በሃይማኖትም ይሁን በብሔር ጉዳይ ያልተመለሱ ጥያቄዎችን የውጭ ኃይሎች በተለይም ግብፆች ኢትዮጵያን ለማወክ እየተጠቀሙበት ነው

https://t.me/eslemanabayy/832

▪️በኢትዮጵያ በሃይማኖትም ይሁን በብሔር ጉዳይ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ የሚለው እስሌማን
የውጭ ኃይሎች በተለይም ግብፆች በውይይትና በንግግር
ይፈታሉ እያልን በይደር ያቆየናቸውን ጉዳዮች ወደ ግጭት
እንዲያመሩ በማድረግ የኢትዮጵያን ሰላም ለማወክ
እየተጠቀሙበት መሆኑን ይናገራል።

▪️”Egyptian Center for Strategic Study የሚባለው የግብፅ የጥናት ተቋም ከወር በፊት በኢትዮጵያ
ጉዳይ ያወጣውን ጥናት ይፋ ማድረጉን እስሌማን
ይናገራል። በዚህ ተቋም የሚደረጉ የጥናት ውጤቶች ለግብፅ የደህንነት መሥሪያ ቤት እንዲሁም ለግብፅ ውጭ ጉመስሪያ ቤት ይቀርባሉ። የጥናቶች መነሻ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ መልስ የሚሹ ጥያቄዎች ናቸው።
መሰል ጥናቶች በግብፅ መደርደሪያ ላይ የሚቀመጡ ሳይሆኑ ወደ ተግባር የሚለወጡ ናቸው።”

▪️ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ይዘው የሚመጡትን ስውር የጣልቃ ገብነት አጀንዳ መመከት የሚያግዝ የህግ አግባብ ቢቀርፅ ችግሮቹን ማቃለል ይቻላል ብሏል።

▪️ጋዜጠኛ እስሌማን ወጣቱ ለጥያቄዎቹ
መፈታት የሚጓዝባቸው አካሄዶች የሀገር ውስጥ እንጂ የውጭ ኃይሎች በቀየሱለት መንገድ ሊሆን እንደማይገባ ይገልጻል።

===================================

አዲስ ዘመን: በዛሬው የወጣቶች አምድ ዝግጅታችን ወጣቶች መልኩን በየጊዜው እየቀያየረ ስለሚገኘውና አሁንም ሃይማኖታዊ መልክ ይዞ በተከሰቱ ሁነቶች ጀርባ የውጭ ጠላት ደባ ማስተዋል እንደሚሻ ምን ያህል ግንዛቤ አላቸው?
ወጣት እስሌማን አባይ /የአባይ ልጅ/ አገራዊና
ወቅታዊ ጉዳዮችን እየተከታተለ ጠቃሚ
ሀሳቦችን በማህበራዊ ሚዲያዎች በማጋራት ይታወቃል።
በተለይም በህዳሴው ጉዳይ ዙሪያ የግብጾችን ሴራ እና
የምዕራባዊያንን ጫና አስመልክቶ በርካታ ቁም ነገሮችን
አስነብቦናል። በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ ኢትዮጵያ
ውስጥ ከሚፈጠረው ትርምስ ጀርባ የውጭ ኃይሎች
እንደሚገኙበት እምነቱ ነው። በተለይም ግብፅ ከታላቁ
ህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ በየጊዜው በጥናት የተደገፉ
ሴራዎችን እየፈበረከች በጥቅም ለገዛቻቸው አካላት
ማስታጠቋ የአደባባይ ምስጢር እንደሆነ ይናገራል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በሃይማኖትም ይሁን በብሔር ጉዳይ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ የሚለው እስሌማን
የውጭ ኃይሎች በተለይም ግብፅች በውይይትና በንግግር
ይፈታሉ እያልን በይደር ያቆየናቸውን ጉዳዮች ወደ ግጭት
እንዲያመሩ በማድረግ የኢትዮጵያን ሰላም ለማወክ
እየተጠቀሙበት መሆኑን ይናገራል።
ሕወሓት ከስልጣን መልቀቁን ተከትሎ በመንግሥት
እና በቡድኑ መካከል የተፈጠረውን ጦርነት የውጭ
ኃይሎች እንደጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ሕወሓትን
በፕሮፓጋንዳ፣ በፋይናንስ እርዳታ እና በመሳሰሉት
በመደገፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ማሳካት የሚፈልጉትን ጥቅም
ለማስከበር ሲጥሩ እንደነበር እስሌማን ያስታውሳል።
በወቅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ
ምዕራባዊያን፣ ግብፅና ሱዳን ሲፈጽሙ የነበረው ሴራ
የሚታወስ ነው። ሕወሓት በጦርነት በትረ ስልጣኑን
መልሶ እንዲቆጣጠርና ጥቅማቸውን እንዲያስከብርላቸው
የነበራቸው ፍላጎት ከፍተኛ ስለነበር በኢትዮጵያ መንግሥት
ላይ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን
የማሳደርና ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን እየተጠቀሙ ሥም
የማጠልሸቱን ሥራ ሲሠሩ ነበር። ሕወሓትአሸንፎ ስልጣን እንደማይዝ ሲያረጋግጡ ደግሞ ሌሎች
አገር ያፈርሳሉ ብለው ያመኑባቸውን አጀንዳዎች እየቀረጹ
በተላላኪዎቻቸው በኩል ለማስፈጸም እየሞከሩ ናቸው
ይላል። ከነዚህም አንዱ ሰሞኑን ያየነው የሃይማኖት
ግጭት ነው።
ጋዜጠኛ እስሌማን እንደሚናገረው፤ በግብጽ አገር
የትኛውም ፕሬዚዳንት መጥቶ ቢሄድ ኢትዮጵያ ከአባይ
ወንዝ ጋር በተያያዘ የግብፅ የምንግዜም ተቀናቃኝ ተደርጋ
መታየቷ አይቀርም። ማንም ይምጣ ማንም ይሂድ
ግብፅ በአባይ ላይ ያላት ጥቅም አይቀየርም። ስለዚህ
ጥቅማቸውን ለማስከበር የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም።
ፕሬዚዳንት አብዱልፈታ አልሲሲ ከአመት በፊት
የኢትዮጵያ መንግሥት ከአሸባሪው ሕወሓት ጋር ጦርነት
ውስጥ ሲገባ ቀጣናው ወደ ትርምስ ይቀየራል እያሉ
ሲያስጠነቅቁ እንደነበር የሚታወስ ነው ይላል። የጦርነቱ
ሁኔታ ብዙም እንደማያስኬዳቸው ሲረዱ ደግሞ የእርስ
በእርስ ግጭት የሚቀሰቀስባቸውን ስስ ብልቶች እያጠኑ
ተግባራዊ ለማድረግ ይሞክራሉ።
Egyptian Center for Strategic Study የሚባል
አንድ የግብፅ የጥናት ተቋም ከወር በፊት በኢትዮጵያ
ጉዳይ ያወጣውን ጥናት ይፋ ማድረጉን እስሌማን
ይናገራል። ተቋሙ በግብፅ መንግሥት ፈንድ የሚደረግ
ነው። በዚህ ተቋም የሚደረጉ የጥናት ውጤቶች ለግብፅ
የደህንነት መሥሪያ ቤት እንዲሁም ለግብፅ ውጭ ጉመስሪያ ቤት ይቀርባሉ። ለሕዝብ መገለጽ ያለባቸውም
በተለያየ መንገድ እንዲደርሱ ይደረጋል።
ጥናቱ እንደ ሌሎች ጥናቶች መደርደሪያ ላይ
የሚቀመጥ ሳይሆን ወደ ተግባር የሚለወጥ ነው። በዚሁ
መሰረት ይህ ተቋም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የተለያዩ
ጥናቶችን አድርጓል። ከነዚህ ውስጥ የሶስቱን ጥናቶች
ይዘት እንዲህ ያስረዳል። ለምሳሌ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ
የኦሮሞ ሕዝብ የፖለቲካ ውክልና እና የዲሞክራሲ
ጥያቄዎች፣ ለዘመናት ያልተሰማው ጩኸት›› በሚል
አንድ ጥናት አውጥተዋል፤ ሌላው ጥናታቸው ደግሞ
‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄደውን ግጭት ሙስሊሞች
እንዴት ይመለከቱታል›› የሚል ሲሆን፤ ሶስተኛው
‹‹እስልምናንና ክርስትናን በመጠቀም በናይል ዲፕሎማሲ
ላይ ጫና ለማሳደር ትልቁ የኃይል አማራጫችን ይሆናል››
የሚል ነው።
ለነዚህ ጥናቶች መደረግ መነሻቸው አገር ውስጥ
ያሉት መልስ የሚሹ ጥያቄዎች ናቸው። ጥናቶቹ
በሰላማዊ መንገድ ሊፈቱ የሚችሉትን የሃይማትና የብሔር
ጥያቄዎችን ቤንዚል ጠብ እያደረጉበት የእርስ በእርስ
ቀውስ ውስጥ እንድንገባ የሚያደርጉ ናቸው።
“ጥያቄ አለኝ” የሚለው አካል ደግሞ አንዳንዱ
በማወቅ፤ አንዳንዱም ባለማወቅ በሰላማዊ ውይይት
የሚፈቱ ጉዳዮችን የግጭት መንስኤ እያደረገ አጀንዳቸውን
ያስፈጽምላቸዋል።
ግብፅ በአባይ ወንዝ ጉዳይ ከየትኛውም የተፋሰሱ
አባል አገራት ግንባር ቀደም ተሰሚነት እንደነበራትና
ፈላጭ ቆራጭ እንደነበረች፣ ከደርግ መንግሥት መምጣት
በፊት ኢትዮጵያ የግብፅ ተባባሪ እንደነበረች፤ በተለይም
በአጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የራሷን ጳጳስ ከመሾሟ
በፊት ጳጳሳት በግብፅ ይሾሙላት እንደነበር በጥናቱ
ተጠቅሷል። ያ ዘመን ግብፅን ተጽዕኖ ፈጣሪ እንድትሆን
አስችሏታል ይላል። በኢህአዴግ ዘመነ መንግሥትም
ኢትዮጵያና ግብፅ እንደቀድሞው ባይሆንም ሰላማዊ
የትብብር መንፈስ እንዳላቸው ይገልጻል። አሁንም
ሃይማኖታዊ ቅርርቦችን በማጠናከር ለናይል ድርድር
መጠቀም በሚያስችል ወሳኝ ሰዓት ላይ እንዳሉ ጥናቱ
ያመላክታል።
እስሌማን እንደሚለው በትግራይና በኢትዮጵያ
የተለያዩ ክፍሎች ሁሉ ከዚህ በፊት ትምህርት ቤቶችንና
የጤና ተቋማትን እያሠሩ እንደነበር በመጥቀስ አሁንም
ይህንኑ አጠናክሮ መቀጠል አንዱ አማራጭ እንደሆነ
ጥናቱ ይጠቅሳል።
ጥናታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ፣ ለምሳሌ ኦሮሚያ ክልል
ከሰማኒያ በመቶ በላይ ሙስሊም ማህበረሰብ አለ ይላል።
ቤኒሻንጉልን፣ አፋርን፣ ሶማሌንም እያነሳ ሙስሊሙ
ማህበረሰብ አብላጫ አሃዝ እንዳለው ይጠቅሳል። ያም
ሆኖ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ፖለቲካዊ ተሳትፎው አናሳ
ነው ይላል።
ጽሑፉ አሁንም እንዲህ አይነት ጥያቄዎችን
የሚያነሱ አካላት መኖራቸውን አትቶ የኢትዮጵያ
ፖለቲካ ከለሩ እስላማዊ እስካልሆነ ድረስ የግብፅ ፍላጎት
ሊሳካ አይችልም ይላል። የተለያዩ ቅንጥብጣቢዎችን
ገጣጥመን ስንመለከት ግብፅ ሃይማኖትን መሰረት አድርጋ
ኢትዮጵያን የማተራመስ እቅድ እንዳላት እንረዳለን። በጣም የተቀናጀና የተናበበ ነገር እንዳለም የሚያሳዩ ነገሮች
አሉ።
ሌላው የውጭ ተራድኦ ድርጅቶች ይዘው የሚመጡት
ተልዕኮ ነው። ከሌሎች አገራት ተሞክሮ ስናይ በእነዚህ
ድርጅቶች የሚደረገው ድጋፍ ሰዎችን በተለይም
ወጣቶችን በገንዘብ እያማለሉ የራሳቸውን ፍላጎት
ለማሳካት ሲጠቀሙበት ነው። መንግሥት ይህን የሚገታ
የህግ አሠራር ቢኖረው ችግሩን ማቅለል ይቻላል ብሏል።
ጋዜጠኛ እስሌማን ወጣቱ ምንም አይነት ጥያቄ
ቢኖርበት መፍታት ያለበት በሀገር ውስጥ አካሄዶች እንጂ የውጭ ኃይሎች በቀየሱለት መንገድ ሊሆን እንደማይገባ ይገልጻል።
መንግሥትም የውይይትና የምክክር መድረኮችን እያዘጋጀ
አስቀድሞ ችግሮችን መፍታት እንዳለበት ይጠቁሟል።

▪️ጥንቅር በጋዜጠኛ እያሱ መሰለ – አዲስ ዘመን

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories