Esleman Abay የዓባይ፡ልጅ
በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በኩል የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ሆነው የተሰየሙት የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ጀነራል ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ የኢትዮጵያን የውስጥ ጦርነት ለማሸማገል የሚደረገውን ሂደት እንደሚመሩ ተገልጿል።
ይሁንና የኦባሳንጆ የማደራደር ውጤታማነት የተለያዩ ጥያቄዎች እየተሰነዘሩበት ሲሆን
ቀደም ሲል የነበሩ ሀሳቦች የጀነራሉ ሽምግልና ነፃ አለመሆኑና በተለይም የምዕራባዊያንን ተልዕኮ ከመፈፀም ያልዘለለና ኢትዮጵያን ሊጎዳ ይችላል የሚል ነበር። ከቀናት ወዲህ ደግሞ የህወሃት ደጋፊ ፀሀፍት አፍሪካ ህብረትም ሆነ ኦባሳንጆ ለፈደራሉ መንግስት የሚያደሉ ይሆናል ማለት ጀምረዋል።
ኦባሳንጆ ከ40 አመታት በፊት የሶማሊያን ወረራ ተከትሎ የተከሰተውን ውጥረት ለመሸምገል የነበራቸው ተሳትፎ ሲሆን ይህም ጀነራሉ የራሳቸውን የሽምግልና ታሪክ ይደግሙት ይሆናል የሚለውን ስጋት ሲገለፅ ነበር።
የቀድሞው የናይጀሪያ ኘሬዝዳንት በ1970 በአፍሪካ አንድነት ድርጅት የኢትዮሶማሊያ ሽምግልና ኮሚሽን ሰብሳቢ ሆነው ከወራሪ አገር ጋር ድርድር እንዲደረግ ከጀርባ ግፊት ያደረገችውን አሜሪካና የወቅቱ ኘሬዚዳንት ጂሚ ካርተርን የቤት ስራ ለማስፈፀም የሄዱበት ርቀት የሚታወስ ነው።
ሌ.ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ጥያቄውን ውድቅ ያደረጉ ሲሆን “የኢትዮጵያ ግዛት በሶማሊያ እጅ እያለ ከሶማሊያ ጋር ቁጭ ብሎ መነጋገር የማይታሰብ ስለመሆኑ የሚታወቅ ነው።
የኢትዮ ሶማሊያ የወቅቱ ችግሬ በኢትዮጵያ ሰራዊት የሉዓላዊነት ማስከበር ስኬታማ ዘመቻ የተደመደመ ሲሆን በቅርቡ የታተመው የብርሀኑ ባይህ መጽሀፍ የወቅቱ የአሜኢካን የሽምግልና ጉትጎታ ፀረ ኢትዮጵያ መሆኑን አስፍረዋል
“…አሁንም ካርተር ይኽንን የመሰለ መልዕክት የላከው ስለሰላም ወይም ስለኢትዮጵያ መወረር ተጨንቆ ሳይሆን ሶማሊያን ከውርደትና ከጉዳት ለማዳን እንደነበር ግልጽ ነው። በአንጻሩም ከኢትዮጵያ ደግሞ ድላችንን በመንጠቅ በሞራልም ብቻ እንኳን ቢሆን ለመጉዳት ነበር”
(ያልታሰበው የሕይወቴ ፈታኝ ጉዞ፤ ሌ/ኮ ብርሀኑ ባይህ፣510)
በሌላ በኩል ኦባሳንጆ ሽምግልናውን መምራታቸው የህወሃትን ጥቅም ይጎዳል ከሚሉት መካከል ዶክተር ሙሉጌታ ገብረ ህይወት አንዱ ናቸው። ዶክተር ሙሉጌታ በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናቶች ያደረጉ ሲሆኑ በመሰል ሚና ከአፍሪካ ህብረት ኢጋድና መሰል ተቋማት ጋር የተሳተፉባቸው ስራዎች ስለመኖራቸው ተፅፏል።
ከአመት በፊት የህወሃትን ትጥቅ ትግል በይፋ መቀላቀላቸው ይታወቃል። ከሰሞኑ ኦባሳንጆ ለህወሃት ስጋት ናቸው በማለት ፅሁፍ አቅርቧል። የዶክተር ሙሉጌታን ፅሁፍ የህወሃት ደጋፊ በመሆን ፀረ ኢትዮጵያ መረጃዎች በማሰራጨት የሚታወቁት እነ ረሺድ አብዲ እና መሰሎቹ እየተቀባበሉ ሲያሰራጩት ነው የሚገኘው።
ዶክተር ሙሉጌታ ነጥብ አፍሪካ ህብረት በትግራይ ስለተከሰተው ጦርነት ምንም ሳይል መቆየቱን ያጣቅሳሉ። ህብረቱ የኢፌድሪ መከላከያ ሰብአዊ የመብት ጥሰት እንደፈፀመ አድርገው ከተከናወኑ የህወሃት ዲጂታል ዘመቻዎቾ ጋር ተመሳሳይ ነው አቋማቸው። በዚህም ህብረቱ የኢትዮጵያን መከላከያ አላወገዘም በሚል ነው ገለልተኝነቱን ለመጠራጠር እንደ ምክንያት ያስቀመጡት።
ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የድርድር ቅድመ ሁኔታዎች መካከል ተደራዳሪዎቹ አደራዳሪውን አካል የተቀበሉት መሆን አለበት የሚለውንም አስፍረዋል።
ፀሀፊው በኢትዮጵያው አገራዊ ምርጫ ውስጥ የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድንን የመሩት ኦባሳንጆ በድህረ ምርጫ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ሂደቱ መርሆችን የተከተለ ነበር ሲሉ የህብረቱን አቋም ማረጋገጣቸው ያስታውሳሉ። ቀጥሎ አፍሪካ ህብረት ድርድሩን እንዲመራ የመሆኑን መረጃ ተከትሎ ህወሃት የህብረቱ ገለልተኝነት አያሳምነኝም ስለማለቱ “ደብረፅዮን ያወጣው መግለጫ” ነው በተባለ ደብዳቤ ተጠቅሷል ሱሉም አስፍረዋል።
ህወሃት ለፌደራል መንግስቱ እውቅና ለመስጠት አሻፈረኝ ያለባቸው እና ራሱን እንደ ሉአላዊ መንግስት የቆጠረባቸው የተለያዩ መግለጫዎቹ (የፌደራሉ መንግስት ህወሃትን እንዳንግሰት የማይቀበልበት ስልጣን እንደተጠበቀ በመሆኑ) በተግዳሮትነት የተጠቀሰ ሆኗል።
በሌላ በኩል ጠቅላይ ምኒስትር አብይ በአንድ ወቅት ከትግራይ የተወሰኑ አካላት ጋር ብቻ ለመምከር ፈቃደኛ ስለመሆናቸው የመግለፃቸው ጉዳይ በፀሀፊው ተወስቷል። ምዕራባዊያኑ በውስጥ ጉዳያችንና በሉዓላዊነታችን ጣልቃ መግባታቸውን ጠ.ሚ አብይ ደጋግመው ስለመግለፃቸው የሚጠቅሱት የህወሃት ታጋዩ ባለሙያ በኦባሳንጆ አሊያም በአፍሪካ ህብረት እውቅና የተሰጠው አዲሱ የኢትዮጵያ መንግስት ከመረጣቸው ተደራዳሪ አካላት ጋር አንዲሆን የገለፀውን አቋሙን ጀነራሉ የሚቀበልበት ሁኔታ ይኖራል ይላሉ። ተደራዳሪ የሆነ አካል ሌላኛውን ተደራዳሪ መምረጥና መወሰን ከመርህ ይወጣል ሲሉ ታዝበናል።
Esleman Abay የዓባይ፡ልጅ
ትዊተር eslemanabayy
በሙሉጌታ ገብረህይወትPHD፣ የቀረውን ፅሑፍ…https://eslemanabay.com/?p=2268