አልፈው ካላለፉ ፈተናዎቻችን አንዱ ነው

ከአውሮፓ ህብረት የሆኑ ባለስልጣናት፣ ብሪታኒያ መራሽ በሆነ ኢ-መደበኛ ቡድን ውስጥ ተካተቱ፣ ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ጉዳይ በሚስጥር ተሰባሰቡ፤ ሚስጥራዊ ውሳኔም አሳለፉ። ጊዜው ደግሞ ህወሓት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ከፈጸመበት ከጥቅምት 24፡ 2013 በኋላ በነበሩት ከሰባት ቀናት በኋላ ነበር።
ስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ዓለም አቀፍ ፍርድቤት የማቆም፤ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠርና እንደ ሶማልያ ያለ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ማንበር፤ እንዲሁም ቀጣዩን የኢትዮጵያ እጣ ፋንታ ምን እናድርገው? በሚሉ ጉዳዮች ላይ አድራጊ ፈጣሪ ሆነው መወያየታቸው ይፋ ሆኖ ነበር።
ይህ የምዕራባውያን ሴራ ቢሳካ ኖሮ ግብ አድርገው ያስቀመጡት እንደ ዩጎዝላቪያ አይነት መገነጣጠል በኢትዮጵያም መፈፀም፤ ይህን ተከትሎም እንደ ቀድሞው የዩጎዝላቪያ ፕሬዚዳንት ስሎቦዳን ሚሎሶቪች አብይ አህመድን ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደነበር በሂደት ተጋልጧል – ይህን በማጋለጥ በተለይ ጂኦፖለቲክስ ፕሬስ የተሰኘው ተቋም የዝሆኑን ድርሻ የወሰደ ነበር።
ምእራባዊያን ይህን ፀረ ኢትዮጵያ እቅድ ለማስፈጸም ኮማንድ ኤንድ ኮንትሮል ፊውዥን ሴንተር -C2FC የተሰኘ ግብረ ሀይል አቋቁመው ወደ ስራ ገብተው ነበር።
ግብረ ሀይሉ ይሄንን የሚያከናውነው ኬንያ ውስጥ ከሚገኙ ተባባሪዎቹ ጋር ሲሆን በኬንያ ውስጥ የኦሮምያ የሽግግር መንግስትና የትግራይ መንግስት ለማቋቋም እንዲቻል በግል የደህንነት ድርጅቶች አማካኝነት ለአክቲቪስቶችና ለፕሮሞተሮች ስልጠና እየሰጠ መሆኑንም ያኔ ተጠቁሞ ነበር።
የአገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፉ ዜጎችን የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች ፔጆችና ግሩፖችን በተቀናጀ ሁኔታ የማዘጋቱ ተግባር ሰፊ ፕሮጀክት የተቀርፀለትና የC2FC ተልእኮ አካል መሆኑ በበርካታ ተጨባጮች የታየ ነው። የC2FC እኩይ ፕሮጀክት ሶሪያን ወደ ብጥብጥ ለማስገባት ምዕራባውያኑ ስራ ላይ ካዋሉት Basma Project መንትያ ነው።(UK በሶሪያ ያደረገችውን የBasma project ፕሮፓጋንዳ ተግባሯን ከአመታት በኋላ ይፋ አድርጋዋለች። Guardian እና መሰል ሚዲያዎቿ ይህንኑ በይፋ አስቀምጠውታል።)
UK ላይ ማዕከሉን የነበረው C2FC በኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ለአላማው እንደ ዋነኛ ማሳኪያ በማድረግ ያለመ ነበር። በዚህ ሴረኛ ፕሮጀክት የኢትዮጵያውን ጦርነት የተመለከቱ አለማቀፍ ዘገባዎች የኢትዮጵያን መንግስት በማጣጣል ከህዝቡ ለመነጠል የጥላሸት አንግሎችን እየጠመዘዙ ሽፋን እንዲሰጡት አቅጣጫ የተቀመጠበት ነው- በወቅቱ Geopolitical Press የተሰኘው ድረ-ገፅ በጥናታዊ ሪፖርቱ በሚገባ እንዳሰቀመጠልን። ሁሉም በሚባል ደረጃ አለማቀፍ የሚዲያ ተቋማት ፀረ ኢትዮጵያ በሆኑ ተከታታይ ዘገባዎች የተጠመዱት ከዚሁ ፕሮጀክት ተልእኮ በመነጨ እንደነበርም ጥናቱ አስቀምጦታል።
ታዲያ UK ውስጥ ዋና ማዘዣው የሆነው ግብረ ሃይሉ በተለያዩ አገራት ንዑስ ግብረ ሀይል አለው። ንዑስ ግብረ ሀይሎቹ Fusion Cels ይባላሉ።
C2FC በኬንያ ውስጥ ከሚገኙ የመንግስትና የግል የደህንነት ተቋማት ጋር ተባባሪዎቹ አማካኝነት በያንዳንዱ Fusin Cel ስር ለሚገኙ አባላት ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ተጠቁሟል። Fusion ሴሎቹ ትልልቅ ስም ባላቸው የሚዲያ ተቋማት የሚሰሩ ጋዜጠኞችን፣ ታዋቂ ሰዎችን፣ የዲሞክራሲ አክቲቪስቶችን፣ ምሁራንን፣ የርዳታ ሰራተኞችን፣ የግል የደህንነት ተቋማትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ያሰባሰበ ነው።
ንዑስ ግብረ ሃይሎቹ (Fusion Cells) የተለያዩ አገራት ዜጎች የተካቱበት ነው። ኢትዮጵያዊ ሱዳናዊ ግብፃዊ እንዲሁም የምዕራብ አገራት ዜጎች ይገኙበታል። በተለያየ አገር መቀመጫቸውን አድርገው የዘመቱት የ fusion cels ንዑስ ግብረ ሀይሎች በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ታንዛንያ፣ ሶማልያና ዩጋንዳ፤ በተጨማሪም በአውሮፓ፣ በኤዥያና ሰሜን-አሜሪካ የተሰማሩ ናቸው።
በያንዳንዱ የ C2FC ንዑስ ግብረ-ሀይል ( fusion cell) ስር የሚገኙ አባላት የኢትዮጵያን ጉዳይ የተመለከቱ መረጃዎችን ከማህበራዊ ሚዲያዎች ይሰበስባሉ። አሰፈላጊ በሆነበት ወቅትም ዕውነታን ለማዛባትና ሀሰተኛ ዜና ለማሰራጨት እንደሚጠቀሙበት Geopolitical Press በሪፖርቱ ጠቁሟል።
የማህበራዊ መገናኛ ገፆችን ማዘጋት፣ ሀክ ማድረግና ማስተጓጎል ደግሞ ሌላኛው ተግባራቸው ነው። ይህን መሰል ገፆችን የማዘጋት ተግባራቸው ታዲያ ሰሜን-ዕዝ ከመጠቃቱ ቀፊት ጥቂት ጊዜያት አስቀደሞ የተጀመረ ዘመቻ እንደሆነ ሪፖርቱ ማስቀመጡን ስንመለከት ነገሩ ቅንጅታዊ አፃፋ እንደሚያሻው ያስረግጥልናል።
በተለያዩ አገራት የተሰማሩ ናቸው የተባሉት Fusion Cels (የ C2FC ግብረ ሀይል ንዑስ ቅርንጫፎች) አባላት የመረጧቸውን ገፆችና ግለሰቦች ቀመምረጥ ሆ ብለው ገፆቹ እንዲዘጉ ለፌስቡክ የ community standard ቅሬታ ያቀርባሉ። ከዚህ ባሻገር የ Lobby ድርጅቶችን ቀጥረው ታላላቅ የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች ጥያቄያቸውን እንዲቀበሏቸው ያደርጋሉም ተብሏል።
በ 2021 ሁለተኛ ሩብ አመት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ደጋፊ ናቸው ያላቸውን ገፆችና ግሩፖች እንዲዘጉ የሆነውም በነዚህ fusion cels ቅንጅታዊ ስራ ነው ብሏል geopolitical press.
ይህ የፕሮፓጋንዳና የኢትዮጵያ ድምፆችን የማዘጋት ድርጊት የዚሁ የ C2FC ፀረ ኢትዮጵያ ግብረ ሀይል ድርጊት ተዋንያን እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ስመ “ኢትዮጵያዊያን” ሳይቀር መፈፀሙ ቢገርምም የመገረም ዘመን ማብቃት አለበት። ወቀሳው ስድቡ ትዝብቱ ወዘተ ምንም አይፈይድልንም በማለት ሀሳብ ተሰጥቶ ነበር። እንደ ምክረ ሀሳብ በወቅቱ ያጋራሁት ለአገርአቀፍና አለማቀፍ የዲጂታል አውድ ሰራዊት መገንባትና ለዚህም ምቹ ፕላትፎርም መዘርጋት ደግሞ ቁልፉ ስራ መሆኑን ነበር።
ያ ሁሉ የውጭ እና የባንዳ ርብርብ ለየትኛውም ብሄር ፋይዳ የሌለው ሲሆን የደም ገንዘብ ለማካበት ብቻ የተሰማሩበት ነበር። ጠቃሚ አላማ ቢኖራቸው ኖሮ ዛሬ ላይ ሲወቃቀሱ ሲሰዳደቡ አንሰማቸውም ነበር። በተለይም ወደ ትግራይ የሚጓጓዘው ርዳታ በተገቢው እየተከናወነ መሆኑን USAID የገለፀው በቅርቡ ነው።(ጦር ይሰደድበትና..)። የC2FC ፕሮጀክት እዚህ ድረስ ነበርና ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ወይም ጥቂት ቀደም ብሎ ይቀርብ የነበረው ፈንድ ተቋርጦ ነበር ማለት ነው። ያኔ የምእራቡን ጣጣ ፈርተውም ሆነ ከነሱው አብረው ጀርባ የሰጡን ሀገራት በአዲስ አበባ በሰልፍ እየመጡ ይገኛል። ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ አውሮፓ ሀገራትና አውሮፓ ህብረት አሁን ላይ አስገራሚ መመለስን ተመልሰዋል። ሰይፋቸውን መዘውብን የነበሩ አሁን አሁን ላይ ወደ ሰገባው የመለሱ አለማቀፍ ድርጀቶቿ ወደ ነባሩ ግንኙነት ተመልሰዋል። የc2fc እና የባንዳዎች ተልእኮም እዚህ ላይ ያከትማል።
ጤዛ ጤዛ ነው አረም አረም ነው ወዲያውኑ ይጠፋል። ያሳደረው ጠባሳ ግን በታሪክ ተሰንዶ ይዘልቃል።
በዬዘመኑ የሚፈጠር የውስጥና የውጪ ሽኩቻ ይኖራል። መልኩ እንደ ጉዳዩ እና እንደ ወቅቱ ተጨባጭ ይለያያል። ፕሮፓጋንዳውም በተመሳሳይ መልኩን አጣጥሞ ይመጣል። ለዚህ ቻሌንጅ ለመዘጋጀት የቅርቡ ጊዜ ጣጣ መግፍኤ ይሆነናል። ምእራባዊያን መሰል ዘመቻዎችን እንደ ቻይና ቱርክ እና ራሺያ ባሉ አገራት ላይም ሲተግብሩት ማየታችን ደግሞ እንደ ሀገር መዋቅራዊ አሰራር እንደሚጠይቀን ያስገነዝበናል።
Esleman Abay
#የዓባይልጅ

ኢትዮጵያዊ ድምፆችን ለማፈን የተደራጀ ዓለም አቀፍ ፕሮጀክት ~ Esleman Abayየአገር መከላከያ ሰራዊትን…

Posted by Esleman Abay on Tuesday, August 10, 2021

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories