ግድቡ በጉባ ይሠራ ዘንድ የአሜሪካው “United States Bureau of Reclamation” የተባለው ኩባንያ ቦታውን መረጠ። የፕሮጀክቱ ጥናትም 1952 ነው ተጠንቶ የቀረበው። ቦታውን በመለየት የተሳተፈው የያኔው የ 27 ዓመቱ ጣልያናዊ ሰርቬየር አሁን ላይም በሳሊኒ በኩል ከግምባር ቀደም ኢንጂነሮች መካከል ሆኖ በግምባታው ላይ እየሠራ ነው የሚገኘው።
በወቅቱ አፄ ኃይለስላሴ ለግድቡ ፕሮጀክት ጥናት 10 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ አድርገዋል። ከ IMF ጋር መልካም ግንኙነት ስለነበረንም ለግድቡ ማስጀመሪያ 130 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦልንም ነበር፡፡
ከ1930ዎቹ ጀምሮ ወዳጆች የነበሩት ኢትዮጵያና አሜሪካ እስራኤል 1941 ላይ እንደ አገር ከተመሠረተች በኋላ ደግሞ ግንኙነቱ ይበልጥ ተጠናክሮ ነበረሰ፡፡ 1946 ላይ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ “ታላቅ ወታደራዊ የትብብር ስምምነት” አድርገዋለሰ፡፡ በዚህም አሜሪካ የኢትዮጵያን አየር ክልል፣ የባህር ኃይል፣ ወደብና የራዲዮ ጣብያዎችን መጠቀም የሚፈቅድላት ነበር፡፡
አፄ ኃይለስላሴም ግድቡን ለማሰራት እየተዘጋጁ ባለበት ወቅት ነገሮች ተለወጡ፡፡ የታህሳሱ ግርግር ! ወይም ደግሞ የ 1953ቱ መፈንቅለ መንግሥት ተከሰተ፡፡ ከግርግሩ ጀርባም የግብፅ እጅ በረጅሙ ስለመኖሩና በዓባይ ላይ ሊሰራ ታስቦ ለነበረው ግድብ መቋረጥ አይነተኛ ምክንያት እንደ ነበረ በርካታ ፀሀፍት ገልፀውታል፡፡ ንጉሱም ለዙፋናቸው በመስጋት ግድቡን ስለማቋረጣቸው ይታመናል፡፡
ግብፅ በዚህ ደረጃ ተፅዕኖዋ የበረታው ንጉሱ የተጠቀሙትን ካርታ እንደ አዲስ በመጫወቷ ነበር። ሲጀመርም የግድቡን ጥናት አሜሪካ አጠናቃና ፈቅዳ እንዲሁም አይ.ኤም.ኤፍም በገንዘብ እንዲረዳን ያደረገችው በእስራኤል ጉዳይ ላይ ግብፅ ተፃራሪ የነበረች መሆኗና ኢትዮጵያ ደግሞ ከአሜሪካም ከእስራኤልም ወዳጅ መሆኗ ነበር። ይሁንና “እስራኤል” ለምትባል አገር በተባበሩት መንግሥታት ጉባኤ እውቅና በሰጠበት ማግስት ውሳኔውን በርካታ ሃገራት አልተቀበሉትም ነበር። ከተቃወሙት ውስጥ ታዲያ ያልተጠበቀው የሀይለስላሴ አቋም ነበር፡፡ አፄ ኃይለስላሴ የዘር ሃረጋቸውን ከእስራኤል ይመዘዛል ባይ ቢሆኑም በፍልስጤሞች ላይ እንዲህ ያለው በደል መፈፀሙን ባለመቀበላቸው በተመድ ጉባኤ ላይ እስራኤል ሌሎች ህዝቦችን በማፈናቀል መመሥረት እንደሌለባት ሞገቱ፡፡ ተቃወሙም። ግብፅ ከሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጋር ውሳኔውን ባይቀበሉትም የንጉሱም መጨመር ግን ለአሜሪካና እስራኤል በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸው ነበር።
ቅር በተሰኙት አሜሪካና እስራኤል ችላ ካሉት የንጉሱ ስልጣን ጋር ለኢትዮጵያ የደህንነት ከለላቸውን ከፈት ማድረጋቸው
ገማል አብደል ናስር ንጉሱን በመፈንቅለ መንግስት ከማሳት ሴራ ባለፈም ኢትዮጵያ ተረጋግታ ግድቡን እንዳትሰራ በኤርትራና ኦጋዴን የመገንጠል ጥያቄ ያነሱ ኃይሎችን በማስታጠቅ ንጉሡን ማስጨነቅ እንዲችል ዕድል ፈጥሮለት ነበር። ግድቡም የንጉሱ ውጥን ሆነ ሊቀር ቻለ።
ያቀርብኩት ማሳያ “ግድቡን ከአገር ውስጥ ሴረኞች በስተቀር የትኛውም ኃይል አያስቆመውም” ላልኩት ሀሳብ ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ ነው። ከሰሞኑ የምናየው ያልተገባ ዘመቻም ለመሰል ሴራ እንዳያጋልጠን እንጠንቀቅ።
[ ሀሳባችሁን አካፍሉኝ፤ በቀጣይ ደግሞ በደርግ ዘመን ግድቡ እንዳይገነባ የነበረውን ሁኔታ አካፍላችኋለሁ ]