ምድር የ24 ሰዓት ሽክርክሪቷን

ቀድማ አጠናቀቀች
ምን እየሆነች ይሆን?
የዓባይ:ልጅ✍️

ምድራችን አንድ ያልተለመደ ክስተትን አስተናግዳለች። የሳይንስ ሊቃውንት የምድራችን ሽክርክሪት እየተፋጠነ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን በመሰል ክስተትም የትላንትናዋ ቀን (በፈረንጆቹ july 29) ከ 24 ሰዓት በታች ርዝማኔ የተመዘገበባት ሆና አልፋለች።
ቀንዎ ቸር ይሆንልዎት ዘንድ ተመኝተው ይሆናል፤ ቢመኙም ባይመኙም ታዲያ… july 30 2022 ለሁሉም ከሃያ አራት ሰአት በላይ ትሆን ዘንድ እውነት ሆኗል ይሉናል – ሳይንቲስቶቹ። ዛሬ ያገኙት ተጨማሪ ጊዜ 1.59 ሚሊሰከንዶች መሆኑም ተነግሯል።

ይህ ሊሆን የቻለው በምድር የመሀከለኛው ክፍል በሚኖሩ ሂደቶች ወይም በአየር ንብረት ለውጦች ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ። አንዳንድ ተመራማሪዎችም ደግሞ በምድራችን ጂኦግራፊያዊ ዋልታዎች ላይ በሚፈጠሩ እንቅስቃሴ የተነሳ ሊሆን ይችላል ይላሉ፤ የመሬት ዋልታ እየቀለለ መምጣት አንዱ መላምት ሲሆን የምድር ሰሜናዊ ዋልታ ወደ ምስራቅ ተንሸራትቷል ተብሏል። ባለፉት 40 አመታት ውስጥ 4 ሜትር መንሸራተቱንም ነው ጥናቶች የገለፁት፤ እንደ NDTV ዘገባ – ወይስ ከሶስተኛው ዙር ሙሌት ጋር ተያይዞ የካይሮ ልብ ትርታ ከፈጠረው መንቀጥቀጥ…🤣
ታዲያ ይህ ክስተት ላይመለስ ካለፈው ከትላንት ጋር አብሮ የሚያልፍ ሁነት? ወይስ የሚያደርሰው ተፅዕኖ ይኖር ይሆን?
ሳይንቲስቶች እንደገለፁት የሴኮንድ ዝላዩ earth spin በአቶሚክ ሰዓት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል። ባለሙያዎቹ አክለውም የምድር ሽክርክሪት መፍጠን ሴኮንዶችን ወደ አሉታዊ ዝላይ የሚያመራ ሲሆን በተለይም በስማርት ፎኖች፣ ኮምፒውተሮችና የመገናኛ ዘዴዎች ላይ ውዥንብር ሊፈጥር ሊችላል ተብሏል።

የጊዜ ሲስተሙ ዝላይ ማሳየቱ በኮምፒውተርና ተያያዥ ቴክኖሎጂዎች ችግር የሚፈጥረው 00፡00፡00 ብሎ ከመጀመሩ በፊት ከመጀመሩ በፊት በሚኖሩት 23፡59፡59 እስከ 23፡59፡60 ባሉ ጊዜያት ውስጥ ሲሆን፤ በነዚህ የጊዜ ቆይታ ወቅት በመረጃ ማከማቻዎች ላይ ባሉት የጊዜ ማህተሞች ላይ በሚፈጥረው መዘበራረቅ ምክንያት ፕሮግራሞችን ሊያበላሽ እና ሊያዛባ ይችላል። ብዙዎቹ ሲስተሞቻችን በሰአት ስሌት የተደረጁ ናቸው። ኮምፒውተሮች ጂፒኤስ ሳቴላይት ሶፍትዌሮች ወዘተ…

ይህ ስርአት ተናግቶ የሴኮንድ ዝላይ ሲፈጠር ሳይንቲስቶች የማስተካከያ Negative leap second ጭማሪ ለማድረግ ይገደዳሉ። ይህን የሚሰራው International Earth Rotation and Reference Services IERS የተባለ ተቋም ሲሆን የመሬትን ሽክርክሪት ይቆጣጠራል። ይኸው ተቋም IERS በ 2012 እኤአ leap second ለማዘለል የተገደደበት ክስተት ተፈጥሮ ነበር። ይህን ተከትሎም የማህበራዊ ሚዲያዎች ቅፅበታዊ ብልሽት አስተናገዱ፤ የዳታ ማከማቻዎች ተዛቡ፤ በመርሃግብር የተቀመጡ ሲስተሞች ብልሽት ገጠማቸው…።
ብሉምበርግ እንደዘገበው በዬአንዳንዷ ሴኮንድ ብቻ 1.4 ሚሊዮን የግዥ ትእዛዝ messages ይላካሉ፤ የአክሲዮን ገበያዎች 4.6 ሚሊዮን ዶላር ይሰራባቸዋል። ይህ እጅግ ብዙ ከሆነው ሲስተም የሁለቱ ብቻ ማሳያ ነው። ይህን የሴኮንድ ርዝማኔ የትላንቱ ቀን ባስተናገደው የ 1.59 ሚሊሰከንድ ስናሰላው እንከን የለሽ የሚባል አይሆንም።
በነገራችን ላይ ይህ ክሰተት ሃያላን ጠፈር ላይ ግብግብ በገጠሙበት፣ የኑክሌር ፍጥጫ ባየለበት፣ የሳይበር ትንቅንቅ በበዛበት ወቅት ነው…ይሁንና ድምዳሜ ለመስጠት የደፈረ ሳይንቲስ እንኳን እስካሁን አልተገኘም። ብቻ እውነቱን ፈጣሪ በጊዜ ሊገልጠው የርሱ ፈቃድ ከሆነ’ንጂ..።

ቀናችንን ሁሉን አዋቂ ለሆነው አንድዬ ፈጣሪያችን መስጠቱ እንዳለ ሆኖ በዛሬው እለት የተጨመረውን የ 1.59 ሚሊሰከንድ ወርቃማ ጊዜ በጥበብ እንዳሳለፏት ተስፋ ላድርግ 🤲 ሰላም ለምድራችን 🤲

#የዓባይልጅ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories