መግለጫ ሆኖ የጠፋው “የቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካ ትብብር መማክርት”

የቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታና የትብብር መማክርት ምስረታ ሊቋቋም መታሰቡ ተገለጸ

[Feb 5, 2021 / ጥር 28፣ 2013 ኤፍ ቢ ሲ]

ይህ የተባለው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ለሦስት ተከታታይ ቀናት ባካሀየዱቴ የምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡

በምክክር መድረኩ ፓርላማው የዲፕሎማሲ አውታር ሊሆን እንደሚገባው ተጠቁሟል፡፡ በውይይት መድረኩ አምባሳደር ሻሜቦ ፈታሞ ቀይ ባህር በዓለም ንግድ ልውውጥ ወሳኝ ድርሻ ያላት መሆኗን ጠቅሰው፤ በቀጠናው ያሉ ሃገራት በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ መስኮች የተሻሉ ለውጦች እያደረጉ መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡

አምባሳደሩ የቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታና የትብብር መማክርት ምስረታ ሊቋቋም መታሰቡን ጠቅሰዋል፡፡

በምክክር መድረኩ የተገኙ የምክር ቤት አባላት ቀይ ባህርን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ግብጽ እየተከተለች ያለችውን የጥፋት መንገድ በመረዳት የአገሪቱን ህልውና ለማስቀጠል ከጎረቤት ሃገራት ጋር ያለትን ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

እያንዳንዱ ዜጋም በሄደበት ሃገርም ሆነ በሚሰራበት ተቋም እንደ ዲፕሎማት በመስራት ተጽእኖ ፈጣሪ ሊሆን እንደሚገባ የጠቆሙት የምክር ቤቱ አባላት በፓርላማ ዲፕሎማሲ ላይ በትኩረት በመስራት ፓርላማውን የዲፕሎማሲ አውታር ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

የፓርላማ ዲፕሎማሲ የምክር ቤቶች የውጭ ግንኙነት ስራ የሃገራችንን አቋም ለማንጸባረቅ፣ የአሰራር ልምዶችን ለመቅሰም፣ የሃገሪቱን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚዊ እንቅስቃሴ ለዓለም ህብረተሰብ ለማሳወቅ ብሎም ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ለማግኘት እንደሚያገለግል በምክክር መድረኩ ተመላክቷል፡፡

የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የተካሄደውን የምክክር መድረክ አስፈላጊነት በገለጹበት ወቅት፤ መድረኩ ኢትዮጵያ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ የሚያስቃኝ በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር ነገሪ አክለውም ውስጣዊ አንድነታችንን እና ከጎረቤት ሃገራት ጋር ያለንን ግንኙነት በማጠናከር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ትኩረታችን ግድባችንን በማጠናቀቅ ላይ ሊሆን እንደሚገባ ማስገንዘባችውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0qDRAojfxDX1xi2tXhfreiEvvLxCRXmNJxcWsgz19HWRzHZn92QSHmsAo4G6VZW4ol&id=100003626461788

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories