ኃይሌ ገሪማ: ዓባይ እና ገጽታ ግንባታ

dawit Tesfaye, writer/director

በካይሮ 36ኛውን ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ተጋብዤ ለመታደም ወደ ግብጽ ስሳፈር 36 የሚለው ቁጥር ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ነው፡፡ እኛ ሀገር ለሰላሳ ስድስተኛ ጊዜ የተካሄደ ዝግጅት ለማስታወስ መሞከሬ አልቀረም፡፡ እኔ አልመጣልኝም እናንተ እርዱኝ፡፡ (አንድ ተንኮለኛ ወዳጄን ይሄንኑ ጥያቄ አቅርቤለት ክረምት ብሎኛል)
ካይሮ ትልቅ ከተማ፤ ግብጽም ትልቅ ሀገር እንደሆነች ለመረዳት ከአውሮፕላን ማረፊያው ወደ አረፍኩበት ማሪዮት ሆቴል መጓዝ በቂዬ ነበር፡፡ እኔ ግን በጠርጣራ ኢትዮጵያዊነቴ ወደኛ ሀገር የሚመጡት እንግዶች ከቦሌ ወደ ሸራተን የሚያደርጉት አይነት ጉዞ ቢሆንስ ብዬ ለመወሰን ታገስኩ፡፡ በቆይታዬም ግን ካይሮ ትልቅ ከተማ መሆኗን ነው የተረዳሁት፡፡


የፌስቲቫሉ የመክፈቻ ዝግጅት በግብጽ የጦር ሰራዊት ሙዚየም አምፊ ቴአትር በመሰለ የተንጣለለ ስፍራ ነበር የተካሄደው፡፡ የጊዜያዊ መድረኩ ግዝፈት፤ የሲንፎኒው ዝግጅት፤ ከስፍራው በቀጥታ የሚያሰራጩት ጊዜያዊ የቴሌቭዥን እስቱዲዮዎች ብዛትና አይነት (እዛው ስፍራ ላይ ከቶክ ሾው እስከ ቃለ-መጠይው ይሰራሉ)፤ የዝነኛ ሰው መስተንግዶ ባህላቸው (glamour and star culture) እንዳለ ‘ባሻ አሸብር በአሜሪካ’ ነገር አድርጎኝ ነበር::


በዚህ የመክፈቻ ዝግጅት ላይ ነበር የኛ ሃይሌ ገሪማ ከዳኞቹ አንዱ በመሆን ስሙ የተጠራው፡፡ ሃይሌ ገሪማ በካይሮ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ትልቁን ቦታ የሚሰጠውን የአለማቀፍ ውድደር ከሚዳኙት ፊልም ሰሪዎችና ፊልም-ሀያሲዎች ማካከል አንዱ በመሆን ወደመደረክ እንዲወጣ የተጠራው “ሃይሌ ገሪማ ከኢትዮጵያ” ተብሎ ነበር፡፡ ምን አለፋችሁ የሱ ስም ከኢትዮጵያ ተብሎ ሲጠራ ከአራቱም መዐዘናት ፌስቲቫሉን ለመታደም መጥተው የተዋወቅኳቸው ዳይሬክተሮች፤ ሲኒማቶግራፈሮች፤ ጸሃፊዎች፤ እና ሀያሲዎች ላይ ደረቴን እንደመንፋት፤ አንገቴን ቀና እንደማድረግ አልኩኝ (በፊልም ረገድ እዚያ ብዙ አንገት የሚያስደፉ ነገሮች አሉ)፡፡
ሃይሌ ገሪማ በዚያ ፌስቲቫል እጅግ ከተከበሩት ሰዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ልዩ ቦታ እንደተሰጠው “V.I.P” ተጽፎባት ከሆቴል ወደ ሲኒማ ቤቶቹ ከሚመላለስባት ጥቁር ዘመናዊ መርሴዲስ ሲወርድና ሲገባ እየተከተሉ የሚያወሩት ሰዎች ብዛት ሰውዬው በአለም አቀፍ ደረጃ ስላለው እውቅናና ክብር ይናገራል፡፡ እኔም ከፌስቲቫሉ መክፈቻ በኋላ በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ሃይሌን ያወራሁት፡፡ ከውሃ ዳር በተዘጋጀው ትልቅ ግብዣ ላይ የውስኪና የወይን ጠርሙሶች እየተንኳኩ፤ የግብጽ አክተሮችና እነ ሃይሌ ላይ የካሜራ ብልጭታዎች አይን እያጥበረበሩ ባለበት ስፍራ በርካታ የውጪ ዜጎች ከበውት ሳለ ከጀርባው ተጠግቼ “እንደምናለህ ሃይሌ” ስለው አዟዟሩ አማርኛ በመስማቱ የበረሃ ወዳጁን እንዳገኘ ሰው ይመስላል፡፡ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ማንነቴን ጠይቆኝ፤ ነገ ከነገ-ወዲያ እንደምንገናኝ ተነጋግረን ለከበቡት ሰዎች ቦታዬን ለቀቅኩ፡፡ ከዚያ በኋላ በተለያዩ አጋጣሚዎች በተለይ ፊልም የሚታይባቸው ቦታዎች ላይ ተገናኝተን አጠር ያሉ ጨዋታዎችን አድርገናል፡፡
ሃይሌ ገሪማን እና እሱ በሌሎች ሀገር ዜጎች ላይ ስለኢትዮጵያ የሚፈጥረውን ትዝብት (impression) ሳስተውል በኛ ሀገር ገጽታ ግንባታ እየተባለ በየአጋጣሚው የሚወራው ወሬ (ወሬ ነው) ላይ ከባድ ጥያቄ እንዳነሳ አድርጎኛል፡፡ አንድ ሃይሌ ብቻውን የቱም ዘመቻ የማይሰራውን ማስተዋወቅ ሲሰራ አይቻለሁ፡፡ እንደፊልም ሰሪነቴ በግብጽ ከየሀገሩ የመጡት ፊልም ሰሪዎችና ፊልሞቻቸው ምን ያክል ለሀገራቸው አምባሳደር እንደሚሆኑ ለመታዘብ ከባድ አይደለም፡፡ የናጅዋ ናጃር “አይስ ኦፍ ኤ ቲፍ” (eyes of a thief) የካይሮውን ጨምሮ በመላው አለም ባሉ ፊስቲቫሎች ሲታይ ከብዙ የቢቢሲና የሲ.ኤን.ኤን ዘገባዎች ልቆ የፍልስጤሞችን ታሪክ በመናገር ተጽዕኖ እንደሚፈጥር ጥርጥር የለውም፡፡ (ከበርካታ ፊልም ሰሪዎች ጋር ያደረግኩትነ ቃለ-መጠይቅ ለወደፊት አስቀምጣቸዋለው፤ ከናጅዋ ጋር ያደረግነውን ግን እዚሁ ታገኙታላችሁ)


