
⏩ ዓለም በዝናብ እጥረት ትመታለች፤ የአማኞች አገር ኢትዮጵያ ዝናቧ ይበዛላታል። አባይን በእጇ ማድረግ ወሳኝ ነው ⏪
በግድቡ ድርድር ላይ የውሃ ድርሻ ክፍፍልን የተመለከተ ፊርማ ዋሽንግተን ላይ ፈርመን ቢሆን ኖሮ ወደፊት የሚገጥመንን ፈተና ከባድ የቀጣዩ ትውልዳችን ወቀሳም በኛ ላይ ምህረት የለሽ የሚያደርግ ነበር። ምክንያቱም የውሃ ዕጥረት ቀጣዩ የዓለም ጭንቀት ነውና።
መጪው ዘመን የሚያስተናግደው የአየር ንብረት ለውጥ ድፍን አለምን ለውሃ እጥረት የሚዳርግ ነው። በበርካታ አገራት ዝናብ ዜሮ ድረስ የሚጠፋባቸው አመታትን ማስተናገድ የሚጠበቅ ስጋት ነው። በከፍተኛ መጠን የዝናብ መጠን መቀነስም አብዛኞቹን የሚጋፈጥ ይሆናል። የዝናቡ ችግር የሚፈጥረው የአፈር ርጥበት ማጣትና ምርታማነት መጥፋት አይቀሬው ስጋት ነው።
እኛ የምንገኝበት የናይል ላይኛው ተፋሰስ ተራራማ አካባቢ ግን በሚገርም ሁኔታ ከፍተኛ ዝናብ የሚያገኝ ይሆናል። ተፋሰሱ የዓለማችን ረጅሙ ወንዝ ናይልን ይዟል። ወንዙ 11 የአፍሪካ አገራትን አቋርጦ ያልፋል። 10 በመቶውን የአፍሪካ ምድር የሚሸፍን ተፋሰስ አለው። በኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን እና ግብፅ የሚኖሩ 250 ሚሊዮን ሰዎች ህይወት የአባይ ወንዝ ጥገኛ ነው፡፡
የአየር ንብረት ትንበያዎች እንደሚጠቁሙት እስከያዝነው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ድረስ በላይኛው የናይል ተፋሰስ አካባቢ የሚኖረው የዝናብ መጠን እስከ 20% ሊጨምር ይችላል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ አስከፊ ሞቃታማ እና ደረቅ አመታት spells በምንኖርበት ላይኛው የናይል ተፋሰስ በተደጋጋሚ እንደሚከሰቱ ነው የተተነበየው፡፡
በክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይም በእጥፍ ከሚጨምረው የህዝብ ቁጥር ጋር የሞቃታማና ደረቃማ አመታት ድግግሞሽ በቀጠናው በአንድነት ይከሰታሉ። በጊዜው የዝናብ መጠኑ የሚጨምር ቢሆንም በወቅቱ የሚኖረውን የዝብ ቁጥር ለማዳረስ ከፍተኛ እጥረት ይገጥመዋል። ይህ ክስተት በቀጠናው የውሃ ውጥረትን ይፈጥራል።
አሁን ላይ በአካባቢው ባለው የዝናብ ወቅታዊ መዋዠቅና የውሃ ሀብት ክፍፍሉ ፍትሃዊ ባለመሆኑ ምክንያት ከተፋሰሱ ነዋሪዎች 10 በመቶው በከባድ የውሃ እጥረት ውስጥ ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2040 የውሃ እጥረት የሚያጋጠማቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 35 % የሰደርሳል፡፡ ያ ማለት፣ የዕለት ተዕለት ኑሯቸውን ለመምራት በቂ ውሃ የማያገኙ ሰዎች ቁጥር ከ 80 ሚሊዮን በላይ ያደርሳል፡፡
የሞቃትና ደረቅ አመታት መከሰት ሰብሎችን ይገድላል፣ የውሃ ሃይል ማመንጫዎችን አቅም ያዳክማል፣ ለሰውና ለኢንዱስትሪዎች የሚቀርበውን የውሃ መጠን ያሳንሳል። በውጤቱም በቀጠናው የውሃ ሀብት ድርሻ የሚፈጥረው ውጥረት አደገኛ እንዲሆን የሠደርገዋል፡፡ ችግሩ በ 2040 በአካባቢው ከሚኖረው ህዝብ 45 በመቶ ማለትም ከ 110 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የናይል ተፋሰስን ተጠግቶ መኖርና የውሃ እጥረቱን ለመቅረፍ የህልውና ትግል ለማድረግ ይገደዳል፡፡
ደረቅ አመታት ባይከሰቱም እንኳን የህዝብ ቁጥሩ መጨመር ብቻውን ለላይኛው ተፋሰስ የውሃ እጥረት መከሰት በቂ ምክንያት ይሆናል፡፡ በሞቃት-ደረቅ ዓመታት ሳቢያም ባካባቢው ከ 5% እስከ 15% የሚሆን ተጨማሪ ህዝብ ለውሃ እጥረት ይዳረጋል። የእነዚህ ችግሮች መባባስ ቀድሞውኑም ውስብስብና በውጥረት የተሞላውን የቀጠናው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፈተና የተባባሰ ያደርገዋል፡፡
በተለይ ደግሞ የሞቃት-ደረቅ ዓመታት ድግግሞሽ አደጋ ይጋርጣል።
የዘርፉ ምሁራን በተፋሰሱ ከ 1961 እስከ 2005 ጊዜ መካከል የነበረውን የዝናብና ሙቀት መጠን ዳታዎች በመተንተን መጪውን ሁኔታ ለመተንበይ አውለውታል፡፡
ግኝታቸው የሚያሳየውም ባለፉት አራት አሥርት ዓመታት በላይኛው ተፋሰስ አካባቢ ሞቃታማ-ደረቅ ዓመታት በየ 20 ዓመቱ አንድ ጊዜ ተከስቷል፡፡ ድግግሞሹ ጭማሪ ወደፊት ባለው ጊዜ በዬ 6 እና 10 ዓመት አንድ ጊዜ ሊከሰት እንደሚችል ተተንብይዋል።ይህም በክልሉ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች የተለመደ ተሞክሮ ነው ፡፡
የቀጠናው ሙቀትም ከ 2 እስከ 6 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ከፍ ይላል። ይህም እስካሁን ከተከሰቱት ሁሉ በባሰ ሁኔታ በሰዎች፣ በእንስሳትና ሰብል ላይ ከፍተኛ ችግር ያስከትላል፡፡
ለተፋሰሱ መፃኢ የውሃ እጥረት ችግር የተለያዩ መፍትሄዎች ተቀምጠዋል። አንዱና የመጀመሪያው የተፋሰሱ አገራትን የውሃ ድርሻ ፍትሃዊ ማድረግ የሚል። በተለይም የግብፅን የቅኚ ግዛት የውሃ ድርሻ ስምምነት ማደስ የሚጠቅስ። እንግዲህ ይህ ባለበት ሁኔታ ነው ግብፅ የውሃ ድርሻዋን 41 ቢሊየን ሜ.ኪዩብ እንድንፈርምላት በትራምፕ ጫና ልትጫወትብን የነበረው። አሁናዊው አቋማችን በውሃ ሙሊት ላይ ብቻ የተገደበ መሆኑ ከጉድ አውጥቶናል።
ግብርና ዋናው የኢኮኖሚያችን በሆነባትና የአባይን ግዙፍ የውሃ አቅርቦት ይዘን መጪውን ድርቃማ ዘመን ሳይቸግረን መጋፈጥ ከዛሬው የድርድሩ ድንጋጌዎች የሚመዘዝ ነው የሚሆነው። ድርድሩ የውሃ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን አረብ አገራትን ጨምሮ በቀጠናው ባይተዋር የሚያደርገንን የጂኦ-ፖለቲካል ጨዋታ ስትዘውርብን የኖረችው ግብፅ ሌሎች ነገሮችን ትተን ዋናው መላዋ በዚሁ በውሃ አቅርቦት ላይ የተመሠረተ ቀመሯ ነው። በግድባችንና በውሃ ሃብታችን የማዘዝ ልዕልናችንን ዛሬ ላይ አስከበርን ማለት በመጪው ውሃ-አጠር ዘመን ከውሃ ብርቅየነት ጋር የሚኖረውን በረከት አገራችን እንድትቋደስ ያስችላታል። ገና ካሁኑ ወደኛ ወደኛ ማጋደል የጀመረው የአገራት ውግንንና ውሃውን መሙላት ስንጀምር ጠቅልሎ በእጃችን የሚገባ ይሆናል።
የአባይ ውሃ ባለቤትነታችንን ማረጋገጥ የምግብም፣ የሐብትም፣ የጉልበትና የሌላም የሌላም ትሩፋታችን መሠረት ነው። የሙሊቱ ድርድርም ይህንን ያገናዘበ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።
↪️
መረጃውን በ Neukom Institute እና Dartmouth ኮሌጅ
ለድህረ-ዶክትሬት ማሟያ የተሰራ ጥናትን እንዲሁም ማጠናከሪያ መረጃዎችን ከልዩ ልዩ ተቋማትና ጥናቶች አሰባስቤ ያጠናቀርኩት ነው።
⤵️
https://www.google.com/search?q=more+rain+less+water+nile&oq=more+rain+less+water+nile&aqs=chrome..69i57j33j69i60l2.8860j0j1&client=ms-android-lenovo&sourceid=chrome-mobile&ie=UTF-8