ሩሲያ እና ቻይና

ለወደዱት እንጀራ ለጠሉት ጦር መሳሪያ የሆነው አፈር ማዳበሪያ            

ያራ ኢንተርናሽናል የሚሉት የአፈር ማዳበሪያ በማምረት የሚታወቅ ኩባንያ በ 60 የዓለም ሃገራት ይንቀሳቀሳል። ኩባንያው ከሩሲያ እጅግ ብዙ ጥሬ ዕቃ ይሸምታል። ወቅታዊው ጉዳይ ስለዚሁ ኩባንያ ትንሽ እንድናወሳ መነሻ ሊሆነን ይችላል። አንዱን ላስቀምጥ።

ያራ ኩባንያ በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ግዢ ውስጥ ከሁለት ቢሊዬን ብር በላይ በያመቱ ሲጭበረበር የነበረው ዝርፊያ አካል እንደነበር በስፋት ሲዘገብ ነበር። ለማባደሪያ ግዢ በየዓመቱ ከሚመደበው በቢሊዬን የሚቆጠር ገንዘብ ውስጥ ተለቅ ያለው ደርሻ ለሙስና ሲጋለጥ እንደነበር ከአራት አመት በፊት ይፋ የሆነ መረጃ ነበር። በወቅቱ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተባለ መንግስታዊ መስሪያ ቤት በወቅቱ እንዳለው ቀደም ባለው ጊዜ የማዳበሪያ ግዢ በግብርና ሚኒስቴር አማካይነት ይካሄድ ነበር፡፡ መስሪያ ቤቱ ከመንግስት ጋር ወዳጅነት ካላቸው ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር በመመሳጠር ይፈጽማቸው በነበረው ግዢዎች የተነሳ 2.6 ቢሊዬን ብር በየዓመቱ ሲመዘበር ቆይቷል፡፡ በተለይ ደግሞ ያራ የተባለው (መለስ ዜናዊን የሸለመው የኖርዌይ ማዳበሪያ አምራች ድርጅት) በማዳበሪያ ግዢ ውስጥ በሚፈጸመው ምዝበራ ትልቅ ሚና ነበረው፡፡
የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተባለው መስሪያ ቤት ‹‹በማዳበሪያ ግዢ አሠራር ላይ ማስተካከያ በመደረጉ ዓለም አቀፍ የማዳበሪያ አምራቾች በቀጥታ በመሳተፋቸው ሁለት የንግድ ሰንሰለቶች ተሰብረዋል፡፡›› ሲል መናገሩ የሚታው ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም በወቅቱ ከመንግስት ጋር በመመሳጠር ሲመዘበር የነበረን 2.6 በሊዬን ብር ወይም 120 ሚሊዬን ዶላር ከምዝበራ መዳኑን ገልፆ ነበር።

በሰሞነኛው የዩክሬይን ቀውስ “ኪየቭ የሚገኘው የያራ ኢንተርናሽናል ቢሮ በሚሳዔል ተመቷል።” በማለት ቢቢሲ መፃፉ ይታወሳል። ሀገረ ሩሲያም የማዳበሪያ ምርት እንዲቆም ማዘዟ አይዘነጋም። ቢቢሲ አማርኛ ስለዚህ ጉዳይ ሲዘግብ አለማቀፍ አንድምታውን ከማሳየት ይልቅ ያራ ወደተባለው ማዳበሪያ አምራች መወገኑን ነበር ያንፀባረቀው። አውሮፓ ውስጥ ምግብ ለማምረት ጥቅም ላይ ከሚውሉ ግብዓቶች ከሩብ በላይ የሚመጣው ከሩሲያ ነው።” የሚለው ቢቢሲ የያራ ኢንተርናሽናል ሀላፊ ተናገሩት በማለትም “ዓለም በቀጣይ ከሩሲያ ጥገኝነት መላቀቅ አለባት።” ሲል ፅፏል። ይህ በወቅቱ ሞስኮን ከአውሮፓ የመነጠል የብሪታኒያ እና አሜሪካ አጀንዳ አካል መሆኑ ነበር – በነበር ቀረ እንጂ።

ሩሲያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በርካታ የግብርና ምርቶች አምራቾች ናት። ከግብርና ምርቶች ባለፈ ለማዳበሪያ እጅግ አስፈላጊ የሆኑትን ፖታሽና ፎስፌት የተሰኙ ነጥረ ነገሮች በገፍ ታመርታለች።
“ከግማሽ በላይ የዓለም ሕዝብ ምግብ የሚያገኘው በማዳበሪያዎች ምክንያት ነው። ይህ ማዳበሪያ ከእርሻ ሥፍራ ከጠፋ ምርት 50 በመቶ ቀነሰ ማለት ነው” ይላሉ የያራ ኩባንያ ሀላፊ።
የማዳበሪያ ግብአት የሆነውን አሞኒያ ለማምረት በርካታ የተፈጥሮ ጋዝ የሚፈልግ ሲሆን፤ ያራ ኢንተርናሽናል አውሮፓ ውስጥ ይህንን ለማምረት በሩሲያ የተፈጥሮ ጋዝ ላይ ጥገኛ ነው።
ሀላፊው እንደገለፁት “በአንድ በኩል ለግብርና ምርት ስንል የማዳበሪያ ምርት እንሻለን። በሌላ በኩል ሩሲያ ዩክሬን ላይ የፈፀመችውን ወረራ እናወግዛለን። ይህ እውነት ለመናገር ከሁለት አንድ እንደማጣት ነው።” ብለዋል።

ሩሲያ 20 በመቶውን የአለም ማዳበሪያ ትሸፍናለች። ቻይና ጉዳዩን እንደ ካርድ ትጠቀማለች እየተባለ ሲሆን፤ ቻይናና ሩሲያ በጥምረት አለምን 45 በመቶ ፎስፌት አቅራቢ ናቸው። ሰሞነኛው የሩሲያ የማዳበሪያ ሽያጭ አገዳ ከአውሮፓ እስከ ካናዳና አሜሪካ ሳይቀር አለምን እየተጫነ የሚገኝ ስጋት ሆኗል።

ስቶን ኤክስ የተባለው ኩባንያ ሀላፊ ስለጉዳዩ ተጠይቀው ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። ሀላፊው ሊንቪል እንዳሉት፣ “አሁን ላይ ቻይና ማዳበሪያ ኤክስፖርት ማድረጓን እንዳታቆምብን ትልቅ ትኩረትም ሰጥተን እየሰራን ነው። ነገር ግን ቻይና የማዳበሪያ ኤክስፖርቱን አቁማ “ሩሲያ ላይ ያደረጋችሁት ሁሉ በኛ ላይ እንደተሰነዘረ ጥቃት ነው የምናየው ብትለንስ? ቤይጂንግ ወደ ታይዋንን ልገሰግስ ነው ብትለንስ? ከዚያም፣ ሩሲያ ላይ ያደረጋችሁትን ሁሉ በቻይና ላይም ልታደርጉት?” ብትለንስ? ያኔ ዛሬ ካለንበት አስቸጋሪ ሁኔታ መኖሪያህ በየትኛውም የአለም ክፍል ቢሆን እጅግ ከባዱን አደጋ ታስተናግዳለህ።” ነው ያሉት።

?ኢትዮጵያ – የመሬት ማዳበሪያ አቅርቦት
ኢትዮጵያ ለማዳበሪያ ግዢ 27.2 ቢሊዬን ብር (ከ 660 ሚሊዮን $ በላይ) ያወጣችው ባለፈው አመት ነበር።
ኬኒያ በተመሳሳይ አመት ለማዳበሪያ ኬሚካልና ዘር ግዢ 65.7 ቢሊዮን የኬኒያ ሽልንግ (578 ሚሊዮን $) ወጪ አድርጋለች።

ለ2014/15 የምርት ዘመን ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገባው ከ1.28 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ከ880ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ /69%/ ወደብ የደረሰ ሲሆን፣ ከ755ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ የሚሆነው ደግሞ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል፡፡

የአፈር ማዳበሪያውን በባሕር የማጓጓዝ ስራው በዓለም-አቀፍ የመርከብ ድርጅቶች 23 ግዙፍ መርከቦች ተመድበውለታል። ከነዚህ መርከቦች 13ቱ NPS ለሚባለው የአፈር ማዳበሪያዎች፣ 10ሩ ደግሞ ለዩሪያ የተመደቡ ናቸው፡፡ 
ጠቅላላ ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገባው የአፈር የማዳበሪያ መጠን ውስጥ 787ሺ ሜትሪክ ቶን ኤን.ፒ.ኤስ ማዳበሪያ ሲሆን ቀሪው 500 ሺህ ሜትሪክ ቶን ዩሪያ ነው፡፡ በ13 መርከቦች ከሞሮኮ ሲጓጓዝ የነበረው NPS ማዳበሪያ ሙሉ በሙሉ ጅቡቲ ወደብ ደርሷል፤ ባሳለፍነው ሳምንት ጅቡቲ የደረሰችው የመጨረሻዋ መርከብ በማራገፍ ላይ ትገኛለች፡፡
ከሚያዝያ አጋማሽ ጀምሮ ከኤምሬትስና ግብጽ እየተጓጓዘ ካለው ዩሪያ ማዳበሪያ ውስጥ የሁለት መርከቦች ጭነት ወደብ ደርሶ ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ ነው። 3 መርከቦች ሁለቱ እያንዳንዳቸው 45ሺ እና አንዷ 50 ሺህ በድምሩ 140 ሺህ ሜትሪክ ቶን ከግንቦት 18-21 ባሉት ቀናት ጂቡቲ ወደብ እንደሚደርሱ ተገልጿል።

Esleman Abay #የዓባይልጅ

https://t.me/eslemanabayy/559

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories