ሃይድሮሎጅይ የሚለው ቃል ከሁለት ቃላት ማለትም ሃይድሮውሃ እና ሎጂኣጥናት ከሚሉት የግሪክ ቃላትየተዋቀረ ሲሆን ስነ-ውሃ ጥናት ማለት ነው፣ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሙያዊ ፍቺው ደግሞ ውሃ ማለት ሁለት ሃይድሮጅን two hydrogen እና አንድ ኦክሲጅን one oxygen በጥቅሉ ኤችቱኦ H2O ነው፣ ይህ የስነ-ምርምር ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው፣ ይህን ስነ-ውሃ ጥናት ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ ነጥብ በነጥብ እናየዋለን፦
ነጥብ አንድ
ስነ-ፍሰት Fluid
24:45 አላህም ተንቀሳቃሽን دَابَّةٍ ሁሉ ከውሃ ፈጠረ፤
ተንቀሳቃሽ የሚለው የአረቢኛው ቃል ዳብበት دَآبَّة ሲሆን ቁስን matter ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፣ ቁስ አራት ፍሰቶች Fluids አሉት እነርሱም፦ ሊኩድ liquid፣ ሶሊድ solid፣ ጋዝ gas፣ ፕላዝማ plasma ናቸው፣ ቁስ የተሰራበት ንጥረ-ነገር ውሃ መሆኑን የደረሰበት ሬኔ ደስካተርስ በ 1650 AD ሲሆን ቁርአን ግን ይህ ግኝት ከመደረሱ ከ 1200 አመት በፊት ነው አላህ የነገረን፦
6.67 ለትንቢት نَبَإٍ ሁሉ የሚደርስበት መርጊያ አለው፡፡ ወደፊትም ታውቁታላችሁ፡፡
ነጥብ ሁለት
ስነ-ህዋስ cell
21:30 ሕያው حَيٍّ የኾነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን አያምኑምን?
25:54 እርሱም ያ ከውሃ ሰውን የፈጠረ፣ የዝምድናና የአማችም ባለቤት ያደረገው ነው፤ ጌታህም ቻይ ነው።
ሕያው የሚለው የአረቢኛው ቃል ሃይይ حَيّ ሲሆን ህይወት ማለት ነው፣ የመውት مَوْت ተቃራኒ ሆኖ መጥቷል፦
30:19 ሕያውን ከሙት ያወጣል፤ ሙትንም ከሕያው ያወጣል፤
3:27 ሕያዉንም ከሙት ዉስጥ ታወጣለህ፤ ሙትንም ከሕያዉ ዉስጥ ታወጣለህ፣ ለምትሻዉም ሰዉ ያለግምት ትሰጣለህ።
10:31 ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን» በላቸው፡፡
6:95 አላህ ቅንጣትንና የፍሬን አጥንት ፈልቃቂ ነው፡፡ ሕያውን ከሙት ያወጣል፤ ሙትንም ከሕያው አውጪ ነው፡፡
ህያው የተባለውን ኢነርጂ ሲሆን ሙት የተባለው ደግሞ ግኡዝ ነው፣ አላህ ከኢነርጂ ግኡዝን ከግኡዝ ደግሞ ኢነርጂን ያወጣል፣ ይህም ኢነርጂ መሰረቱ ውሃ ነው፣ ይህን በሃይድሮ ኤለትሪክ ፓወር ተረጋግጧል፣ የሰው፣ የእንስ ሳት፣ የዕጽዋት ህይወት መሰረቱ ሴል መሆኑን ሴል ደግሞ ከመቶ 70% ውሃ መሆኑ ተረጋግጧል፣ ልብና አንጎል ከመቶ 73% ፣ ሳንባ ከመቶ 83%፣ ቆዳ ከመቶ 64%፣ ጡንቻና ኩላሊት ከመቶ 79% ፣ አጥንት ከመቶ 31% ፣ በጥቅሉ የሰው አካል ከመቶ 75% ውሃ መሆኑን ጥናቶች ያመላክታሉ፣ ይህ የተረጋገጠው በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን አጋማሽ ወዲህ ሲሆን አላህ ግን በቁርአን የነገረን ቀድሞ ነው፦
38.87-88 «እርሱ ቁርኣን ለዓለማት መገሠጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ትንቢቱንም نَبَأَهُ ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡»
ነጥብ ሶስት
ስነ-ባህር Oceanology
55:19 ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲሆኑ ለቀቃቸው። እንዳይዋሐዱ በመካከላቸው ጋራጅ بَرْزَخٌ አልለ፤ አንዱ ባንዱ ላይ ወሰን አያልፍም፤
25:53 እርሱም ያ ሁለቱን ባሕሮች፣ አጐራብቶ የለቀቀ ነው፤ ይህ ጥምን የሚቆርጥ ጣፋጭ ነው፤ ይህም የሚመረግግ ጨው ነው፤ በመካከላቸውም ከመቀላቀል መለያንና የተከለለን ክልል ያደረገ ነው።
27:61 በሁለቱ ባሕሮችም በጣፋጩና በጨው ባሕር መካከል ግርዶን ያደረገ ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?
35:12 ሁለቱ ባሕሮችም አይተካከሉም! ይህ ጣፋጭ ጥምን ቆራጭ፣ መጠጡ በገር ተዋጭ ነው፤
የፓስፊክ ውቂያኖስ፣ የአትላንቲክ ውቂያኖስ፣ የአርክቲክ ውቂያኖስ፣ የኢንዲያን ውቂያኖስ፣ የሜድትራንያን ባህር በውስጣቸው ጨዋማና ጨዋማ ያልሆነው ሁለት ክፍል አለው፣ ሁለቱ ክፍሎች እንዳይገናኙ በመካከላቸው ግርዶሽ አለ፣ ይህን ግርዶሽ ቁርአን በርዘክ بَرْزَخٌ ጋራጅ ይለዋል፣ ይህ ምርምር የታወቀው በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን አጋማሽ ወዲህ ነው፣ ታዲያ ይህ እንደሚሆን በበረሃ ያለ አንድ ግመል ገፊ መሃይም እንዴት ሊያውቅ ቻለ? ፦
78:1-4 ከምን ነገር ይጠያየቃሉ? ከታላቁ ትንቢት النَّبَإِ ከቁርአን ይጠያየቃሉ ። ከዚያ እነሱ በርሱ የተለያዩበት ከሆነው። ይከልከሉ፤ ወደፊት የሚደርስባቸውን በእርግጥ ያውቃሉ።
ነጥብ አራት
ትነተ-ስርገት Evaporation
67:30 አያችሁን? ውሃችሁ ሰራጊ ቢሆን ፈሳሺን ውሃ የሚያመጣላችሁ ማን ነው? በላቸው።
86:11 የመመለስ ባለቤት በሆነችው ሰማይም እምላለሁ።
56:68-69 ያንንም የምትጠጡትን ውሃ አያችሁን? እናንተ ከደመና አወረዳችሁትን? ወይስ እኛ አውራጆቹ ነን?
ከሰማይ የሚወርደው ውሃ ተመልሶ ወደ ሰማይ እንደሚተን የተረጋገጠው በኬነቲክ በ 1905 AD ላይ ነው፣ ነገር ግን አላህ በቃሉ የተናገረው ግን ይህ ግኝት ከመደረሱ ከ 1500 አመት በፊት ነው፣ ታዲያ ይህ ሃቅ የሩቅ ነገር ሚስጥር አይደለምን?
38:67 በላቸው «እርሱ ቁርኣን ታላቅ ትንቢት نَبَأٌ ነው፡፡ «እናንተ ከእርሱ ዘንጊዎች ናችሁ፡፡
መደምደሚያ
ነቢያችን የማይጽፉና የማያነቡ ነበሩ፦
29:48 ከርሱ በፊትም መጽሐፍን የምታነብ በቀኝህም የምትጽፈው አልነበርክም፤ ያን ጊዜ አጥፊዎቹ በእርግጥ በተጠራሩ ነበር።
7:157 ለነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነብይ የሆነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለሆኑት በእርግጥ እጽፋታለሁ፤
፦
ታዲያ ነቢያችን የማይጽፉና የማያነቡ ከነበሩ ይህ ድንቅ ምስጥር ከየት ሊያገኙት ቻሉ? ለሚለው ጥያቄ መልሱ አላህ በአጽናፎችና በራሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ታምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን ብሎ ቃል በገባው መሰረት ዛሬ ስነ-ውሃ ጥናትን አይተናል፦
41.53 እርሱም ቁርአን እውነት መሆኑ ለነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ፣ በአጽናፎቹ ውስጥና በራሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን ታምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን፤ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ መሆኑ አይበቃቸውምን?
27:92-93 ቁርአንንም እንዳነብ ታዝዣለሁ የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ብቻ ነው፤ የተሳሳተም ሰው እኔ አስጠንቃቂ ነኝ እንጂ ሌላ አይደለሁም በላቸው፣ ምስጋና ለአላህ ነው፤ ታምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፤ ታውቁታላችሁ በላቸው፤
የስነ-ውሃ ጥናት ዋቢ መጽሐፍት ይመልከቱ፦
1.ALMA Greatly Improves Capacity to Search for Water in Universe”. Retrieved 20
2.Anderson, Malcolm G.; McDonnell, Jeffrey J., eds. (2005). Encyclopedia of hydrological sciences.
3.Hendriks, Martin R. (2010). Introduction to physical hydrology. Oxford: Oxford University Press.July 2015.
ወሰላሙ አለይኩም