በኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ግንባታ፣ በኢንቨስትመንት እና ንግድ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ጋራ ስለመስራት
ይህ የተገለጸው በጀርመን የኢትዮጵያ ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልእክተኛ ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን ከዱዝልዶልፍና ሙኒክ አከባቢ የመጡትን ባለሀብቶች በጽሕፈት ቤታቸዉ ተቀብለዉ ባናገሩበት ወቅት ነው።
ባለሀብቶቹን ያስተባበሩት ትዉልደ ኢትዮጵያዊት ወይዘሮ አስቴር ሮዝ ማሞ የGlobal Ethiopian Women Alliance ም/ፕሬዘዳንት እና የCoffee Alliance ድርጅት ባለቤት ሲሆኑ፣ እሳቸዉም እየተሳተፉበት በሚገኙት የትምህርት ቤቶች ግንባታ እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸዉ የInitiative Handwork for Africa እና Garenfeld Strategy Consulting ፕሬዚዳንት Mr.Friedrich Garenfeld ፣ የሙኒክ ዳይመንድ ክለብ አባል Mr. Georg Schmidt እና የ enlop GmbH Managing Director Mr. Eugen Eichmann ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን በተወያዩበት ወቅት ነው ።
በውይይቱ የሁለቱን ሀገራት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ዕድሎች ለማስፋፋት የኢትዮጵያ የንግድ ምክር ቤት/Chamber of Commerce / ቢሮ እንዲከፈት ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ባለሀብቶቹ የገለጹ ሲሆን፣ ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን በኢንቨስትመንት እና በንግድ ለመሳተፍ ላሳዩት ፍላጐት አመስግነው በኢትዮጵያ ስላው ምቹ ሁኔታ በማብራራት በኢትዮጵያ እና በጀርመን
መካከል በየዘርፉ ያለው
ግንኙነት እንዲጠናከርና
እንዲጉለብት፣ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በርሊን እስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመግንባት እና በሌሎችም ዘርፎች የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍና አብሮ ለመስራት የተቋማቱ ሓላፊዎችና ባለሀብቶቹ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
መረጃው በጀርመን በርሊን የኢትዮጵያ ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ ነው። https://www.facebook.com/901383599940260/posts/4994117794000133/