ታዲያ ከነዚህ ፊልሞች አብዛኛዎቹ በሀገራቸው መንግስት (የባህል ቢሮዎቻቸው) ድጋፍ የተደረገላቸው ናቸው፡፡ ፊልሞቹ ሲጀምሩ ከሰሯቸው ስቱድዮ ስሞች ጋር የመንግስት ባህል ቢሮዎች ተጽፈው ታነባላችሁ፡፡ ስታወሯቸው አንዱ ካሜራውን፡ ሌላው ገንዘቡን፤ አንዱ ሰቱዲዮውን፡ ሌላው ባለሙያዎቹን ያገኘው በመንግስት ድጋፍ ነው፡፡
የግብጽ መንግስት ለፌስቲቫሉ ድጋፍ የሚያወጣው በሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ በብልጣብልጥ አይን ሲታይ ሞኝነት ይመስላል፡፡ በመቶ የሚቆጠሩ እንግዶችን ከመላው አለም የአውሮፕላን ትኬት ከፍለው፤ በባለ አምስት ኮከብ ሆቴል የምግብ ወጪን ሸፍነው የሚጋብዙት እውነተኛ ገጽታ ግንባታ ያለውን ትሩፋቶች ስለሚያውቁ ነው፡፡ ግብጽ አንደኛ ደረጃ የገቢ ምንጯ ቱሪስም መሆኑን ያስታውሷል፡፡
በግብጽ ሌላው ቦታ የሚያሰጠን ጉዳይ ዓባይ ነው፡፡ ሁሉም ግብጻውያን ከኢትዮጵያ ነኝ ስላቸው ስለዓባይ ለማውራት ይፈልጋሉ፡፡ አንዳነዶቹ ከግብዣ ጋር ሁሉ ነው፡፡ ይሄኔ እኔ አምባሳደር ሆንኩኝ! ዓባይ ለግብጾች እስትንፋስ እንደመሆኑ አብዝቶ ያሳስባቸዋል፡፡ የዓባይ ጉዳይ በግብጾችና በሌሎችም ሀገር ዜጎች ዘንድ ኢትዮጵያን ትኩረት እንዲሰጣት ማድረጉንና እጅግ በጣም ስስ (sensitive) ጉዳይ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በዓባይ ተነስተን ከብዙ ግብጻውያን ጋር ስለብዙ ጉዳይ ተጨዋውተናል፡፡ አንዳንዶቹ በልምምጥ “መቼም ፈጣሪን ካልፈራችሁ…” ሲሉ ሌሎቹ ዛቻ ቢጤ ይሰነዝራሉ፡፡ ዓባይ ለኢትዮጵያ የሚፈጥረው ገጽታ አይነት በቀጣዮቹ አመታት ፍጹም ሊቀየር እንደሚችል መገመትም አዳጋች አይደለም፡፡ እናም ምን ይምሰል የሚለውን ማሰብ ወሳኝ ነው፡፡ ይሄኔ ነው የፊልም ልዩ ሃይልን መጠቀም ብልህነት የሚሆነው፡፡
በካይሮ የፊልም ፌስቲቫል ከመላው ዓለም የመጡ ፊልሞች ከመታየታቸውም በተጨማሪ፤ ውይይቶች፤ ኤግዚብሽኖች፤ ጥያቄና መልሶች፤ ጉብኝቶችና የልምድ ልውውጦች ተካሂደዋል፡፡ የመዝጊያው ዝግጅት በግብጽ መታወቂያ ፒራሚዶቹ ላይ ነው የተካሄደው፡፡ በፌስቲቫሉ በብዙ ዘርፎች በርካታ ሽልማቶች ቢኖሩም በጉጉት የሚጠበቀውና ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ሃይሌ ገሪማ በዳኝነት የሚሳተፍበት የአለም አቀፍ ውድድር ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ አሽናፊ ሆኖ የወርቃማ ፒራሚድ ሽልማት የተቀበለው በኒማ ጃቪዲ ዳይሬክት የተደረገው የኢራኑ ሜልቦርን (Melbourne) ነው፡፡ ይሄንን ፊልም እንደምንም ብላችሁ ካላያችሁ የሆነ ነገር ይጎልባችኋል፡፡

The Cairo international film festival is one of the biggest film festivals in the world bringing together hundreds of filmmakers, critics, journalists from all over the world including the Ethiopian Haile Gerima who is in the jury for the international competition. This is a brief interview dawit Tesfaye had with Najwa Najjar- a Palestinian-Jordanian filmmaker- director of the highly praised film “EYES OF A THIEF”- Palestine’s entry for the 2015 Oscars.
Q. What inspired the story for “eyes of a thief? Was there a particular incident or story?
Najwa- Basically we live under occupation with no home to live in, with no children, no future, with no plan for our lives; we are left with no options. So that is the situation in general. And in the second Palestinian uprising in 2002, there was a boy who planned an operation. He didn’t kill any civilians, and he never claimed responsibility. So that’s one of the inspirations for “eyes of the thief”
Q. Do you make an effort to use a unique structure in story telling?
Najwa- I am always interested in finding and using different structures to narrate every story. In my first film, I used a linear kind of storytelling. In this one I used flash backs going back and forth to uncover the secrets of the main character.
Q. You chose to make Israel a shadow in the story instead of making it the center of the story as many Palestinian films do. Was that a conscious choice, or did the writing dictate it?
Najwa- I mean the operation is there, soldiers are there. But, you are right; it suffocates us. It doesn’t always have to be a direct conflict. But even as shadows, don’t forget that they are always there.
Q. Do you consider yourself to be a Palestinian freedom fighter?
Najwa- There is something that always burns inside me, something that has to be said. And, may be my way of expressing it is through cinema. I am fortunate to be able to do it twice, very fortunate. Whether that makes me a fighter, I don’t know. Though it’s a form of resistance,  I don’t consider myself to be anything other than a person trying to contribute something.
Q. For?
Najwa- Cinema
Q. When the protagonist in your story says “….he is dead already…”, was it you talking?
Najwa- (Long laugh) Did you think it was not the character?
Q. (Laugh) I just wanted to hear it from you
Najwa- I wrote the script.
Q. Do you consider such a person to be dead?
Najwa- (Long laugh) I make the stories for you to decide. You can’t ask the writer or the director what they think (laugh). You have to react.
Q. Does being in the Oscars make any difference for you as a filmmaker?
Najwa- You know you will have the highest title bestowed upon you- “Oscar nominated film”. The importance of that for me is that a story which might not be seen in the west, now it will be seen. That is the importance
Q. Accusing the U.S of helping Israel in the occupation, don’t you find it to be ironic to promote you film as an Oscar entry from Palestine?
Najwa- May be because they have such a big influence in our lives, its time for them to see different narratives from the ones they see in Hollywood. And, Hollywood has demonized the Arabs, Muslims, and Palestinians.
Q. What will your next project be about?
Najwa- It is a musical.
Q. Really, can you tip me?
Najwa- No (laugh)
Shukern!
Najwa- Afwan!

✍️ dawit Tesfaye, writer/director

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories