ናይጄሪያዊው ኦቦሳንጆ ከ 44 ዓመታት በኋላድጋሚ በኢትዮጵያ ላይ ያሤሩ ይሆን?

በ1970 ዓ.ም የናይጄሪያ ኘሬዚዳንት ጀኔራል ኦሊሶንጎ ኦቦሳንጆን የኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል የሽምግልና ኮሚሽን ሰብሳቢ እንዲሆኑ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ወስኖ ነበር። ይህንን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ተልኮ ለመፈጸም ኦቦሳንጆ ወደ አዲስ አበባና ሞቃዲሾ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸውን መልእክት አስይዘው ላኩ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጀኔራል ጋርባ ሌ/ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም የኦቦሳንጆን መልዕክት ይዘው አዲስ አበባ ይመጡና ወይይት ያደርጋሉ።

“ወንድሜ ጀኔራል ኦቦሳንጆ ስለ አፍሪቃ ሰላም በመቸገርና በድርጅታችን ማለትም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት፤ይኽንን እርምጃ በመውሰዳቸው በጣም አመሰግናለሁ። ነገር ግን ጉዳዩ ቀላል እንዳለመሆኑ መጠን መልስ ከመስጠቴ በፊት ጓደኞቼ ጋር መመካከር ስላለብኝ ወደፊት ሁኔታውን መርምረን መልስ እንሰጣለን” በማለት መንግስቱ ኃይለማርያም አጭር ምላሽ መስጠታቸውን የሌ/ኮ ብርሀኑ ባይህ አዲስ መጽሀፍ ይጠቅሳል፤(ገጽ 510)።

ኮረኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ያደረጉት፤የኢትዮጵያ ግዛት በሶማሊያ እጅ እያለ ከሶማሊያ ጋር ቁጭ ብሎ መነጋገር የማይታሰብ ስለሆነ ነበር። ይኽንኑ በግልጽ መናገሩ ደግሞ ኢትዮጵያን ሰላም እንደማትፈልግ እንዳያስቆጥራትና እንዳያስነቅፋት ለማድረግና ማምለጫ ዘዴ በመፈለግ ጊዜ ለመግዛት መሆኑን በመጽሀፉ ተጠቅሷል።

“የሁሉም ሩጫ ኢትዮጵያ መልሳ እንዳታጠቃ ለማድረግና ቢቻልም የተወሰነ መሬት በመልቀቅ እንድትስማማ ለማድረግ ነበር። ኢትዮጵያ መልሳ በማጥቃት ከድንበሯ አልፋ ሶማሊያ በመግባት ዚያድ ባሬን ለመገልበጥ ትሞክራለች የሚል ጠንካራ ስጋት ተፈጥሯል።

ኦባሳንጆ የተንቀሳቀሱት በአሜሪካ ግፊት ነበር። ስለሆነም የናይጄሪያው ውጭ ጉዳይ ሚኒሥትር ጀነራል ጋርባ ከመንግሥቱ ኃ/ማርያም በተሰጠው መልስ አልረካም። “ኘሬዚዳንት ካርተር ከሦስት ቀን በፊት ደብዳቤ በመላክ የማስታረቅ ተግባራችንን እንድንገፋበት አጥብቀው ጠይቀውናል” አለ። ብርሀኑ ባይህ በዚሁ መጽሀፋቸው የአሜሪካንን በተለይ የኘሬዚዳንት ካርተርን ፍላጎት ሲገልጹ “…አሁንም ካርተር ይኽንን የመሰለ መልዕክት የላከው ስለሰላም ወይም ስለኢትዮጵያ መወረር ተጨንቆ ሳይሆን ሶማሊያን ከውርደትና ከጉዳት ለማዳን እንደነበር ግልጽ ነው። በአንጻሩም ከኢትዮጵያ ደግሞ ድላችንን በመንጠቅ በሞራልም ብቻ እንኳን ቢሆን ለመጉዳት ነበር።( ያልታሰበው የሕይወቴ ፈታኝ ጉዞ ከሌ/ኮ ብርሀኑ ባይህ መጽሀፍ ገጽ 510 የተወሠደ)

የናይጄሪያው የቀድሞ ኘሬዚዳንት ጀኔራል ኦሌሴንጎን ኦባሳንጆ 1970 ዓም ላይ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የኢትዮጵያና ሶማሊያ የሽምግልና ኮሚሽን ሰብሳቢ ነበሩ። በወቅቱ ከሳቸው ሽምግልና ጀርባ የአሜሪካና ኘሬዚዳንቷ ጂሚ ካርተር ስውር ግፊት ነበር።

ከ44 ዓመታት በኋላ ዛሬ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ጡረተኛው ጄነራል ኦባሳንጆን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ አደርጎ መሰየሙ ተነግሯል። የአሁኑ የኦባሳንጆ ተልዕኮ የህብረቱ ተልዕኮ ተብሎ ቢነገርም፤ አሁንም አሜሪካና ኘሬዚዳንቷ ጆ ባይደን ግፊትና ረጅም እጅ ነጻ አለመሆኑን ብዙ ምልክቶች መጥቀስ ይቻላል።

By Eskinder Kebede

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories