ተፈጥሮ ሀብቶች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት

ተፈጥሮ ሀብቶች በሰው ልጆች ጥረት ወይም አስተዋፆ ብቻ ያልለሙ ሀብቶችን የሚይዝ ፅንሰ ሀሳብ ነው፡፡ ፋላስፋው ጆን ሎክ ተፈጥሮ ሀብቶችን ግለሰብ ወይም ቡድን ሙሉ ባለቤትነት(unqualified ownership) መያዝ እንደሌለበት ያስቀምጣል፡፡ ይህ ማለት ግን ማንም ሰው የተለየ ጥቅም ከተፈጥሮ ሀብቱ ሊኖራው አይችልም የሚል መደምደሚያ የሚያደርስ አይደለም፡፡

ግለሰቦች ወይም ማህበረሰብ የተፈጥሮ ሀብቶች ህጋዊ አሰራሮችን በመከተል ገደብ የተጠለበት ባለቤትን መብት ሊይዙ ይችላሉ፡፡ በህግ በመመራት በሚሰጠው ፈቃድ መሰረት ከወንዞች ውሃን ወይም ሌላ የውሃ ሀብትን ባለቤት መሆን ይቻላል፡፡ የጋራ የሆነው የወንዝ ውሃ ከመንግሰት በሚሰጠው የመጠቀም ፈቃድ መሰረት ፈቃዱን ያገኛው ሰው ለተፈቀደው ውሃ መጠን ብቻ የባለቤትነት መብት ይኖራል፡፡ ወንዙን በአጠቃላይ አንድ ሰዉ ግን ባለቤት ነኝ ለማለት አይችልም።

ይህ በብዙ የአለም ሀገረት የተለመደ አሰራር ነው፡፡በእንግልዝ በውሃ አካለት ውስጥ የሚገኛው ውሃ በሀሪቱ ህዝብ ባለቤትነት የተያዘ መሆኑን ተመልክቷል፡፡ ፈረንሳይም ተመሳሳይ ይዘት ያለውን አሰራር ይከተላሉ፡፡በወንዝ የሚፈሰው ወይም ያለው ውሃ የህዝብ ሀብት ነው፡፡ ህዝብ የሚለው ፅንሰ ሀሳብ ጠቦ የሚታይ አይደለም፡፡

የሀገርቱ ሁሉም ህዝቦች ባቤትነት ኖሮት መንግስት ግን በባለአደረነት የሚጠብቀው ሀብት ይሆናል ማለት ነው፡፡ ድንባሪ ተሻጋሪ ወንዞች በተመለከቱ ባለቤትነቱ በተፋሳስ ሀገራት የሚገኙትን ህዝቦችን ሁሉን የሚያከትት ነው፡፡ ስለዚህ ነው ማንኛውም ድንባሪ ተሻጋሪ ወንዝ ፍትሃዊና ምክንታዊ አጠቃቀም መርሆን በመከተል በጥቅም ላይ እንዲውል የአለም አቀፍ ህጎች የሚደነግጉት፡፡

በታህሣሥ 15 ቀን 1987 ዓ.ም የወጣው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክረሰሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት መሬት የህዝብና የመንግስት ይዞታ መሆናቸውን ይደነግጋል፡፡ ይኸው የ1987 ህገ መንግሥት በአንቀጽ 89(5) መሬትና ሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶችን ለህዝብ ጥቅም ማዋል እንዲቻል መንግስት ሃላፊነት እንዳለበት ያረጋግጣል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ህገ መንግስቱ በአንቀጽ 92 ላይ ማንኛውም ፕሮግራም ወይም ፕሮጀክት ሲታቀድም ሆነ ሲተገበር በአካባቢ ላይ ጉዳት ወይም ጥፋት ማድረስ እንደሌለበት ያሳስባል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 (3) ላይ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት እንዲሁም በሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶች ላይ የባለቤትነት መብት ያላቸው መንግሥትና ህዝብ ብቻ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡ በዚህ መሠረት መሬት የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች፣ ህዝቦች እና የመንግስት የጋራ ንብረት የሆነና በማናቸውም ሁኔታ ሊሸጥ ወይም ሊለወጥ የማይችል ሀብት ነው ሲል ያስፍራል፡፡

በሀገራችን አሁን በሥራ ላይ ያለዉ የፌዴራል ህገመንግስት መሬትና የተፈጥሮ ሀብት የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች እንዲሁም የመንግስት ሀብት መሆኑ የደነገገ በክልሉ ዉስጥ የሚገኙ ተፈጥሮ ሀብቶችን በፌዴራል መነሰግስት በሚወጡ ህግጋት ክልሎች እንዲያስተዳድሩ የተመለከተ ሲሆን፤ ድንበር ተሸጋሪ ወይም ከአንድ ክልል በላይ የሚያቆርጡ ወንዞች ከሆኑ ደግሞ የማስተዳደር ስራዎችን ጭምር የፌዴራል መንግስት ሚና እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡ ነገር ግን፤ የትኛውም ወንዝ ዘላቂነት ጉዳይ በየደረጀ የሚገኙት የመንግስት አካላትን ሙሉ ትብብርና ቅንጅታዊ ተሳትፎን የሚፈልጉ ናቸው፡፡

የዓለም ህዝቦች እጅግ ለተወሳሰቡ የተለያየ ቀውሶች የመጋለጣቸው ሀቅ በየወቅቱ እያደገ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ፤ ፈጣን የህዝብ ቁጥር መጨመር፤ ያልተገራ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲሁም በርከታ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ክስተቶች አለምን የደህንነት ቀውስ እና ድህነት ማዕከል አድርጓታል፡፡ አንድ ሀገር በተፈጥሮ ሀብቷች የበለፀገች መሆኗ ለዜጎቹ ብልፅግና አንዱ መሰረት ነው፡፡

በርካታ የኤዥያ ሀገሮች ለፈጣን ኢኮኖሚ ዕድገት ትኩረት በመስጠት ለተፈጥሮ ሀብቶች ዘላቂነት ተገቢውን ትኩረት መንፈጋቸው፤ ዛሬ ለፈርጀ ብዙ ችግሮች አጋለጧቿል ብሎም ለኢኮኖሚያቸው ግብአት የሚሆን ጥሬ ዕቃ ለማግኘት እየተቸገሩ ነው፡፡ በተለይም የተፈጥሮ ሀብቶችን ፍትሃዊነት ባለው መልኩ ለመጠቀም የሚያስችሉ ህጋዊ አሰራሮች ያለመኖር ወይም ያሉ ህግጋት በውጤታማነት ያለመተግበር ችግር ለቀውሱ መባበስ የበኩላቸውን ሚና በመጨወት ላይ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ውስንነት የተፈጥሮ ሀብቶች ዛለቂነት በሌላው አግባብ ይበዘበዛሉ፡፡ በተደረጁ ህገወጥ ቡዱኖችም ይዘረፋሉ፡፡

የተፈጥሮ ሀብቶች መመናመንና መራቆት የኢኮኖሚውን ልማት ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ሊገታ ወይም ሊያሰናክል ይችላል፡፡ የዓለም ተፈጥሮ ሀብቶችን ዘላቂነት በሌላው ሁኔታ የተጠቀሙ ዛሬ አኮኖሚያቸውን የኢኮኖሚ እድገታቸውን በዘላቂነት ለማሳከት ተግዳሮችት ገጥሟቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የበለፀጉ ሀገራት እየጨመረ በመሄድ ላይ የሚገኛውን የጥሬ-ዕቃ ፍላጎታቸውን ለማሟላት የተለያዩ ተፈጥሮ ሀብቶችን ከጨረቃ፤ ከጥልቅ የመሬት አካል እንዲሁም ከባህር ግርጌ የማፈላለግና የማልማት ሥራዎች ላይ እየባዘኑ ናቸው፡፡ የቅኝ ግዛት እሽቅድድምም የነበረው በዋነነት ተፈጥሮ ሀብቶችን በመቀራመት እያደገ በመሄድ ላይ የነበረውን የኢንዱስትሪ ግብአት ፍላጎትን ለማሟ፨ላት ታሳቢ በማድረግ ነበረ፡፡

በተለያዩ ስልቶች የተፈጥሮ ሀብቶችን ለመቆጣጠር መቻል አገራት ለህልውናቻው ጭምር መሰረት አድርገው ይወስዱታል፡፡ ለዚህም በሀገራችን የአባይ ወንዝ ታሪክ ማያት ይቻላል፡፡ ከግርጌ ተፋሰስ ሀገረት ከሆኑት ውስጥ ግብፅ በተደጋገሚ፤ በተለይም የወንዙን ምንጭ ለመቆጣጠር የተፋሰሱ አካል የሆነውን የኢትዮጵያ ክፍሎች ለመያዝ ሙከራ አድርጋለች፡፡ በሌላ በኩል ሀገራችንን የተፈጥሮ ሀብት የሆነውን ወደብ በማሰጣት አቅሟን ለማዳከም የተደረገው ያልተቋረጣ የውጭ ሀይሎች ትልም በእኛ ዕድሜ ተሳክቶላቸዋል፡፡

ሀገራችን በብሔራዊና አለም-ዓቀፋዊ ደረጃ ፋይዳ ባላቸው ብርቅዬና ዓይነተ-ብዝሀነት ያላቸው የብዝሃ-ሕይወት ሀብቶችን የያዙ ሥርዓተ-ምህዳሮች ባለቤት ነች፡፡ ውሃ አዘል መሬት ከጠቅላላው የኢትዮጵያ የቆዳ ስፋት በግምት 1.5% ያህሉን የሚሸፍን ነው፡፡ እነዚህ የተፈጥሮ ሃብቶች ለሰውና ለእንስሳት የሚሆኑ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ምንጭ ከመሆናቸውም በተጨማሪ የውሃ ጥራትን ይጠብቃሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ውሃ አዘል መሬት ለመስኖ አገልግሎት፤ ለኢንዱስትሪ፤ ሊበሰብሱ የሚችሉ ቆሻሻዎችን ለመምጠጥ፤ ለአሣ መጠለያነት፣ ለብዝሃ ህይወት መኖሪያነት፤ ጎርፍን ለመከላከልና የከርሰ ምድር ውሃ እንዲበልፅግ በማድረግ በኩል ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡

የሀገራችን የውሃ አዘል መሬቶች በጊዜ ሂደት ተንጣፈው ለግብርና አገልግሎት፣ ለሰፈራ እና ወደ ለሌሎች የመሬት አጠቃቀሞች ተለውጠዋል ፤ በመለወጥ ላይም ናቸው፡፡ የውሃ አዘል መሬት መመናመን በአገሪቱ ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ ህልውና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያለው በመሆኑ ችግሩን ለመቀልበስ፤ ፈጣን እና የተሟላ መፍትሄ የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡ የሀገራችን ተራራማ ሥፍራዎች ለወንዞች መነሻና ምንጭ ናቸው፡፡ ነገር ግን፤ የደኖች መመንጠርና መመናመን እንዲሁም በመሬት መጎሳቆል ሳቢያ የወንዞቹ ተፋሰሶች ለከፍተኛ ጉዳት ተዳርገዋል፡፡

ኢትየጵያ በውሃ ሀብት በአንፃራዊነት የበለፀገች መሆኗ ይነገራል፡፡ ነገር ግን ይህ ሀብት በሀገርቱ በሁሉም ክፍሎች በተመጣጠነ ሁኔታ የሚገኝ አይደለም፡፡ አንደንድ አከባቢዎች በአንፃራዊነት ብዙ የውሀ ሀብት ሲኖር በሌሎች አካባቢ ደግሞ አጅግ ከፍተኛ የሆነ እጥረት የሚታይበት ነው፡፡ በተጨማሪ በፍጥነት እየደገ በመሄድ ላይ ካለው የህዝብ ቁጥር፤ የኢንዲስትሪ መስፋፋት፤ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተዳምሮ ተከታተይ የሆነ ድርቅ እና ሌሎች ተዛማጅ ችግሮች ምክንያት፤ የውሃ እጥረት ሀገራችንን ከሚያሰጉ የደህንነት ስጋቶች ውስጥ የሚመደብ ነው፡፡

በሀገራችን አብዘኛው ህዝብ የንፁህ ውሃ ተደራሺነት የተረጋገጠ አይደለም፡፡ እርሻዎቻችንም ቢሆኑ በአብዘኛው በዝናብ ውሃ ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ አሁን የሚታያው ኋላቀር ግብርና አሰራር ስንቀይር የውሃ ፍላጎታችን እየደገ መሄዱ አይቀርም፡፡ ይህ ደግሞ ለግርጌ ሀገረት የእለት ተዕለት ስጋታቸው ነው፡፡ ሀገራችን ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን ለመጠቀም አቅም እያሳደገች መሄድ ማለት እንደግብፅ ያሉ ሀገረት በአሁኑ ጊዜ ያለገደብ የሚጠቀሙት ውሃ መጠን መቀነሱ አይቀሬ ይሆናል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ግብፅ ሀገራችን የህዳሴ ግድብ ሙሌት ሳይሆን ይባልጥ እንቅልፍ የሚነሳት በቀጣይ ሀገርቱ ሊትወስድ የሚትችላውን የልማት እንቅስቃሴን ለመቆጣጣር የሚያስችል ልጓም ለማበጀት ይህንን አጋጣሚ በተቻለ መጠን የመጠቀም ጉዳይ ነው፡፡ ከሱደን ድንበር እጅግ በቀረበ ርቀት ላይ የሚገነበው ግድባችን፤ ለሀገራችን ለቀጣይ የውሃ ልማት እንቅስቃሴ እንደ ጅምር እንጂ በምንም አይነት የመጨራሻ የሚሆን አይደለም፡፡

ከሀገራችን ጋር ምንም አይነት ገዥ ውል ሳይኖር በቅኝ ግዛት ዘመን የተደረጉት ስምምነቶች በአሁኑ ጊዜ ግብፅ ይገባኛል ለምትለው 55 ቢሊየን ኪዩብክ ሜትር ኢስኩየር ውሃ በየአመቱ ለማግኛት የሚያስችለት አይሆንም፡፡ ከአፄ ሚሊኒክ ጋር በ1902 ዓ.ም የተደረገው ስምምነትም ውሃን ሙሉ ለሙሉ ላለማስቀረት የተገባ ውል እንጅ በኢትዮጵያ ድንባር ውስጥ ውሃን ላለመጠቀም የተገባ ስምምነት አይደለም፡፡

በመሆኑም ስምምነቱ የግብዕን የተዛበ ፍላጎት፤ ውሃን በብቸኝነት ለመጠቀም ያለትን ህልም የሚያስቀጥል አይሆንም፡፡ በ1929 እ.አ.አ በግብፅ እና በአንግልዝ መካከል የተደረገው የውሃ ክፍፍል ስምምነት ሀገራችን አልተሳተፋችም፡፡ በ1959 እ.አ.አ ግብፅ እና ሱዳን የናይል ወሃ ሀብትን በመካከላቸው ያደገ ስምምነት በመፈራረም የተቀረመቱበት እንጅ የተፋሳስ ሀገራትን ኢትዮጵያን ጨምሮ ያሳተፋ አልነበራም፡፡ እነኝ የውሃ ስምምነቶች የውሃ ባለቤት የሆኑ ሀገራትን ፍትሃዊ የውሃ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ የተሸረቡ አለም አገቀፍ ልማድን የሚጋፉ ናቸው፡፡

በተለይም ግብፅ ዉሎቹን ታሪካዊ መብት ወይም የተፈጥሮ መብቶች ያጎናፀፉ በማድረግ ሌሎች የተፋሳስ ሀገራት ውሃን በስምምነቱ ፈቃድ ሳይሰጡ ቢሆን እንደሰጡ ለማስመሰል ሲትደክር መየት የተለመደ ነው፡፡ በውል ህጎች ውል የሚገዘው ተዋወይ ወገኖችን እንጅ በውል ስምምነቱ ፈቃድን ያልሠጠውን ጭምር አይደለም፡፡ በተለምዶ ውሉን ያልፈረመ ሶስተኛ ወገን የውል ግዴታውን ለመሸከም የሚገደድበት ሁኔታ እምብዘም ነው፡፡

በ 2015 እ.አ.አ በግብፅ፤ ኢትየጵያ እና ሱዳን መካከል የተፈረመው ታላቁን የህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል የተመለከተው ሰነድ በራሱ ስምምነት ተደርጎ የሚታይ አይደለም፡፡ ይልቁንም ሰነዱ መንግስታት ድርድሩ የሚመረበት አግባብ ላይ ፈላጎታቸውን የገለጡበት ሰነድ ነው፡፡ ይህ ዲክላሬሽን ኦፍ ፕርስፕልስ ሰነድ እንደ አስገደጅ ውል ለማሰመሰል በግብፅ በኩል የሚነሰው ክርክር አሁንም ውሃ የሚቋጥር አሳመኝ ሀሳብ ሆኖ የሚወሰድበት አይሆንም፡፡

የትኛውም ዓለምአቀፍ የውሃ ስምምነት ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አጠቃቀም ምክንታዊና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ጉልህ የሆነ ጉዳት በተፋሰስ አገራት ላይ ሳያደርሱ መጠቀምን የሚያበረታቱ እንጂ አንድ ሀገር እየለማ ሌላው በድህነት እንዲማቀቅ፤ እንዲሁም ኢ-ፍትሃዊ አጠቃቀምን እንዲቀጥሉ ዋስትና የሚሠጥ አይደለም፡፡ የናይል ተፋሳስ ሀገራት ያለተስማሙበት ግዴታ ግብፅ በሀገራቱ ላይ ለመጣል ያልፈነቀለችሁ ድንጋይ የለም፡፡ ኢ-ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀምን ለማስቀጠል ግብፅ አሁንም ሆነ ወደፊት ክርክሩን ትቀጥላለች፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ የተለመደውን የተፋሳስ ሀገራት አንድ ላይ ድርድር ማድረግን አትፈልግም፡፡ የመከፋፈል ስልት መጠቀምን ትመርጣለች፡፡

የውሃ ተፋሳስ ሀገራት አብዘኛዎቹ አፍርካዊያን ስለሆኑ በአፍርካ ህብረት በኩል የእሷን ኢ-ፍትሃዊ ውሳኔ የሚያስቀጥል ውሳኔ ይሰጣል ብለ አታምንም፡፡ ስለዚህ ኢ-ፍትሃዊ መፍትሄን ሊያሳኩአቸው ይችላሉ ብለ የሚታስባቸው ተቋማት ወይም ሀገራትን ዘንድ መውሰድን እንደ ብቻኛ መፍትሄ በመውሰድ መኮተንን ትቀጥላለች፡፡ ገላልተኛ ህጋዊ ውሳኔ ሰጪ አካለትም ዘንድ ጉዳዩን ለመውሰድ ድፍረት አይኖራትም፡፡

ለዚህም ነው ወደ ማንኛውም ህጋዊ ውሳኔ ለሚሰጥ አካል ጉዳዩን ከማቅረብ ይልቅ ወደ ኢ-መደበኛ የዳኝነት አካለት ግብፅ ማቅረብን እየመረጠች ያለችው፡፡ ይህ አካሄድ ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጣ አይችልም፡፡ ከአባቶቻችን ጊዜ ጀምሮ የተለመደውን የዛቻ ዘመቻን መቀጠልን ወይም በሀገራችን ውስጥ ሰላም እንዳይኖር በህዝባችን ውስጥ የመከፋፈል ሥራን አጠናክራ በመቀጠል ወደ ልማት ፊቱን እንዳያዞር ሌተ ከተቀን መስራቱን የመቀጠል ልማዶን ትቀጥል ይሆናል፡፡ ቢቻላት ደግም ሀገርቱን በመበታተን፤ የተዳከሙ እና አቅም የሌላቸውን ትንንሽ አገረት እንዲፈጠሩ መስራትን መቀጠሏ አይቀርም ፡፡ ይህንን አይነት ሴራ ኢትዮጵያን ሁላችን ለማክሸፍ የሚያስችል ሥራ አጠናክረን መስራት ይጠበቅብናል።

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories