
እስሌማን ፡ ዓባይ ✍️
“..ከሉዓላዊው የኢትዮጵያ መንግስት አሊያም ከህወሃት..”
“ኢትዮጵያ ከአየርላንድ የነበራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት ታሪክ ከግምት ስናስገባው በዚህ ደረጃ ለከት-የለሽ ፀረ-ኢትዮጵያ ድርጊት ከአየርላንድ ልንጠብቅ አንችልም።” ይላል ይፋ ያልተደረገውና ከእጄ የገባው የአቶ ደመቀ ደብዳቤ በመክፈቻው።
“አይን ያወጣው የአየርላንድ ህዋሃታዊ አካሄድ፣ ሊታረም ያልቻለው የዲፕሎማሲ ጫና እና የሴራ አራማጅነት ከዚህ ወዲያ ኢትዮጵያ ልትታገሰው እንደማትችል..” የኢፌድሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዱብልን በፃፈው ደብዳቤ ተሰምሮበታል። ደብዳቤው አየርላንድ ከአዲስአበባ ጋር መቀጠል አለመቀጠሏን ለመጨረሻ ጊዜ እንድትወስን “Deal or Not Deal” ሲል የሚያስጠነቅቅ ሲሆን ዋነኛ ነጥቦች ያልኳቸውን መራርጫቸዋለሁ።
በኦክቶበር 11 በውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ በአቶ ደመቀ መኮንን ፊርማ ወጪ የሆነው ደብዳቤው፣ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ጎህ መታየት ከጀመረበት የፈረንጆቹ 2018 ጀምሮ ክፋትና ሴራ ሲያውጠነጥን የቆየው ህወሃት፣ በትግራይ ክልል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን በማፈንና እንደ ፖለቲካዊ መያዣ ሲጠቀም ቆይቶ፤ November 23 2021 ላይ በኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ላይ የከፋ ክህደታዊ ጥቃት ስለመጀመሩ ዓለም የሚያውቀው ነው” ሲል ያወሳል። ቀዉሱን የማስተካከል ስራዎች ቢጀመሩም ህወሃት ሌላ ወረራ በድጋሚ ከፍቷል። ይህም ኢትዮጵያ ላስተናገደችው ቀውስ ሁሉ መነሾ ነበር።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሰት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ተቀብሏል። ለተግባራዊነቱም ቁርጠኛ ነው። የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይም ምርመራ ይደረግ ዘንድ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።
አካታች የሆነ ብሔራዊ የእርቅ ውይይት ለሀገሪቱ የሚያመጣውን በጎ ውጤት በመገንዘብ ለዚሁ በተቋቋመው ኮሚሽን በኩል ስራዎች ተጀምረዋል። ይህም ኢትዮጵያ ቀጣይ ቅጭትን መከላከል የሚያስችል መሰረት ይሆን ዘንድ ታሳቢ የተደረገለት ነው።
ይህን ጅምር የአየርላንድ መንግስት ሊደግፈው ሲገባ በተቃራኒው ኢትዮጵያን ማጥቃት እምደመረጠ ነው የቀጠለው። አየርላንድ በፀጥታው ምክርቤት፣ በአውሮፓ ህብረት ያላትን አባልነቷን በመጠቀም ኢትዮጵያን ለመበደልና ለመጉዳት ያለ የሌለ አቅሟን ስትጠቀም ቀጥላለች።
በአቶ ደመቀ ደብዳቤ ላይ የሰፈረው ሌላ አስገራሚ ነገር “አውሮፓ ህብረት እክል የገጠመውን የኢትዮጵያ ግንኙነቱን ለመመለስ ስራዎች በተጀመሩበት ወቅት አየርላንድ ጅምሩን ለማደናቀፍ ብዙ አክሎች ስትፈጥር ነበር ብሏል።
ከአውሮፓ ህብረት ወደ ኢትዮጵያ ጉብኝት የሚያደርጉ ቡድኖች በግል ይለግሱን የነበረው ተደጋጋሚ ምክርም”ከአውሮፓ ያላችሁን ወዳጅነት ለማስተካከል ከአየርላንድ ጋር ባላልሁ ግንኙነት ላይ አጥር ማበጀት አለባችሁ የሚል ነበር።” በማለት ተገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት አሁን ከአየርላንድ የሚኖረው ግንኙነት ወደ ተገቢው መስመር ይመጣ ዘንድ ፈቃዱ መሆኑን የገለፀው የአቶ ደመቀ ደብዳቤ “አየርላንድ የስከዛሬውን በደል አቁማ የመከባበር መርሆች ላይ የተመሰረ ግንኙነት እንዲኖረን ተግባራዊ ርምጃ እንድንጠብቅ ተገድደናል።” ብሏል።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዱብልን ተገቢውን ምላሽ እንደሚጠብቅ በመግለፅ ባሰፈረው ማሳሰቢያ “ኢትዮጵያ ላቀረበችው ጥያቄ አየርላንድ የምትሰጠን ምላሽ የሁለቱን ሀገራት የግንኙነት እጣ ፋንታ የሚወስን ይሆናል” ሲል አስምሮበታል።
#ወዲዓባይ #የዓባይልጅ Esleman Abay
ደብዳቤውን ሊንኩ በመክፈት ያግኙት ?