የአውሮፓ ህብረት በዘር ማጥፋት ተጠያቂ ለሆነው የጃንጃዊድ ሚሊሻ የገንዘብና ስልጠና ድጋፍ በማድረጉ በአለማቀፍ ቋማት ሲጋለጥ ቆይቷል። ከብዙ ሪፖርቶች በጥቂቱ፣ ሪሊፍ ዌብ ኢንተርናሽናል “Border Control from Hell” በሚል የጥናት ሪፖርቱ እንዲሁም ዘ ኒው ሂውማኒቴሪያን “Inside the EU’s flawed $200 million migration deal with Sudan” በሚል 2017 እና 2018 ይፋ የተደረጉ መረጃዎች የሚያሳዩትም አውሮፓ ህብረት ወንጀለኛውን ቡድን በማፈርጠም የሰብዓዊ መብት በሰፊው እንዲጣስ ቤንዚን አበርክቷል የሚሉ ናቸው።
በሂደት rapid support force የሚል ስያሜ የተሰጠውና በሔሜቲ የሚመራው ሚሊሻ በድንበር ጥበቃና ስደተኞችን እንዲቆጣጠር ነው ድጋፍ ሲደረግለት የቆየው። በዋናነትም ወደ አውሮፓ የሚደረግ ስደትን ለማስቆም በማሰብ። ከሶማሊያ ኤርትራና ኢትዮጵያ ተነስተው በሱዳን በኩል የሚጓዙ ስደተኞችን በተለየ ለመቆጣጠር። ህብረቱ ከ 2016 ጀምሮ ከ 200 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ገንዘብ ለሚሊሻው አበርክቷል።
የስለላ ፍተሻና የማንነት መመዝገቢያ ቴክኖሎጂዎችንም አበርክቷል። ይሁንና መሳሪያዎቹ ሱዳናዊያንን ለመሰለልና መብታቸውን ለመጋፋት መዋላቸው ነው በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የተጋለጠው። ገንዘቡም ከታለመለት አላማ ውጪ ሚሊሻው ከሱዳን ገዢዎች ጋር ተመሳጥሮ ተቃውሞዎችን ለማፈንና ታጣቂዎች በዜጎች ላይ ለሚፈፅሙት ወንጀል ሲበጅቱት ነበር።
አለማቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች የህብረቱ ብልሹ ድጋፍ እንዲቆምና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ቢጠይቁም ማስተካከያ አልተደረገም። በአንድ ወቅት ገለልተኛ የምርመራ ቡድን ወደ ሱዳን አምርቶ ለማጣራት ቢሞክርም ምቹ ሁኔታ ማግኘት አልቻለም ነበር። የታጣቂው ቡድን ሃይሎችና ከጀርባ ከሚደግፋቸው የወቅቱ የአል በሽር ባለስልጣናት መርማሪውን ቡድን እየመሩ በተፈቀደላቸው ቦታ ብቻ ምልከታ እንዲያደርጉ ገድበዋቸዋል። በዚህ ሁኔታ ውስጥም አውሮፓ ህብረት ድጋፉን አለማቋረጡ የመብት ተሟጋቾችን አስገርሞ ነበር።
በዳርፉር 400 ሺ የሚደርሱ ንፁሃንን የጨፈጨፈው የጃንጃዊድ ሚሊሻ የአገሪቱን የጦር ምክክር ቤት ከአል ቡርሃን ጋር እንዲረከብ ሲደረግ ህብረቱ ተቃውሞ አለማሰማቱ በበርካታ ድርጅቶች ተተችቷል።
የአውሮፓ ህብረት ከሰሞኑ ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን የ 88 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አዘገያለሁ ማለቱ ለኛ እጅጉን ያስገረመ ሆኗል።
Esleman Abay , የዓባይ ልጅ