ታላቁ አረንጔዴ ግድግዳ | The Great Green Wall

the great green wall
(first published, መጋቢት 2011)

የአለም መገናኛ ብዙሃን ስለ አፍሪካ ከሚያወሯቸው የችግር አጀንዳዎች በተቃራኒው ከተስፋ ሰጪዎች የሆነው ታላቁ አረንጔዴ ግድግዳ ነው…!!

የሰሃራ በረሃን ደቡባዊ ጠርዝ በመያዝ ከምስራቅ እስከ ምእራብ ጫፍ የሚደርስ የዛፍ ግምብ በመልማት ላይ ይገኛል። የጫካ ግምቡ ርዝመት 8 ሺህ ኪሎ ሜትር ነው። በዚህ በታላቁ አረንጔዴ ግምብ ልማት ውስጥ 20 የአፍሪካ አገራት በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ። አገራችን ኢትዮጵያም ከአገራቱ ውስጥ ናት።
አልጄሪያ፣ ቤኒን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ቻድ፣ ኬፕ-ቬርዲ፣ ጂቡቲ፣ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያ፣ ማሊ፣ ሴኔጋል፣ ናይጄሪያ፣ ኒጀር፣ ሞሪታኒያ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ጋምቢያ፣ ቱኒዚያ፣ ግብፅ የደን ግምቡን ለማልማት በጋራ ከተነሱ አገራ ውስጥ ናቸው።

ይህንን የደን ግምብ ለመስራት በ1954 እኤአ ጀምሮ ዝንባሌዎች ነበሩ። በ 2002 እኤአ በቻድ እንጄሚና በተደረግው የአካባቢ ጥበቃ ኮንፈረንስ ላይ ሃሳቡ ድጋሚ ተነሳ። በ 2005 እኤአ በአኡጋዱጉ ቡርኪናፋሶ በተደረገ ተመሳሳይ መድረክ ላይ ሃሳቡ ሙሉ ድጋፍ አገኘ። ከአልጄሪያው green dam እና ከቻይናው the gret green wall ተሞክሮም ተወስዶበታል።

ሃሳቡ ድጋፍ ተችሮት ስራው እንዲጀመር ግምባር ቀደም ቁርጠኛ ከነበሩት 11 የአፍሪካ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት።

የታላቁ አረንጎዴ ግድግዳ ልማት 2017 ላይ 15 በመቶ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቦት ነበር። የተሻለ ስራ የተከናወነውም በሴኔጋል፣ ናይጄሪያና አኢትዮጵያ መሆኑንም ዘገባው ጠቁሟል።

ከዚህ ክንውን ውስጥም በናይጄሪያ ብቻ ምድረ በዳ የነበረን 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ድርቅን በሚቌቌሙ የግራር ዛፎች እንዲሸፈኑ ማድረግ ተችሏል። “በኢትዮጵያም 15 ሚሊዮን ሄክታር ምድረበዳ በዛፎች ለምቷል”። በሴኔጋልም ከ 10 ሚሊዮን በላይ ሄክታር መሬት በተመሳሳይ ለምቷል። ዛፎቹ በተተከሉባቸው አካባቢዎች ላይ የአየር ጠባዩ አንፃራዊ መሻሻል።እየታየበት ነውም ተብሏል።

“አለማችን በርካታ ድንቅ ነገሮችን ይዛለች፣ ይህ ታላቁ አረንጔዴ ግምብ ግን ልዩ ነው፤ እያንዳንዱ የዚህ ታሪክ አካል መሆን አለበት” በማለት የአፈሪካ ህብረት ሊቀመንበሯ ዶክተር ዲላሚኒ ዙማ መናገራቸውም የሚታወስ ሲሆን “በህብረት ሰርተን የአፍሪካን መፃአኢ ጊዜ መልካም ማድረግ እንችላለን” ብለዋል።

[ እዚህ ላይ በአገራችን የለማው 15 ሚሊዮን ሄክታር የትና እንዴት? የሚለውን በተናጠል ማግኘት ባልችልም። መረጃው ያላችሁ ብታጋሩን

የታላቁ አረንጔዴ ግድግዳ እውን እንዲሆን ተባብረው ከተነሱት 20 ያህል አፍሪካዊ አገራት ጎንም ልዩ ልዩ ተቌማትም ድጋፍ የሚያደርጉ ይሆናል። ተቌማቱም የሚከተሉት ናቸው…

• African Forest Forum (AFF)
• African Union Commission (AUC)
• Association for the promotion of education and training abroad (APEFE)
• Arab Maghreb Union (UMA)
• Community of Sahel-Saharan States (CEN-SAD)
• Economic Community of West African States (ECOWAS)
• European Union (EU)
• Food and Agriculture Organization of the United Nations (FAO)
• Global Mechanism[12] of theUnited Nations Convention to Combat Desertification (GM-UNCCD)
• Intergovernmental Authority on Development in Eastern Africa (IGAD)
• MDG Center for West and Central Africa (MDG-WCA)
• Pan African Farmers Organization (PAFO)
• Panafrican Agency of the Great Green Wall (PAGGW)
• Permanent Interstate Committee for Drought Control in the Sahel (CILSS)
• Sahara and Sahel Observatory(OSS)
• Secretariat of the United Nations Convention to Combat Desertification (UNCCD-Secretariat)
• United Nations Development Programme–Drylands, Development Center (UNDP-DDC)
• United Nations Environment Programme (UNEP)
• United Nations Environment Programme–World Conservation Monitoring Center (UNEP-WCMC)
• Walloon Region of Belgium, Wallonie-Bruxelles InternationalWorld Agroforestry Centre (ICRAF)
• World Overview of Conservation Approaches and Technologies (WOCAT)The World Bank

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories