በዩክሬይኑ ጦርነት; የምዕራባዊያን የአለም አለቅነት ማክተሙ እና የቻይና ልዕለ ኃያልነት ጅማሮ – ቶኒ ብሊዬር

አሜሪካ እና አውሮፓ ትብብራቸው ሳይላላ እንዲቀጥል ለመምከር ለንደን፣ ዲችሌይ ፓርክ በተካሄደ መድረክ ላይ “የዩክሬን ቀውስ ለምዕራባውያን ፖለቲከኞች ምን የአመራር ትምህርት ይሰጣል?” በሚል ርእስ የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ምኒስተር ቶኒ ብሌር
ባደረጉት ንግግራቸው የምእራባዊያኑ ሃያልነት ማክተሙን ገልፀው ከዚህ ነባራዊ እውነታ ጋር የታረቀ የውጭ ፖሊሲ በአስቸኳይ ተግባራዊ ማድረግ አለብን ብለዋል።

አንጋፋው ፖለቲከኛ ቶኒ ብሌር “Blair Institute” የተሰኘ ፋውንዴሽናቸውን ወክለው ባደረጉት ንግግራቸው የአለም ፖለቲካ ድሮ እና ዘንድሮ ፍፁም ለዬቅል ናቸው ብለዋል። “ቀደም ባሉት አስርት አመታት በአውሮፓና አሜሪካ ሀገራዊ ብልፅግና ላይ የተመሰረተ መንግሰት ተመስርቶ የዜጎች ኑሮ ተሻሻለ፤ ሶቬት ህብረት ፈራረሰች፤ ምእራባዊያን ጠንካሮች ሆኑ። በ2022 ግን ነገሮች በተቃራኒው ናቸው። የዜጎች የኑሮ ደረጃ መሻሻል ካቆመ ቆዬ፤ ሀገራዊ የጤና እና በዜጎች የኑሮ ዋስትና ላይ የሚደረገው ድጎማ እያሽቆለቆለ ይገኛል። ይህን በብሪታኒያ በተለየ ብንመለከተው ሀገሪቱ ለዜጎች የምትመድበው ድጎማ እየወረደ በተቃራኒው ከዜጎች ልዩ ልዩ የታክስ ተቆራጮቿን እያሳደገች ለመቀጠል ተገድዳለች። ኮቪድ እና የዩክሬይኑን ጦርነት ተከትሎ ችግሩን የከፋ አድርጎታል።”

“በቅርብ ዘመናት እንደታዘብነው አሜሪካ መራሽ የሆነው የአለም ፖለቲካ ለምእራባዊያን ከአትራፊነት ይልቅ አክሳሪነቱ ሲያመን ቆይቷል። ብዙ ድካምና በጀት የወጣባቸው ጥረቶች ትርፋቸው ኢምንት ብቻ ሲሆን ተመልክተናል። በዚህ ላይ የቴክኖሎጂ አብዮቱ ነገሮችን ከቁጥጥር ውጭ አድርጎታል።
ይህ ጊዜ በአለም ፖለቲካዊ ሽግሽግ ውስጥ የክፍለዘመኑ ታላቅ ምእራፍ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።
በዚህ ጊዜ ግን ምዕራባውያን ወደ ላይ እንዳልሆኑ ግልጽ ነው።

አለም ወደ ኒውክሌር ጦርነት ልትገባ ነው በማለት ብዙዎችን ስጋት ላይ ጥሎ የነበረው የ 1962ቱ የኩባ ሚሳኤል ቀውስ ወዲህ ሩሲያ በዩክሬን የፈፀመችው ወረራ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት ሲሆን በሩሲያና በምዕራቡ ዓለም መካከልም ከፍተኛ የሆነውን ቀውስ ያስከተለ ነው።
ፕሬዝዳንት ፑቲንን ከምእራቡ አለም የሩስያን ኢኮኖሚም በማዕቀብ ለማግለል የተደረገው የኢኮኖሚ ጦርነት ሞስኮ አጋርነቷን ወደ ቻይና እና ህንድ እንድታዞርና በዚያም አዳዲስ ሃያላን ይፈጠሩ ዘንድ እንድታማትር አድርጓታል።
የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ፑቲንን መደገፋቸውን ቀጥለዋል። በምዕራቡ ዓለም የሚጣሉትን ማእቀቦችንም በተደጋጋሚ ተችተዋል። ፑቲን ከቻይና ጋር “ስትራቴጂካዊ አጋርነት” የሚሉትን እውነታ በተጨባጭ ፈጥረዋል።
ቻይና እ.ኤ.አ. 1979 ላይ የነበራት ኢኮኖሚ ከጣሊያን ያንስ ነበር። አሁን ላይ ግን በዓለም ሁለተኛዋ ባለ ታላቅ ኢኮኖሚ ሆነች። ኢኮኖሚው በጥቂት አመታት ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስን እንደሚረከብ የተተነበየ ሲሆን የአለማችን ሃያልነት ቢያንስ ባለሁለትዮሽ ምናልባትም ባለብዙ ሃያላን (መልቲ-ፖላር) ትሆናለች” ብለዋል። የክፍለ ዘመኑ ታላቅ ጂኦ-ፖለቲካዊ ለውጥና ኃያልነት የሚመጣውም ከቻይና ነው። የቻይና ልዕለ ኃያል መሆን ተፈጥሯዊ እና ትክክለኛም ነው። ተባባሪዎቿ ሩሲያ ቱርክ ኢራንና ሌሎችም መሆናቸውን ማጤን ይኖርብናል። የህንድን ጉዳይም ከውስጣዊም ውጫዊ ጉዳያችን አንፃር ትልቅ ዋጋ ሰጥተን ልንመለከታት የሚገባት ሀገር ሆናለች።

ምዕራባውያን ቻይናን በወታደራዊ ኃይል እንድትረከብ መፍቀድ የለባቸውም ብለዋል። “የመከላከያ ወጪን ማሳደግ እና ወታደራዊ የበላይነትን ማስጠበቅ አለብን” ብለዋል ብሌየር። ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ “ለማንኛውም ክስተት ወይም የግጭት አይነት እና በሁሉም አካባቢዎች ለማስተናገድ ከበቂ በላይ መሆን አለባቸው.”

በዩክሬይን የተከሰተው ቀውስ ህገወጥ ወረራን ተከትሎ የመጣ ቢሆንም ውጤቱ ግን ወራሪውን ቅቡላዊ የማድረግ እሳቤ የፈጠረ ነው የሆነው።
በዩክሬይ ጦርነት ዙሪያ በተለይም ጦርነቱ ሲጀመር እኔ እራሴ ለዩክሬይን የሚደረገው ወታደራዊና ሌሎች ድጋፎች ውጤት ያመጣሉ ብዬ ስሞግት ነበር። ይሁንና አሁን ላይ በተጨባጭ የታየው ግን የዩክሬይን ማለት ከዩክሬይን ባለፈ አጠቃላዩን የምእራባዊያን የውጪ ፖሊሲ ጉዳይ ነፀብራቅ ተደርጋ ልትገለፅ ትችላለች።
ቻይና ኃያል ሀገር ናት። ይህ ምንም ጥርጥር የለውም። ሩሲያም እጅግ ሃያል ወታደራዊ አቅም ያሳካች ሀገር ሆናለች።
እነዚህ ነገሮች የክፍለዘመኑን የአለም አሰላለፍ ለውጥ እንዲመጣ አድርገውታል። ለዚህ መዘጋጀት አለብን።
ለምሳሌ ቻይና ታይዋንን ለመጠቅለል ከፍተኛ ዝግጅትና ፍላጎት እያሳየች ነው። ቻይና ታይዋንን በጉልበት ትጠቀልላለች በሚለው ላይ ብቻ ማተኮር የለብንም። ምክንያሁም ቤይጂንግ ብቻዋን አይደለችም። በርካታ አጋሮች አሏት።
በዚህም ምክንያት የቻይናን ሃይልነት በክፍት ልቦና ተቀብለን የትብብሩ አካል ለመሆን መዘጋጀት አለብን። ይህን ባናደርግ እንኳን ቻይና በራሷ አለማቀፍ ኃያልነቷን መምራቷ አይቀሬ ብቻ ሳይሆን የሚመጣውን ሁሉ ተቋቁማ መዝለቅ የምትችልበት አቅምና ነባራዊ ሁኔታዎች እየታዩ ናቸው። ይህ ምን ማለት እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባል። በሃይፐርሶኒክ ሚሳይል የገነባችው ከአለም ቁጥር አንድ አቅም የሚታወቅ ነው፤ የሳይበር ደህንነት የዘመናችን የመከላከያ አቅም ሆኗል። በዚህም የቤይጂንግን አቅም የተመለከትነው ነው።

አቶ ብሌር በዚህ ታሪካዊ ንግግራቸው አለምአቀፉ የኃይሎች አሰላለፍ መለወጡን፣ የምእራባዊያን ፍፁማዊ የበላይነት ዳግም ተመልሶ ላይመጣ በቻይናዊያን መናድ መጀመሩን፣ መንግስታትን የሚያፀናው ተጨባጭ ውጤት የሚያመጣ አሰራር እንጂ ዲሞክራሲን የሚያቀነቅነው የምእራባዊያን አጀንዳ የመጭው ዘመን ትኩረት አይሆንም።”

“በመጨረሻ የምናገረው ቢኖር አሁን የሚታዩ አለማቀፍ ተጨባጮችን ያገናዘብ የለውጥ ርምጃ መውሰድ ይኖርብናል የሚል ነው። ምናብ ምኞትና መሰል አካሄዶችን አስወግደን በምክንያት ማመን መጀመር አለብን። ለአዲሱ አለም አቀፍ ፖለቲካዊ ተጨባጭ ፖሊሲና ስትራቴጂ መንደፍ አለብን፤ የቤት ስራችንም አስቸኳይ ተግባር የሚጠይቀን ነው።
▪️የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ምኒስተር ቶኒ ብሌር
Blair Institute

Esleman Abay

የዓባይልጅ #eslemanabay

📽️ 👇
https://youtu.be/uGQ0zlH1n5M

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories