ቻይና የናይል ጂኦ-ፖለቲካ ጨዋታ ለዋጭ

china changing nile geopolitics

Esleman Abay – የዓባይ ልጅ


ቻይና በናይል ተፋሰስ የምዕራባዊያንን ነባር ጫና በማምከን ሰፊ ተሳትፎ እያደረገች መሆኗ ይታወቃል። ለዘመናት በቅኝ ገዢ ተቋማት IMF እና WORLD BANK ይሁንታና ክልከላ ስር የነበረውን የውሃ ሃብትን የማልማትና ያለማልማት ታሪክ ቤይጂንግ በእጅጉ ለውጣዋለች።

ኡጋንዳ

የኡጋንዳ የሀገሪቱ ትልቁ የሃይድሮ-መሰረተ ልማት ፕሮጀክት ለሆነው የኩራማ ግድብ ከ IMF ብድር ተከልክላ ነበር። ያስከለከለችውም ግብፅ ናት። ነገር ግን ቻይና 1 ቢሊዮን ዶላር አበድራት ግንባታውን በቻይና ኩባንያዎች እንዲገነባ ሆኗል። ለተለያዩ የውሃ ሀይል ማመንጫ ግድቦችም ተጨማሪ 900 ሚሊዮን ዶላር አበድራታለች።

ሱዳን

ሱዳንም ለሜሮይ ግድብ ማስፋፊያ ከአውሮፓዊያንና ሌሎች ለጋሾች የጠየቀችው ብድር ውድቅ ነበር የሆነባት። እዚ ላይም ቻይና የ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ብድር አቀረበችላት። ለሌላ ግድብ ማሳደጊያም 396 ሚሊዮን ዶላር፣ ለ ጀበል ግድብ 705 ሚሊዮን ዶላር፣ 711 ሚሊዮን ለሻሸኪ ግድብ እንዲሁም 838 ሚሊዮን ዶላር ለላይኛው አትባራ ፕሮጀክት አቀረበችላት፡፡

ኢትዮጵያ
አገራችንን ብንመለከት እ.ኤ.አ. በሚያዚያ 2011 የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ “ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ ከመገንባት ልታስቆመን አትችልም፡፡ በዓባይ ወንዝ ላይ ግድቦች በመገንባት የራሳችንን ሃብት መጠቀም እንችላለንም እንፈልጋለንም” ሲሉ ይፋ አደረጉ…
በመቀጠልም የተከዜ፣ ጊልገል ጊቤ 3 እና 4 ፣ ጣና-በለስ፣ ፊንጫ አመርቲ የውሃ ኃይልና የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክቶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

ለ IMF እና WORLD BANK ያቀረብነው የብድር ጥያቄ ውድቅ ተደረገ። እነሱ በከለከሉን ማግስት ግን ቻይና “..አታስቡ..” አለችን። የቻይና መንግሥትና የቻይና ዓለም አቀፍ የውሃ እና ኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን China International Water and Electricity Corporation በርካታ ቢሊዮን ዶላሮች መድበው የሃይል ማመንጫዎቹን ለመገንባት እንቅስቃሴ ጀመሩ። ለተከዜ ፕሮጀክት 365 ሚሊዮን ዶላር፣ ለጊቤ ሦስት 500 ሚሊዮን ዶላር ከአሜሪካ ጠይቀን ብንከለከልም ቻይና ሙሉውን አቀረበች፡፡

የጣና-በለስ የውሃ ኃይል ማመንጫ ካስፈለገው 500 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 85 በመቶው በቻይና ብድር ተሸፈነች። ለህዳሴ ግድቡም በይፋ ያልተነገረ የ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብድር አሰንደሰጠች ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ላይ ተመልክቻለሁ፡፡ ይኸውም የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መሠረተ ልማቶችን ለመዘርጋት በሚል የተሰጠ ነበር።

ይህ የቻይና Game Changer የተባለለት የ Soft Diplomacy አቋማ በለይም ከኢትዮጵያ ጋር ካላት strategic partnership አኳያ ከአሁናዊም ሆነ ለመፃኢ ጫናዎች ሚዛን ማስጠበቂያ ስለመሆኑ አያጠያይቅም።
– Esleman Abay የዓባይ ልጅ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories