
በሃያ አመቱ የጥፋት ዘመን ውስጥ 47,600 ንፁህ አፍጋናዊያን ተገድለዋል። የህፃናትና ሴት ሟቾች አሀዝ ደግሞ እስከ 40 በመቶውን እንደሚይዝ ተዘግቧል። ባለፉት 5 አመታት ብቻ 1,600 ህፃናት በአሜሪካ መራሹ የአየር ድብደባ ተገድለዋል። ላለፉት 14 ዓመታትም በእያንዳንዷ ቀን 5 ህፃናት በዚሁ ድብደባ ሲሞቱ መቆየታቸውን የጥናት ተቋማት ይፋ አድርገዋል።
Watson org. UN, Afgan state data
~ ቁጥሮች ስለ አሜሪካ መራሹ ዘመነ-ጥፋት ~
አሜሪካ የአገረ አፍጋኒስታን ወረራዋን የጀመረችው ከ sept. 11 2001 ማግስት octo. 7, 2001 ጀምራ ነበር። ዋሽንግተን ለ 20 አመታት የቆየችበትን የአፍጋን ወረራዋን እስካቆመችበት ያሳለፍነው ሳምንት ድረስ ከ 1 ትሪሊዮን ዶላር በላር ፈጅታለች። ፕሬዝደንት ባይደን በይፋ እንደገለፁት። 20 ሺ የአሜሪካ ወታደሮች አካል ጉዳተኛ ሆነዋል። 2,400 ወታደሮቿም ተገድለዋል።
አሜሪካና 38 የኔቶ አባል አገራት የተውጣጡ እልፍ ወታደሮች በአፍጋኒስታን አሰማርተዋል። የአሜሪካ ኮታ ደግሞ ከፍተኛው ነው። በኦባማ ዘመነ ስልጣን የፔንታጎን መረጃዎች እንደሚያሳዩት 2011 እኤአ 98,000 አሜሪካዊ ወታደሮች በአፍጋን ምድር ነበሩ።
አሜሪካ መራሹ ጦር በአፍጋን የገደላቸው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተፋላሚዎች፣ ያወደመው ንብረት፣ ያስከተለው የኢኮኖሚ ድቀት፣ ያፈናቀለው በሚሊዮን የሚቆጠር የአፍጋን ዜጋ ነገር በታሪክ በጥቁር ማህደር ተመዝግቧል።
በሃያ አመቱ የጥፋት ዘመን ውስጥ 47,600 ንፁህ አፍጋናዊያን ተገድለዋል። የህፃናትና ሴት ሟቾች አሀዝ ደግሞ እስከ 40 በመቶውን እንደሚይዝ ተዘግቧል። ባለፉት 5 አመታት ብቻ 1,600 ህፃናት በአሜሪካ መራሹ የአየር ድብደባ ተገድለዋል። ላለፉት 14 ዓመታትም በእያንዳንዷ ቀን 5 ህፃናት በዚሁ ድብደባ ሲሞቱ መቆየታቸውን የጥናት ተቋማት ይፋ አድርገዋል።
ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል አሜሪካ በኢራቅ ሶሪያና አፍጋኒስታን ባደረገችው ዘመቻ ከ 2001 እስካሁን ባሉት ሃያ አመታት ከ 6.4 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ወጪ አድርጋ፤ በሌላ መልኩ ሲገለፅም ይህንን ግዙፍ ሐብት ለመሳሪያ ፋብሪካዎችና ወታደራዊ ተቋማት እንዲሁም ለመልሶ ገንቢ የምዕራብ ኩባንያዎች በተዘዋዋሪ መንገድ ገቢ አድርጋላቸዋለች።
በነዚህ አሜሪካ ሰራሽ 20 የመከራ አመታት ውስጥ ለአገረ አፍጋን ያበረከትነው ነገር አለ ይላሉ፤ እነ ግፍ አይፈሬ። ይኸውም አሁን ላይ 4 ሚሊዮን የአፍጋን ሴት ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ እንዲሆኑ፣ ከ 20 አመት በፊት ከነበረው 3,000 ት.ቤት በተጨማሪ 15,000 ት.ቤቶች እንዲገነቡ ሆኗል፤ 68 ሴት አፍጋናዊያን የአገሪቱ ፓርላማ አባል እንዲሆኑ ደግፈናል ብለዋል። ይኸው ነው…።
አሁን ላይ አገሪቱን እየጠቀለለ የሚገኘው ታሊባን ከምዕራባዊያን በአስተርጓሚነትና በተለያዩ ሚናዎች ላይ ሲሰሩ የነበሩ የአፍጋን ልጅ እና አዋቂዎችን እየገደለና እያገለለ ይገኛል ሲሉ ምዕራቦቹ ይናገራሉ። ስጋት ያየለባቸው የአፍጋን ዜጎች ከታሊባን ወይም ከመንግስታቸው አሊያም ከአሜሪካ ያገኙት ከለላ የለም፤ አገራቸውን ጥለው ለመሰደድ እስካሁን ድረስ ብቻ 18,00 የሚደርሱት ቪዛ አዘጋጅተው ለስደት ተሰናድተው ይጠባበቃሉንጂ።
የዋሽንግተንን መንግስት ለታሊባን ጥቃት አጋልጣችሁን ጠፋችሁ ለሚለው የአፍጋን መንግስት ተደጋጋሚ ጥያቄ ፕሬዝደንት ባይደን የሰጡት አጭር ምላሽ የሚከተለው ነበር፦
“አገራችሁን መጠበቅ፤ አፍጋኒስታንን መከላከል የናንተው የራሳችሁ ኃላፊነት ነው!”