የቀድሞዋ ራሽያ ፌዴሬሽን የአሁና ሩሲያ አፍሪካዉያን ለነፃነት ያደረጉት የነበረዉ ትግል በመደገፍ ያበረከተችዉ አስተዋጽኦ በአብዛኛው አፍሪካዉያን ልብ ዉስጥ በደማቅ ሁኔታ ተከትቦ ይገኛል። ይህም እዉነት ራሽያ በቀላሉ በነፃነት ማግስት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የቀረበ ወዳጅነት ለመመስረት መንገደ ከፍቷል።
ወቅቱ በምስራቁና በምዕራቡ ገራ የነበረው ፍጥጫ ጫፍ የደረሰበትና የጎራ መደበላለቁ ቡዙ የአፍሪካ ሀገራት ወዳጅ ለማፍራት ከቀኝ ወደ ግራ የሚባክኑበት የቀዝቃዛዉ ጦርነት ወቅት ነበር።
የቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት ተከትሎ በ1990|ቹ የራሽያ ፌዴሬሽን መበታተንና በሩሲያ የነበረዉ የኢኮኖሚ መቀዛዘቅ ሀገሪቱ በዉጭ ሀገራት የነበሩዋት ጥቅሞችና እንደ የባህልና የኢኮኖሚ ማዕከሎችን ያሉ ተቋሞችን መዝጋት አልያም ከሚጠበቀው በታቸ እንዲቀሳቀሱ ያስገደደበት ወቅት ነበር። ሩሲያ በአፍሪካ ከሚገኙ 20 የባህል ማዕከላቶችዋ 13ቱን እንዲዘጉ አድርጋለች። ኩነቱም ቡዙ የአፍሪካ አገራት ዉስጥ የመንግስታት ለዉጥና የርዮተ ዓለም ለዉጥ እንዲመጣ ምክንያት ሆኗል።
የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ሩሲያ ከአህጉሪቱ ጋር የነበራትን የተለያዩ ግንኙነቶች ያዳከመበት ሲሆን ለምሳሌ ሩሲያ በአህጉሪቱ ከነበሩዋት የአየር ጉዙዎች መዳረሻ አብዛኞቹ የተቋረጡ ሲሆንና የተለያዩ የሁለትዮሽ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲታጠፉ አልያም እንዲቋረጡ ሆኗል። በወቅቱ በሩሲያ ባንኮች ላይ የተጣለው አለም አቀፍ ማዕቀብ ሩሲያ በአፍሪካ ዉስጥ በዘርፉ ያላትን ድርሻ ቀንሷል።
ቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት ተከትሎ ሀገሪቱ ወደ ኢኮኖሚ ማገገሚ ፖሮግራሞችና የዉስጥ አጀንዳዋች ላይ መጠመድዋ ሩሲያ በዉጭ ፖሊስዋ በይበልጥ አፍሪካ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ላይ የላላበት ሆኔታ ነበር።
እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ ዘገባ በ2008 እ.ኤ.አ ሩሲያ በአፍሪካ ከ20 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ የማዕለ ንዋይ ማፍሰስዋን የተመዘገበ ሲሆን ነገር ግን በ2009 እ.ኤ.አ የዲሚትሪ ሜድቨዴቭ የአፍሪካ ጉብኝት ተከትሎ ቀዝቅዞ የነበረዉ የአህጉሪቱና የሩስያ ግንኙነት የማንሰራራት ምልክት አሳየ።
ይህም ተከትሎ በተሰራ ስራ ከአስር አመት በኋላ የመጀመሪያ የአፍሪካ ሩስያ የጋራ ጉባኤ ለማዘጋጀት መነሻ ሆነ።
ሩሲያ በአፍሪካ የነበራትን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ግንኙነት መልሶ ለማደስ በጥቁር ባህር የመዝናኛ ከተማ በሆነችዉ በሶሺ ከጥቅምት 12-13 2012 ዓ.ም በተካሄደው የመጀመሪያው የአፍሪካ-ሩሲያ ጉባኤ ሩሲያ በአፍሪካ ያላትን አዳዲስ እቅዶች ይፋ ያረገችበትና በዛ የለ የሁለትዮሽ ስምምነቶች የተፈረመበት ወቅት ሆኖ አልፋል።
የስብሰባው መሪ ቃል የነበረው “የሩሲያ -አፍሪካ ጉባኤ፦ ለላቀ ግንኙነት ለአፍሪካ” የሚል ነዉ ኩነቱ የዓለምን ትኩረት ስቦ የሰነበተ ሲሆን በተለያዩ አካላት የተለያየ እይታ ሲስጠዉ ከርሟል።
አንዳንድ ሚዲያዎች የሞስኮ ዉሳኔና አካሄድ ድጋሚ አፍሪካን ከመቀራመት አጀንዳ ጋር አዛምደው ሲዘግብ ከርመዋል።
የብዙ የዘርፉ ተንታኞች ግራ ያጋባዉና ብዙ ያስባለዉ ለምን አሁን የሚለዉ ጥያቄ ነዉ? በመቀጠልም በምን አይነት መንገድ ሩሲያ የቀድሞ ጥቅሞችዋንና ፍላጓትዎን ልታሳካ ትችላለች የሚለዉ ጥያቄ ነዉ?
ምክንያት የ1990ቹ ራሺያ ከአሁንዋ ሩሲያ መካከል ባለ የሮይዕተ አለም ልዪነት፤ የዓለም ወቅታዊ አሰላለፍ፤ እና የሩሲያ ቀብልነት በአህጉሪቱ ሀገራት መካከል የታሰበዉ ግንኙነት ላይ እንቅፋት እንዳይሆን ስጋት አለኝ።
ሶሺ ትኩረት
በሶሺ የነበረው ጉባኤ ትልቅ ትኩረት ስቦ የነበረዉ በፕሬዝዳንት ቨላድሚር ፖቲንና በግብፅ አረብ ሪፐብሊክና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንበር ፕሬዚዳንት አል ሲሲ የተመራዉ የሰላም የደህንነትና የልማት ኮንፈረንስ ተጠቃሽ ነዉ። ኮንፈረንሱ በሩሲያና በአፍሪካ መካከል ሊኖር ሰለሚገባዉ ትብብር ያጠነጠነ ሲሆን ስብሰባውን ተከትሎ በሩሲያና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መካከል የተለያዩ የንግድ እና በኢንቨስትመንት ዙርያ ስምምነት ተደርጓል።
ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስና አዲስ ግንኙነት ለመመስረት አህጉሪቱ ለ20 አመታት የተጠራቀመ 20 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እዳ የተሰረዘ ሲሆን በአህጉሪቱና በሩሲያ መካከል የነበረ ግንኙነት ለማጠናከር ስምምነት ላይ ተደርሷል። በአሁኑ ሰዓት ከ10,000 በላይ የአህጉሪቱ ዜጎች በሩስያ የከፍተኛ ትምህርት ገብተዉ እንዲማሩ ተደርጓል።
የተቋረጠው የሚመስለው የሩሲያና የአፍሪካ ግንኙነት የማዳከም ምልክት ሲያሳይ የነበረ ሲሆን ሩሲያና የአፍሪካ ሀገራት ጋር የተሻለ ግንኘነት ለመመስረት ጥረቶች ነበሩ ሆኖም በአሁኑ ሰዓት የሩሲያ-አፍሪካ የንግድ ግንኙነት ከሩሲያ የዉጭ ንግድ ሲሰላ ከ3% ያነሰ ነዉ።
እንደ ሩሲያ የዉጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጄ ላቭሮቭ በሶሺ በነበረ ጉባኤ ላይ በደረጉት ንግግር ሩስያ ሁሌም ቢሆን አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ዉስጥ ሊኖራት ስለሚገባዉ ቦታ ቋሚ ዉክልና ጥያቄ ከአፍረካ ጎን የምትቆም መሆንዋን ያረጋገጡ ሲሆን በቀጣይም ሩስያ አብሮ ለመስራትና ለማደግ ያላትን ቁርጠኝነት አንፀባርቀዋል።
በሩሲያና በአፍሪካ መካከል ሊኖር የሚችል ግንኙነት ማጠንጠኛው?
ከሰላምና ደህንነት ሊህቃን ዘንድ ያለዉ ግንዛቤ ሩስያ በአብዛኛው ከአፍሪካ ያላት ግንኙነት ማጠንጠኛዉ የሀይል አቅርቦት፤ የማዕድን ዘርፍና ከጦር መሳርያ ሽያጭ ጋር የተያያዘ ነዉ።
ሩስያ በተደጋጋሚ ጊዜ በተባበሩት መንግሥታት በሚቀርበባት ክስ ማዕቀብ ለተጣለባቸዉ ወይም በህግ ገደብ የተደረገባቸው የጦር መሳርያ አይነቶች ሽያጭ ህግ በመተላለፍ ሸጣለች የሚል ነዉ።
ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት በሁለት አጀንዳዎች ላይ ያጤናል የሚል መላ ምት አለ። አንድኛ በአፍረካ የተፈጥሮ ሀብት ላይ የሩሲያዉያን ባለሀብቶች የማልማት አጀንዳ ሲሆን።
በሩሲያ መንግስት ባለ ድርሻ የተያዙት እንደ ጋዝፖሮም፤ ሉክኦይል፤ ሮስቴክ እና ሮሳአቶም ኩባንያዋች እና ሩስያ በዝንቧቡዌ የምታለማዉ የአለም ግዙፍ የፖላቲንየም ቀጠና እንዲሁም በአንጎላ በድጋሚ የሚቆፈረዉ የዳይመንድ ጉድጓድ እና የአለማችን 7% የሚሆነዉን በናሚቢያ የሚገኘዉን ዩራንየም ማዉጪያ በአፍሪካ ያላትን አጀንዳ እንደማጠናከርያነት ያቀርቡታል።
የተጨበጡ መረጃዎች ባይገኙም እንደ ISPIonline እና ቢቢሲ ምርመራ መረጃ ሩሲያ በማዳካስካር ምርጫ ሂደት ዉስጥ መግባቷ በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፐብሊክ የሩሰያ የግል ቅጥር ወታደሮች በዋነኝነት የዳይመንድና ወርቅ ማዉጫ አካባቢ መጠበቃቸው እና ለሀገሪቱ ዋነኛ የጦር መሳርያ አቅራቢ መሆንዋ በቅርቡ ከስልጣን በአመፅ የለቀቁትና በእስር የሚገኙት የሱዳን የቀድሞ ፕረዚዳንት ኡመር አል በሽር ዋነኛ የጦር መሳርያ አቅሪቢ እንደሆነች ይታመናል።
አገሪቱ በአንዳንድ ሀገራት ዉስጥ የጦር ሰራዊት የማስታጠቅና የማዘመን እና የደህንነት ተቋማትን የሚደረጉ ተከታታይነት ያላቸዉ ድጋፎች በምዕራቡ አለም ዘንድ በበጎ አይታይም።
ሩሲያ በሀይል አቅርቦትና በሚሊተሪ ዲፖሎማሲ እራሷን ከአፍሪካ የልማት አጀንዳ ጋር የማስተሳሰር በሀይል አቅርቦት፤ በተፈጥሮ ጋዝ፤ ዘይት አና በኒኩለር ሀይል ማመንጫዎች ለማስተሳሰር እየተሰራ ነዉ።
ሁለተኛዉ በሩሲያ ትኩረት የሚሰጠዉ የአፍሪካ ሀገራት የምታቀርበዉ የጦር መሳሪያ ሽያጭ፤ የደህነት ቴክኖሎጂዎች ሽግግርና ድጋፎች ላይ ያተኩራል።
በአለማችን ከአሜሪካ በመቀጠል ሁለተኛ ትልቋ የጦር መስርያ ለዉጭ ገበያ አቀራቢ የሆነችው ሩስያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋራ ከ20 በላይ የሚሆኑ የጦር ስምምነት ህብረት ፊርማ ያላት ሲሆን አልጄሪያ ግብፅና አንጎላ ከአፍሪካ ዋነኛ የጦር መሳርያ ገዚ ሀገራት ናቸዉ።
የሩሲያ-የአፍሪካ ትብብር መድረክ ትኩረት ሰጥቶ ወይይት ከተደረገበት አጀንዳዋች መካከል የሽብር እንቅስቃሴዎች መከታተል፤ መረጃ መቀያየር ፖሮቶኮል እና የጋራ የጦር ልምምድ የካተተ ነዉ።
ሩሲያ፤ የተባበሩት መንግስታት እና አፍሪካ ህብረት
በተለያየ አጋጣሚ ሩስያ በተባበሩት መንግስት ጥላ ስር በሚመራ በአፍሪካ ዉስጥ የተከሰቱ ግጭቶችን ለማብረድ የሰላም አስከባሪ ጦር ሰራዊት በመላክ ተሳትፎ አድርጋለች። የሚነሳበት ቅሬታ የሰላም የማስከበር ሂደቶች ላይ በተመረጡና በዉስን የሰዉ ቁጥር መወከልዋ ነዉ። የሰላም አሰከባሪ ከላከችባቸዉ ሀገሮች መካከል ኮንጎ ዲሞክራቲክ፤ ምዕራብ ሳራዊ፤ ኮትዲቯር፤ ደቡብ ሱዳንና ሊቢያ በምሳሌነት ይጠቀሳሉ ።
የአፍሪካዉያን አጀንዳ አፍሪካዊ መፍትሄ ነዉ የሚያስፈልገዉ በሚል አቋሟ የምታውቀው ሩሲያ በፀጥታ ምክር ቤት ያላትን ቋሚ መቀመጭያና ድምፅ በድምፅ የመሻር መብቷን በመጠቀም በተለያዩ ጊዜአት በአህጉሪቱ አባል ሀገራት ላይ የሚነሳ ክሶችን ማምከኗ ከቡዙ አፍሪካ ሀገራት ሙገሳን ያሰገኘትሎታል። በተመሳሳይ የአፍሪካ ሀገራት በሩሲያ ላይ የሚነሱ ክስችን ሲቻል በመቃወም ካልሆነ ድምፅ ታቅቦ ድምፅ በመስጠትም ይታወቃሉ። ለእዚህ ማሳያ የሚሆነው በክርሚያና በዩክሬን ጉዳይ ላይ በሩሲያ ላይ የተነሳዉን ክስና የወቅቱ የአፍሪካ ተለዋጭ የተባበሩት መንግስት የፀጥታ ምክር ቤት ዉሳኔ ማየት ይቻላል።
የሩሲያና የአፍሪካ ትብብር ከእዚህ ቀድም አፍሪካ ከሌሎች ሀገራት ህብረት ጋር የተለየ የሚያድርገዉ ሩስያ በአፍሪካ ያላት ፍላጎት የተገደበ እና በዉስን ትብብሮች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ነዉ። ሩሲያ ከአፍሪካውያን አጀንዳ ላይ ከቻይና ጋር ተቀራራቢ የሆነ አቋም ታንፀባርቃለች ። ነገር ግን ቻይና ከአህጉሪቱ ጋር የጋራ ትብብርን በመመስረት በ20 አመት ትቀድማለች።
ሶሺና መድረክ: ታላቁ የህዳሴ ግድብ
መዉጫዬ ላድርግ በቅርቡ የአፍሪካ ህብረት ከሩሲያ ጋር ያለዉን የትስስር ለማጠናከር የትስስር ቢሮ በሞስኮ ይከፍታል ተብሎ ይጠበቃል።
ትብብሩ ለአህጉሪቱ ተጨማሪ ምን ያስገኝ ይሆን? የእኔም ጥያቄ ነዉ።
ህዳር 2019