ታላቁ ሰው ሠራሽ ወንዝ ይባላል። የዓለማችን ትልቁ የመስኖ ፕሮጀክት ነው፡፡ የሊቢያን የውሃ ፍላጎት 70 በመቶ ያሟላል፡፡
በቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ የተጀመረው ፕሮጀክቱ የዓለማችንን ትልቅ ባለ 2,820 ኪ.ሜ ርዝመት የቧምቧ መስመር ያለው ነው። ሃ ከ 1,300 በላይ ጉድጓዶች አሉት። አብዛኞቹም ከ 500 ሜትር በላይ ጥልቀት ያላቸው ናቸው። በየቀኑም ከ 6 500,000 ሜትር ኪዩብ ንፁህ ውሃን ለትሪፖሊ፣ ቤንጋዚ፣ ሲርት እና ለሌላ ከተሞች ያቀርባል።
የቀድሞው የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋጋፊ “የዓለማችን ስምንተኛ ድንቃ-ድንቅ ስራ” በማለትም ገልፀውታል
እ.ኤ.አ. በ 1953 በደቡብ ሊቢያ ዘይት ለመፈለግ የተደረጉት ጥረቶች ናቸው ይህን የውሃ ሀብት መኖሩን ድንገት ያሳዩት፡፡ ታላቁ ታላቁ ሰው ሠራሽ ወንዝ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ. በ 1960 ዎቹ መጨረሻ የተፀነሰ ሲሆን ፕሮጀክቱ መሰራት የጀመረው በ 1984 ነው፡፡ የፕሮጀክቱ ግንባታ በአምስት ምዕራፎች የተከፈለ ነው፡፡ የመጀመሪያው ምዕራፍ 85 ሚሊዮን ሜትር ቁፋሮ 1991 ተመረቋል። ሁለተኛው 2004 ተመረቋል።
የፕሮጀክቱ ወጪ ከ 25 ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው። ሊቢያ ያለ ማንም ድጋፍ ዓለም ባንክንም ሳትጠብቅ በጋዳፊ በጀት ነው የገነባችው።
በሊቢያ ጦርነት ወቅት ከፕሮጀክቱ ጣቢያዎች አንዱ በ NATO የአየር ጥቃት ደርሶበታል፡፡ ኔቶ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ኔቶር የውሃ ፕሮጀክቱ የወታደሮች መደበቂያ ስለነበር መደብደባችን ተገቢ ነበር ብሏል። በጦርነቱ ምክንያትም እስከ 2019 ድረስ 479 ጉድጓዶች ተደምስሰዋል፡፡
ሊቢያ – ከግብፅ በሚያዋስናት በረሃ ላይ ድፍን ሊቢያ ውሃ የሚያቀርብ ፕሮጀክት ነው። aquifer ን መቆጣጠር ከ “አዳኝ” “ጠቃሚ” የተፈጥሮ ሀብቶችን “ለማዳን” በዋጋ ሊተመን የማይችል ነው።
ሶስት የፈረንሳይ እህትማማች ኩባንያዎች የዓለማችንን 40 በመቶ የውሃ ቢዝነስ የተቆጣጠሩ ናቸው። ፈረንሣይ በጦርነቱ ግምባር ቀደም ነበረችና የውሃ ከፕሮጀክቱ መልሶ ግምባታም ታላቅ ትርፍ ያሰላችበት ነው ተብሏል።
ጥቃቱን የሚያሳይ ቪዲዮ በቻናሌ ሊንክ አስቀምጨላችኋለሁ👇