መሆኑ ነው። አልሲሲ የውሃ ጉዳይ ቢያሳስባቸው ኖሮ አዲስ መዲና በ 58 ቢሊዮን ዶላሮች ሲመድቡ ለውሃ ማጣራት በአመት ከ 2 ቢሊዮን በታች እንደሚመድቡ ትዝ ባላቸው ነበር።

ቆጣሪ የማያውቀው የግብፅ አባካኝነት የገጠሩን ሳይጨምር በከተሞች ብቻ በአመት 10 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውሃ ይድፋፋል። ይህን በግማሽ መቀነስ እንደሚቻል ይነገራል። ያውም ለቀቅ ተደርጎ። 5 ቢሊዮን ማዳን ይችሉ ነበር ማለት ነው። እየደመራችሁ..?

እንግዲህ ይሄ ትላንት የፃፍኩትን አይነት ለውጭ ኢንበስተር የሸጡትን አየሰጨምርም። በትነት በብክለት በግዴለሽ አጠቃቀም በውሃ ፈጅ ማሳ ወዘተ የሚባክነውን አያካትትም። ይህ ለመዝናኛ ቅንጦች ብቻ የተደፋፋው የዓባይ ነው። የከተማው 5B ብክነትና ለጎልፍ-ቱሪዝም 2.5B ተደምረው 7.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ደረሰ።

ታዲያ ግድባችን ከጎርፍ ላይ ቀንሶ የሚይዘው ውሃ እንደማይጎዳቸው ራሳቸውም ጠንቅቀው ያውቁታል። ትኩረታችን መሆን ያለበት ከሁለተኛው ሙሊት በኋላ ከሐሰት ይልቅ በአመዛኙ ወደ በሳይንሳዊው ሙግት ለሚጋጠመን የካይሮ ተደራዳሪ ታጥቆ ስለ መጠባበቅ ነው።
መሰል ጥናታዊ ሐቆች ሌሎች ግድቦችን ስንጀምር ለሚጠብቀን ጥናታዊ ሙግት ከትጥቃችን መካከል ናቸው።

የውሸት ፒራሚዱን እያንኮታኮቱ መጓዝ ቀጥሎ የሚጠብቀን አገራዊ የቤት ስራ ??

[ፌስቡክ ለተወነ ጊዜ ስላገደኝ ቴሌግራም ላይ ታገኙኛላችሁ ⬇️
https://t.me/eslemanabayy

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories