አል-ፋሻጋ የካይሮ ጨዋታ ሜዳ ?

Egyptian proxy against ethiopia

By, Esleman Abay

ኢትዮ ሱዳኑ አል ፋሻጋ መሬት ሰሞነኛው ጉዳይ ነበር። መሬቱ ሰፊ ነው። 600 ፌዳን የተዘረጋ። ላለፉት 25 ዓመታት በኢትዮጵያ ስር ሆኖ ሱዳኖች እየተከራዩም ያርሱበት ነበር ተብሏል። ከቀናት በፊት ደግሞ ሱዳኖች በቁጥጥር ያዋሉት የህወሃት ሰው ነበር። በዚሁ መሬት ከፍተኛው ከበርቴ ነበር። ሃይል ያደራጀ መሬቱን የሚያሳርስ የሚያከራይ አዛዥ ናዛዥ፤ ሱዳኖች 900 ቢሊዮን የሱዳን ፓውንድና በርካታ ወርቅ ከሰውየው ኤግዚቢት አድርገዋል።

…. ስለ አል ፋሻጋ መሬት እነዚህን መረጃዎች ታሳቢ እናድርግና ነገሮን ከነገሮች አስተሳስረን ብንመለከትስ? የቀረው ፌደራል መንግስትን የሚመለከት ነውና መረጃ እስከሚሰጥበት መጠበቅ ግድ ይለናል ……


  • ክስተቱን ትኩረት እንዲሰጠው የሚያደርገው መሬቱን የሱዳን ሃይሎች መያዝ የመጀመራቸው መረጃ የተሰማው ሁለት ሰሞናዊ ነገሮችን ተከትሎ መሆኑ ነው። የውስጥ ጦርነት ላይ መሆናችን አንዱ ነው። ሁለተኛው የሱዳንና ግብፅ አየር ሃይል የጋራ ልምምድ ማድረጋቸውን ተከትሎ። የልምምዱ አላማ “ድንበርን በጋራ መጠበቅ” የሚል ነበር። እንዴት ሆኖ ነው ድንበር በልዩ ትኩረት በአየር ሃይል?” የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነበር። ጉዳዩ ከህዳሴ ግድቡ እንደሚያያዝ ከኢትዮጵያውያን ባሻገር አለማቀፍ ትንተናም ተደርጎበታል።
    ግብፅ ከትራምፕ ስንብት በፊት ኢትዮጵያ ትፈርም ዘንድ የፈጠረችው የጫና መላ መሆኑንም ነው አብዛኞቹን ያሳመነው ድምዳሜ።
    በዚህ አተያይ ከሆነ፣ ልምምዱን ተከትሎ የኢትዮ ሱዳን የድምበር ነገር ሆኖ መምጣቱ ታዲያ ካይሮ የሱዳንን ፍላጎት ከዘመቻ ህወሃት ጋር ቀምራ ያቀረበችው ካርታ ሊሆንም ይችላል።

የአልፋሻጋ መሬት አወዛጋቢ ጉዳይ ከጥንት ከጠዋቱ የተጠነሰሰው በእንግሊዝ እጅ ነው ይባላል። አወዛጋቢነቱም ከዚህ ይመነጫል። እንግሊዝ ካለች ካይሮን መጠርጠራችን የዋህ አያስብለንም።

ወደ ኋላ ስንመለከት

አገራችን አድዋ ላይ የተቀዳጀችው ድል በምዕራቦቹ የተያዘባት ዘላቂ ቂም በመሰል ወቅቶች የሚያወራርዱት ነበር ነበር። ነገርሮች እንደበፊቱ ቢሆኑ ማለቴ ነው። ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ የአለም ኋይል አሰላለፍ በአሜሪካ ከሚመራው Unipoalr አሰላለፍ ተገለባብጦ ጉልበት የብዝሃ መንግስታት ሆኗል። አዲሱ Multi-Polar የሃይል አሰላለፍ ምስራቅ አፍሪካ ላይ ተማክሏል። የጎንዮሽ ስጋቱ ላይ በደምብ ከሰራንበት በርካታ ዕድል ያመጣልንም እየሆነ ነው። እንደ ድሮው ቢሆንማ ምዕራቦቹ ያቀዱልን ብዙ ነበር።

የአድዋ ድልን ተከትሎ በነበሩት ጥቂት ቀናት በተለይም ከ March 5, 1896 ጀምሮ ጋዜጦቻቸው በኢትዮጵያ የተቋጠረውን ቂም ማስነበብ ጀምረው ነበር። ለአብነትም Cape Argus የተባለው ጋዜጣ “አውሮፓውያኑና ጣልያን ማንኛውንም ዋጋ ከፍለው የኢትዮጵያና የሚኒሊክን ስነ ልቡና ሰብሮ ከአፍሪካ የሚያስወግድ ፖሊሲ ሊቀርፁ ይገባል” ነው ያለው። Times of London ለተባለ ጋዜጣ የሚሰራ ጋዜጠኛ የዘገበው ደግሞ “አቢሲኒያዎቹ ወደፊት እንዲሳካላቸው አንፈልግም። ድፍን አፍሪካን አነሳስተው ስልጡን አውሮፖዎች ላይ ኪሳራ አድርሰዋልና” ብሎ ነበር።

አካሄዳችን Long Term ጥቅማችንን ታሳቢ አድርጎ በመለኛ አካሄድ ማዝገም ያለበት ይመስለኛል። ካይሮ በግድቡ አሁናዊ ድርድር ላይ የቀራት የጫና ካርድ ያለቀ ይመስለኛል። ጩጨዋን ደቡብ ሱዳንን ምን ላርግልሽ የምትለውም ለዚህ ነው። አጋሯ ትራምፕ እየሄደባት ነው። ከህወሃት ጋር የነበረው አተካራ ትልቅ ተስፋዋ ነበር። “የኢትዮጵያ መንግስት ህወሃትን ድል ቢያደርግም በቀጣይ የሚፈጠሩ ችግሮች ይኖራሉ” የሚለው የነ Al Ahram እና Egypt Independent ማስተዛዘኛ ሆናለች። የተባበሩት አረብ ኢምሬት ለኢትዮጵያ መንግስት እወግናለሁ ብላታለች። ቱርክን በመቃረን አብራት የነበረች አገር በኢትዮጵያ ጉዳይ ግን የተለየ አቋምን መምረጧ ግብፅን አስደንግጧል። ቀጣይ ትብብራቸው ምን መልክ ይኖረው ይሆን የሚሉ ትንተናዎች በስፋት ሲቀርቡ ነበር።
በአንፃሩ አገራችን ባሳለፈቻቸው የዘመቻ ህወሃት ጊዜያት የሱዳን ጂቡቲ ሶማሊያ ዱባይ ቻይና ቱርክና ራሺያን ሲሪየስ ድጋፍ አሳክታለች። እነ ጀርመንና ሳዑዲም በወዳጅ ወዳጅ ወደኛው አዘንብለዋል።

ኢትዮጵያውያን መፍራት ካለብን አገራዊ አንድነትን የሚያዳክም የራሳችንን አስተሳሰብ ነው። እንደኔ በወቅቱ የጂኦ-ፖለቲካ ጨዋታ አገራችን ጥሩ ላይ ናት። የአል ፋሻዳ መሬት የግብፅ ጨዋታ ሜዳ እንዳይሆን የማድረግ ዕድል በእጃችን ናት ባይ ነኝ። አገራዊ አንድነታችንን ካስጠበቅን የማንሻገረው አይኖርም።
የዓባይ ልጅ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories