ሸክሲያት ኢትዮፒያ Shakhsiyat Ethiopia

አዲስ መፅሐፍ በአረብኛ

በሀገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ሚዲያዎች ረዘም ላሉ ዓመታት የዳበረ ሙያዊ ተሞክሮ ያለው ጋዜጠኛና ደራሲ Anwar Ibrahim Anwar Ibrahim አዲስ መፅሀፍ ጀባ ብሎናል፡፡
‘’ሸክሲያት ኢትዮፒያ’’ የተሰኘው ይህ መፅሐፉ በአረብኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን በ 251 ገፆቹ የሚዘክረው በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሀገራቸውን ያስጠሩ ኢትዮጵያውያንን ስራ ነው፡፡

በመፅሀፉ የተካተቱት 50 ስመጥር ኢትዮጵያውያን ስራዎች ውስጥ የተመረጡ ታሪኮች ለተደራሲያን በውል ያልቀረቡ ሲሆኑ የቀረቡትም ቢሆኑ በአረብኛው አንባቢው ዘንድ የመነበብ እድል ያላጋጠማቸው ናቸው፡፡

ደራሲው ካለው የአረቡ አለም ታሪካዊ߹ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንዛቤ በመነሳት߹የሚዲያ ትንተናዎች በመስጠትና አርቲክሎች በመፃፍ ከሚያደርገው አስተዋፅኦ በተጨማሪ መሰል መፅሀፎችን በመድረስ የአረቡ አለምና የኢትዮጵያውያንን የጋራ ግንዛቤ የማስፋት አላማ አንግቦ በመስራት ላይ ይገኛል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ኢትዮ-አፍሪካ ሚዲያ እና ኮምኒኬሽን የተሰኘ ተቋም መስርቷል፡፡

በዚህ መፅሀፍ የታዋቂ ኢትዮጵያውያን ፖለቲከኞች߹ የስነ ፅሁፍ ሰዎች߹ ብሄራዊ ጀግኖች ወዘተ… ዋና ዋና ስራዎች በጥሩ አገላለፅ ተተርኳል፡፡
ለአረብኛ ቋንቋ አንባቢዎች በአንድ መፅሀፍ ከሀምሳ በላይ ባለ በጎ ታሪክ ሰዎች መተዋወቅ ትልቅ እድል ነው፡፡
መፅሐፉን ያንብቡ! ገዝተው የራስዎ ያድርጉት ለወዳጆችዎ ምርጡ ማስታወሻ የሆነው መፅሐፍን ያበርክቱ!

▪️በጋዜጠኛ እና ደራሲ አንዋር ኢብራሂም
▪️ኢትዮ አፍሪካ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን

ሸክሲያት_ኢትዮፒያ #Shakhsiyat_Ethiopia

ኢትዮአፍሪካሚዲያና_ኮሚኒኬሽን

Ethio_Africa_Media_and_Communication

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories