ቻይና እና ሩሲያ የኢጋድ አጋር መሆን አለባቸው”

  • የሱዳኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
  • ቤይጂንግ የቀንዱን ጂኦፖለቲካዊ ትግል ለማሸነፍ የቆረጠች ይመስላል ✍️ የዓባይ፡ልጅ

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግስታት IGAD 48ኛ የሚኒስትሮች ስብሰባን ለመሳተፍ የሀገራቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ካርቱም ገብተዋል። የህብረቱን አሁናዊ መሪ የሆነችው ሱዳን ስትሆን፤ የስብሰባው አጀንዳዎች ሰላምና ፀጥታ፣ ድርቅና በረሃማነት እንዲሁም የግጭት አፈታት ጉዳዮችን የሚመለከት ይሆናሉ ተብሏል።

በካርቱም በመጪው ረቡዕ ከሚካሄደው የሚኒስትሮቹ ጉባኤ ስብሰባ በፊት ሱና በተሰኘው የዜና ወኪል በሰጡት ኦፊሴላዊ መግለጫ ወቅት ነው ታዲያ የሱዳኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቻይና እና ሩሲያ ከኢጋድ ጋር አጋርነት መፍጠር አለባቸው ያሉት።

ሱዳናዊው ውጭ ጉዳይ ኢጋድ ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ያለውን ግንኙነት ሚዛናዊ ማድረግ አስፈላጊ ነው በማለት በአጽንኦት የተናገሩ ሲሆን “ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ኡጋንዳ የተውጣጣው የኢጋድ ህብረት ከአውሮፓ ህብረት፣ ከጀርመን፣ ዴንማርክ፣ ኔዘርላንድስ፣ አሜሪካ፣ ኖርዌይ፣ ስዊድን፣ ጣሊያን፣ ካናዳ፣ ጃፓን እና ሌሎችም ጋር አጋርነት ፈጥሯል።” ያሉ ሲሆን አክለው ሲናገሩም “28ቱ የኢጋድ አጋሮች በአብዛኛው የምዕራባውያን ሀገራት እና ሁለቱ ድርጅቶች የአውሮፓ ህብረት እና የአረብ ሊግ መሆናቸውን ከግምት በማስገባት የተናገሩት ሱዳናዊው ውጭ ጉዳይ፣ እንደ ቻይና፣ የባህረ ሰላጤ ሀገራት እና ሩሲያ ያሉ አጋሮችን ለማግኘት መጣር ያስፈልገናል” በማለት ተናግረዋል።

“ሱዳን የኢጋድ ፕሬዚዳንት ሆና በምትቆይባቸው ጊዜያት ሌሎች አጋር ሀገሮችን ለማካተት ትጥራለች። በአንድ ወገን (የምዕራባዊያን ብቻ) አጋርነት ላይ መታመን አንፈልግም። በምስራቅ እና ምዕራቡ አለም አቀፍ ግንኙነታችን ላይ ሚዛኑን የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር እንፈልጋለን” ሲሉም ነው ሱዳናዊው ውጭ ጉዳይ ጨምረው ያሳሰቡት።

myperspective

▪️በኢትዮጵያ መንግስትና ህወሃት የሰላም ሂደት ውስጥ ቻይና ቁልፍ ሚና የመጫወት ፍላጎት እንዳላት የሚታወቅ ነው። ይኸውም በቀጣናው የምዕራባዊያንን ግጭት ተኮር አካሄድ በመመከት በአዎንታዊ ትብብር መለወጥ ያስፈልጋል የሚል አላማ ያነገበ እንደነበር ነው የሚታወሰው። ለአብነትም የቻይና-ምስራቅ አፍሪካ የሰላም ኮንፈረንስ ይጠቀሳል።
በአፍሪካ ቀንድ የቻይና ኮንፈረንስ የተደረጉ መግባባቶችን ተከትሎ በኢትዮጵያ የሰላም ስምምነት አተገባበር ውስጥ ቤይጂንግ በምን መልኩ እየተሳተፈች ነው የሚለው የኔም ጥያቄ ሆኖ የቆየ ጉዳይ ነበር። ታዲያ የኢጋድ መሪዋ ሱዳን በውጭ ጉዳይ ምኒስትሯ በኩል የሰጠችው መግለጫ ታዲያ ለጥያቄው ምላሽ የሚሆን ፍንጭ የሚሰጥ ነው።
▪️ቻይና የምስራቅ አፍሪካ ግጭቶችን በልማት ተኮር መፍትሄ ለመፍታት ያለመ የመጀመሪያውን ጉባኤ በአዲስ አበባ ያደረገችው በወርሃ ሰኔ እንደነበር አይዘነጋም።

▪️ኮንፈረንሱ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ግጭት ለመቀነስ ያለመ ሲሆን ኬንያ እና ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ጅቡቲ ተሳትፈዋል። june 20-21 የተካሄደውን ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ እና ኬኒያ በጥምረት አስተናግደውታል። ይህ በቻይና አነሳሽነትና ስፖንሰርነት የተካሄደው ኮንፈረንስ በአይነቱ የመጀሪያው ሲሆን ቤይጂንግ በአፍሪካ አህጉር ያላትን ሚና ለማጠናከር በጀመረችው ሰፊ ጥረት ውስጥ ሀገሪቱ በአፍሪካ ቀንድ ልዑክ እንደምትሾም ማስታወቋን ተከትሎ ነበር ይፋ የሆነው።
በአፍሪካ ቀንድ ስትራቴጂክ መልክ ላይ ትልቅ አንድምታ የሚኖረው ጅምር ይፋ ያደረገችው በ january 11 ነበር። በአዲስ አበባ የቻይና ኤምባሲ በወቅቱ ያደረሰኝን መግለጫ ከታች በተቀመጠው መልኩ አጋርቻችሁ ነበር።

▪️ቤይጂንግ ለአፍሪካ ቀንድ ባዘጋጀችው የሰላም እና የትብብር ኢኒሼቲቭ ቀጣናው የሚገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት ግጭትን በሰላማዊ ጎዳና ሊያራምድ የሚችል መሆኑን መግለጿ ይታወሳል። ከመግለጫው ውስጥ ስናወሳ፦

▪️የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እና ትልቅ የመልማት አቅም ያለው ቢሆንም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአለምን ሃያላንን ትኩረት የሳቡ ክስተቶችን ተከትሎ ነገሮች ወደ ግጭት ሲያመሩ ተስተውሏል። ይህ ደግሞ ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ሕዝቦችን ፍላጎት የሚጻረርና ከዚህ በኋላ በዚህ ሁኔታ መቀጠል የማይገባው ነው።”
▪️በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ዘላቂ መረጋጋት፣ ሰላምና እድገት እውን እንዲሆን ቻይና ሰላማዊ የሆነ መልካም ኢኒሼቲቭ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀምራለች። በዚህም ለቀጠናው ሀገራት የጸጥታ፣ የልማት እና የአስተዳደር ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ ሶስት ዘርፎች ላይ ወሳኝ ሚናዋን መጫወት የቻይና ፈቃድ ነው። በቀዳሚነት የተቀመጠው የጸጥታ ችግሮችን የሚመለከተው ሲሆን በዚህም ቻይና፦
▪️ቀጣናዊ ውይይቶች የሚጠናከሩበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አቋሜ ነው። ይህ የሚሳካው የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትና ህዝቦች ኃያላን አገራት በቀጣናው የሚያደርጉትን የጂኦፖለቲካ ፉክክር አስወግደው በአንድነታቸው እና ራስን በማሻሻል ጎዳና ላይ በፅናት መጓዝ ይገባቸዋል ብላለች። የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የቀጣናቸውን ዕጣ ፈንታ በራሳቸው ለመወሰን በራሳቸው እጅ ውስጥ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
▪️በጉዳዮቹ ላይ ጥልቅ ውይይት ለማድረግ፣ ፖለቲካዊ መግባባት ላይ ለመድረስ እና የጋራ ተግባራትን ለማቀናጀት የቀጠናው ሀገራት የቀጣናው ሀገራት በአፍሪካ ቀንድ ሰላም ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ እንዲያደርጉ ቻይና ዝግጁ ናት። ሀገራቱ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ውይይቶችን አድርገው በሚደርሱበት የጋራ መግባባት ላይ የተመሰረተ የጋራ አቋም እንዲጨብጡም ከሂደቱ ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ ታደርጋለች። በሁለተኛነት የተቀመጠው ተግባር የቀጣናውን የልማት ፈተናዎችን መፍታት ላይ የሚያተኩራል፦
▪️ቀጣናዊ የልማትን ማነቃቃት ላይ ተመስርቶ የሞምባሳ-ናይሮቢ የባቡር መስመር እና የአዲስ አበባ-ጅቡቲ የባቡር መስመርሮችን ወደተቀሩት ጎረቤት ሀገራትም የማስፋፋትና የማሳደግ አላማ ያለው ነው።
▪️የቀይ ባህር ዳርቻ እና የምስራቅ አፍሪካ የባህር ዳርቻዎች ልማት መፋጠን አለበት። “two axes plus two coasts” በሚል የተሰየመው ይህ የእድገት ማዕቀፍ የ Industrial Belt እና Economic Belt ግንባታ በማፋጠን የለቀ የስራ ዕድልና እድገት ማሳካት፣ ግለ-ወጥ የልማት አቅምን ማሻሻልና የወቅቱን ፍጥነት መከታተል..። በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ፣ የአፍሪካ ቀንድ አገራት የሚገጥሟቸውን አስተዳደራዊ ፈተናዎች ለመቋቋም ውጤታማ ዘዴ እንዲኖራቸው መደገፍ የሚል ነው።
▪️የቀጣናው ሀገራት ከራሳቸው ሀገራዊ ተጨባጭ ጋር የተጣጣሙ የእድገት ጎዳናዎችን በመፈተሽ፣ በአስተዳደርና መንግስታዊ ጉዳዮች ላይ መስተጋብራዊ ልውውጦች እንዲጠናከሩ ብሎም ጠቃሚ ልምዶቻቸውን እንዲለዋወጡ እና ቻይና ድጋፏን ታደርጋለች።
▪️በቀጣናው ታመጋጋቢ፣ ተደጋጋፊ፣ የተረጋጋና የተቀናጀ የዕድገት ምህዳር እንዲፈጠር ቻይና አስፈላጊውን ድጋፍ ታቀርባለች።
▪️ልዩ ልዩ ብሔር-ነክ፣ ሀይማኖታዊና ክልላዊ አለመግባባቶች በአፍሪካዊ መንገድ የሚፈቱበትን ሂደትም ቤይጂንግ የምትደግፍ ይሆናል።
ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ ዋንግ ዪ አፅንኦት ሰጥተው እንደገለፁት “ቻይና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል እና የአፍሪካ ቅን አጋር እንደመሆኗ የአፍሪካ የልማት ስትራቴጂዎች ከቻይና Belt & Road Initiative ጋር የተሰናሰለ እንዲሆን ትሻለች።” ነበር ያለችው።

የዓባይልጅ #HornOfAfrica #Ethiopia

https://www.facebook.com/100003626461788/posts/2624804344317089/?mibextid=Nif5oz

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2503971396400385&id=100003626461788&mibextid=Nif5oz

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories