“አሸባሪው ሕወሓት አፋር ክልልን ሙሉ ለሙሉ ለቆ አልወጣም”፦ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን


“ኢትዮጵያ ከማንኛውም አካል ጋር በሰላምና በትብብር የመስራት ፅኑ አቋም አላትም”

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በኢትዮጵያ የአሜሪካን መንግስት ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

“ሕወሓት መንግስት ለትግራይ ህዝብ በማሰብ የሰጠውን የሰላም አማራጮች ሳይጠቀምበት ቀርቷል፤ ይልቁንም ግጭቱን ወደ አፋርና አማራ ክልሎች በማስፋፋቱ ተጨማሪ ጉዳት አድርሷል” ብለዋል አምባሳደር ሬድዋን።

“የሕወሓት ኃይል በአፋር ክልል ከያዛቸው አንዳንድ አካባቢዎች እየወጣ ቢሆንም በክልሉ ከሚገኙ ሌሎች ስፍራዎች ለቆ አልወጣም” ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ከማንኛውም አካል ጋር በሰላምና በትብብር የመስራት ፅኑ አቋም እንዳላትና ለኢትዮጵያም ይሄን የሚመጥን ምላሽ “ሌላኛው ወገን” ማሳየት እንዳለበት አመልክተዋል።

መንግስት በትግራይ ክልል ተፈጽሟል ስለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በራሱና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ ጋር በመሆን ባደረገው የጋራ ምርመራ በጉዳዩ ላይ ተሳትፎ አድርገዋል የተባሉ አካላትን በሕግ ተጠያቂ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

“ይሁንና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሕወሓት በአማራና አፋር ክልሎች የፈፀማቸውን አሰቃቂ ወንጀሎች በመሸፋፈን አድሏዊ አካሄድ ሲከተል ነበር” ብለዋል አምባሳደሩ።

መንግስት በትግራይ ለሚኖሩ ዜጎች የምግብና የመድሐኒት አቅርቦት በተገቢው መልኩ እንዲደርስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሆነና ድጋፉም በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ጽኑ ፍላጎት እንዳለው አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ የአሜሪካን መንግስት ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን በበኩላቸው አሜሪካን ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን ፈተናዎች በሰላማዊ መንገድ እንድትፈታ ማንኛውንም ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል።

የኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግኑኝነት ዳግም ወደ ተሻለ ደረጃ እያደገ መጥቷል ያሉት አምባሳደሯ ግንኙነቱ ወደ ነበረበት እንዲመለስ ጠንካራ ስራ እንደሚሰሩ አመልክተዋል።

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories