አለም ያልዘመረችለት ሳይንቲስት | ኒኮላ ቴሥላ

ስለ ሳይንሳዊ ፈጠራ ሲነሳ ቀድሞ ትዝ የሚለን ቶማስ ኤዲሰን ነው። ሁላችንም ስለ ኤዲሰን የበረከቱ ፈጠራዎች በተለይም በዬእለት ኑሯችን ውስጥ መብራትን ስለማበርከቱ..

ይሁን እንጂ መታወቅ ሲኖርበት እምብዛም እውቅናው ያላገኘ፣ ለነ ኤዲሰንና ሌሎች ፈጠራዎች አብርክቶው የበዛ፣ እጅግ ባለ ተሰጥኦ ሰው አለ፤ እሱም ኒኮላ ቴስላ ይባላል።

ከቶማስ ኤዲሰን ይልቅ ቁጥር አንዱ የፈጠራ ጀግና ኒኮላ ቴስላ ነው ብልዎት ምን ይሉ ይሆን?!
እንደውም ቶማስ ኤዲሰን ከ(ሠዋዊ) የፈጠራ ሰውነቱ ይልቅ የቢዝነስ ሰውነቱ ያደላል ብልዎትስ ምን ይሉኝ ይሆን?!

የኒኮላ ቴስላ ልጅነትና እድገት

ኒኮላ ቴስላ ደሙ ከሰርቢያ የሆነ አሜሪካዊ የፈጠራ ሰውና የፊዚክስ ሊቅ ነው። የተወለደውም ከ162 አመታት በፊት በሐምሌ 10፣ 1856 ነበር።

በተማሪ ቤት ቆይታውም ፕሮፌሰር የሆኑት መምህሩ በሚያሳዩት የኤሌክትሪሲቲ ትምህርት መማረክ ጀመረ።
ባለተሰጥኦ ስለነበረም “integral calculus” በአእምሮው ብቻ መስራት ይችል ነበር። ወደ ኦስትሪያ ፖሊ-ቴክኒክ ተቌም በመግባትም እጅግ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በተቌሙ የጀመረውን ትምህርት ቀጠለ።

ከአባቱ ሞት በኌላም ፕሮፌሰር መምህሩ ለአባቱ ይልኴቸው የነበሩ ደብዳቤዎችን አገኘና አነበባቸው። ደብዳቤዎቹም “ቴስላ ከትምህርት ቤቱ እንዲወጣ ካልተደረገ በእላፊ ስራና ጫና ሊሞት ይችላል” የሚሉ ነበሩ።

የድካሙን ዋጋ ገደል የከተተ ድርጊት በአባቱ መፈፀሙን ያወቀውም የትምህርት ክፍያውን በቁማር ምክንያት መጥፋቱን ሲመለከት ነበር። ከዚህ በኌላም ቴስላ ለፈተና በቂ ዝግጅት ለማድረግ ዝግጅትም ሆነ ፍላጎቱ ስለጠፋበት ፈተናውን ሳይወስድ ቀረ። የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱንም ሳያጠናቅቅ ቀረ።

በ 1897 እኤአ ቴስላ የነርቭ ጤና እክል ገጥሞት ነበር። በ 1881 ወደ ቡዳፔስት በመጔዝ በቴሌግራፍ ኩባንያ ውስጥ መስራት ጀመረ።

ቴስላና ኤዲሰን

በ 1884 እኤአ፣ ቴስላ ወደ አሜሪካ አቀና። የኤዲሰን ማናጀር በሆነው ቻርለስ ባችለር ፍላጎት መሰረትም ኒውዮርክ በሚገኘው የቶማስ ኤዲሰን ማሽን ውስጥ እንዲሰራ ሆነ። ለአንድ አመት ያህል ሲሰራም ቶማስ እልዲሰንን በትጋቱና በፈጠራው አስገረመው። ሁለቱ በጋራ ሆነው የኤዲሰን ፈጠራዎችን ለማሻሻል መስራት ቀጠሉ። ይሁንና አብሮነታቸው ባለመስማማት በመለያየት ተቌጨ።

ነገሩ እንዲህ ነበር። ኤዲሰን ቴሥላን 50 ሺህ ዶላር ይሸልመው ዘንድ የኤዲሰንን DC ዲናሞዎች ዲዛይን እንዲያሻሽል ሀሳብ ያቀርብለታል። ከወራት ጥናት በኌላም ቴሥላ ዲዛይኑን አሻሽሎ ማቅረብ ቻለ። ሽልማቱን ሲጠይቅም ኤዲሰን አሻፈረኝ አለ። እየቀለደ እንደነበረም በመግለፅ። ኤዲሰን ለቴሥላ “የእኛ የአሜሪካውያንን ቀንድ አዋቂነት አታውቅም ማለት ነው!” እንዳለውም ተፅፏል። ይህን ስላቅና ክህደት ተከትሎም ቴስላ ከኤዲሰን ጋር መስራቱን አቆመ።

የኤሌክትሪክ ጦርነት Battle of the currents

ቴሥላ ከኤዲሰን ኩባንያ ጋር ስራውን ካቆመ በኌላ የራሱን የመብራት ኩባንያ መሰረተ። በ AC ዥረት የሚሰራውን መብራት ቴክኖሎጅ አእምሯዊ ንብረትም ማስመዝገብ ቻለ። ነገር ግን ፈጠራውን ለገበያ አቅርቦት ለማምረት የቴሥላ ኩባንያ ባለድርሻ ኢንቨስተሮች ፈንድ ለማድረግ አቅማሙ። በወቅቱ የነበረው የዘርፉ ጠንካራ ፉክክር ለኢንቨስተሮቹ ማመንታት ምክንያት እንደነበር ይነገራል። እንቨስተሮቹ ከኩባንያው ለቀቁ። ቴስላንም ባዶ አስቀሩት። አእምሯዊ ንብረቱንም ለነበረበት የአክስዮን ድርሻ እንደ ክፍያ ለማስረከብ ተገደደ።

ችግር ላይ የወደቀው ቴስላ ህይወቱን ለማቆየት ሲል የእጅ ሙያ እየሰራ ኑሮውን ቀጠለ። በቀን 2 ዶላር ለማግኘትም የጉድጔድና ቦይ ቁፋሮ ስራንም ሳይመርጥ ለመስራት ተገደደ።

በ 1886፣ ቴሥላ Alfred S. Brown እና የኒውዮርክ ጠበቃ የሂኑትን Charles F. Peck የተባሉ ሰዎች ተዋወቀ። ሰዎቹ የፈጠራ ሰዎችን በገንዘብ ፈንድ የሚረዱ ናቸው። ቴሥላንም ፈንድ ለማድረግ ተስማሙ።
በ 1887 ቴሥላ በ AC ኤሌክትሪክ ዥረት የሚሰራ ሞተርን ሰራ። ይህ ፈጠራ ያል ሽቦ ረጅም ርቀት ድረስ ስለሚያገለግል ታዋቂ ቢሆንም ቶማስ ኤዲሰን ደግሞ ለአደጋ ያጋልጣል በማለት ዘመቻ ከፈተበት።

Westinghouse የተባለ ተቌም ተስላን ቀጠረውና ለ DC ዥረት የሞተር ፈጠራዎቹም ፈቃድ እንዲሁም ለራሱ ላቦራቶሪ ሰጠው።

የቴስላን ፈጠራ ተወዳጅነት የፈራው ኤዲሰን ከቴስላ የተሻለ የገበያ መላዎች ክህሎት ነበረውና በትልስላ ላይ ማንኛውንም ዘመቻ አድርጎ ገበያውን ለማሸነፍ ወሰነ። የኤሌክትሪክ ዥረት ዘመቻም ይሄኔ ተጀመረ።

የቴስላን ፈጠራ በህዝብ እንዲፈራ በብዙው የደከመው ኤዲሰን በወቅቱ በህዝብ ፊት እንዲገደል የተወሰነበትን ነፍሰ ገዳይ ወንጀለኛ ግድያ በቴሥላው የ DC ኤሌክትሪክ ጅረት የተገጠመለት ተንቀሳቃሽ ወንበር ላይ ሆኖ በአደባባይ በዥረቱ እንዲሞት ከባለስላጣናቱም ጋር መክሮ ተተግባሪ እስከማድረግ ተጓዘ። በ 1890 የነበረው የፋይናንስ ቀውስ ደግሞ ሰኔና ሰኞን በቴስላ ኩባንያ ጋር አመጣበትና የገንዘብ ፈንድ ማግኘት ሳይችል ኩባንያውም ከስሮ እንዲዘጋ አስገደደው።

የቴሥላ ልዩ ልዩ ፈጠራዎች

የ DC ሽቦ አልባ የኤሌክትሪክ ፈጠራው ዋነኛው ነው። ይህንን ፈጠራ በተለያየ መንገድ አለም መጠቀም ከጀመረ ቆይቷል። አሁን ላይ ደግሞ ተፈላጊነቱ ጨምሯል። ቴስላ ሞተርስ በመባል በመታሰቢያነት የተከፈተው የአሜሪካ ኩባንያም የኤሌክትሪክ መኪኖችን መሸጥ ጀምሯል። በ ኤሌክትሪክ ዥረት ዘመቻው ኤዲሰን ቢያሸንፍም ጦርነቱን ያሸነፈው ግን ቴስላ ሆኗል።

ቴስላ የፍሎረሰንት መብራትንም የፈጠረ ሳይቲስት ነበር።

ለራዲዮ ፈጠራው አለም ማርኮንክ የተባለ ሳይንቲስትን እውቅና ብትሰጥም እውነታው ግን ትልስላ ከ 1 አመት በፊት በይፋ ፈጠራውን አሳይቶ ነበር። ይሁን እንጅ የአሜሪካ አእምሯዊ ንብረት ፅህፈት ቤት የቴስላን ሮያልቲ ክፍያ በመተው ፓተንቱን ለማርኮኒ ሰጥቷል።

የመጀመሪያው የራዳር ሲስተም በ 1934 አ.ም ሲፈጠር መሰረት ያደረገው የቴስላን የራዲዮና የሃይል ምጣኔ የ 1917 ፈጠራዎች ላይ ነበር።

ሪሞት ኮንትሮልንም የፈጠረው ቴሥላ ነው።

በኒያንጋራ ፏፏቴ ላይ AC ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕላንት 1895 ላይ ነበር በቴሥላ የተገኘው።

ቴሥላ ኮይልንም (Tesla coil) በ1891 መፍጠር ችሏል።

የኤሌክትሪክ ሞተርንም በ 1930 ማግኘት ችሏል። በአለም ጦርነትና በኢኮኖሚ ቀውሱ ሳቢያ ግን ለገበያ ለማቅረብ ምቹ ሳያደርግለት ቀርቷል።

በ 1900 ኒኮላ ቴሥላ ታላቅ ፕሮጀክትን ጀምሮ ነበር። ፕሮጀክቱ ሃይልን ያለ ገመድ ለማስተላለፍና ሽቦ አልባ ግንኙነትን ለመፍጠር የሚያስችሉ ግዙፍ የሆኑ ማማዎችን ግንባታም ያቀፈ ነበር።

ቴስላ ሳይንቲስት እንጅ ስራ ፈጣሪ ኢንተርፕረነር አልነበረም። ፈጠራዎቹ ከሱ ዘመን እጅግ የራቁ ናቸው። የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1943 ላይ ለማክሮኒ የነበረውን የራዲዮ ፈጠራ አእምሯዊ ንብረት እውቅና የቴሥላ መሆኑን በማረጋገጡ ለቴስላ ሰጥቷል።

ፈጠራዎቹ ታላቅ ቢሆኑም እንደ ኤዲሰን በቢዝነዝ ስትራቴጂ ላይ ክህሎት አልነበረውም። የሱ ፈጠራዎች ለሌሎች ፈጠራዎች መነሻ እየሆኑ አለምንም ግለሰቦችንም ጠቅመዋል። የቴሥላ ፈጠራዎች ግን አንዳቸውም ለፈጣሪያቸው ቴስላ ፈይደውለት አያውቁም።

ቴስላ ትዳርም አልነበረውም። በአእምሮ ህመም በተለይም በ hallucinations ይሰቃይ ነበር።

ቴሥላ በጥር 7፣ 1943 ከዚህች አለም ሲለይ ቤሳ ቢስቲን የሌለው ምስኪን ነበር። በህወት ዘመኑ ላበረከታቸው ፈጠራዎች አለማችን አንድም እውቅና አልቸረችውም ነበር።

በአሜሪካው ግዙፍ የለይል ማመንጫ ሁቨር ግድብ ላይ የቴስላ ፈጠራዎች ለአገልግሎት ውለዋል። ታዲያ ፍትህ አልባዋ አለማችን የቴስላን ፈጠራዎች ሌሎችን ቢሊየነር አድርጋ ቴስላ የመጨረሻ የዕድሜ ዘመኑን በድህነት ሲመራ አላዘነችለትም። የመብራት ፓል ተከላ የጉልበት ስራ እየሰራም ህይወቱን ለማቆየት እስከመገደድ ደርሷል።

ቶማስ ኤዲሰን የቴስላን የፍሎረሰንትና X-Ray ፈጠራዎች ቀምቶ በራሱ አድርጎታል። የራዳር ፈጠራ ዲዛይኑ ለገበያ እንዳይቀርብ አሲሮበታል። የኤዲሰን ፈጠራዎች ከጥቂቶች በስተቀር ከቴስላ የቀማቸውና ከሱ የቀዳቸው መሆናቸውን ጎግል ብታደርጉ ማረጋገጥ ትችላላችሁ። ለቴስላ አክብሮት እንኳን ያላሳየው ኤዲሰን የጉልበት ስራ እየሰራ ትዳር እንኳን ሳይኖረው ዘመኑን ለፈጀው ኒኮላ ቴስላ ርህራሄም አሸንዳላሳየው ታሪክ አስቀምጦታል። ኤዲሰን በመጨረሻው የእድሜ ዘመኑ የ 16 ዓመት ሚስት ነበር ያገባው። ሲሞ

ታዲያ ሞት ሲቃረብ ዕውነትን እናወራለንና ቶማስ ኤዲሰን ከመሞቱ ጥቂት ጊዜ በፊት በቴስላ ላይ የፈፀመውን ግፍ በይፋ አምኗል። ያደረገው ሁሉ እንደፀፀተውም ተናዟል።
…………………………….
Tesla VS Edison, ቪዲዮውን በዚህ ተመልከቱ
መረጃዎቼ ከተመቿቹህ አሪፍ አሪፍ ዶክመንተሪዎች በቻናሌ እጭናለሁና SUBSCRIBE አድርጉት
https://youtu.be/yWfBGj2GjBw
………………
Towards the end of Edison’s life, he was quoted as saying he wished he respected Tesla and his work more than he had. Too bad, at that point the damage had been done: Tesla died broke and lonely, while Edison died wealthy and with great self-esteem.

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories