አፍሪካ የምዕራባዊያን እብሪት በታሪካዊ ትግል ተመቶ የሚቀበርባት ምድር ትሆናለች: ማዖ ዚዶንግ

Africa would become the battlefield where the power of the West could be destroyed and the world revolution could be started, and that China, would be the leader of this historical struggle Mao Zedong
  በእስሌማን ዓባይ ✍️ #የዓባይልጅ 

“Africa would become the battlefield where the power of the West could be destroyed and the world revolution could be started, and that China, would be the leader of this historical struggle” – Mao Zedong

ቻይና፣ የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ድል ነስታለች፤ ከድል በዓሏ ጋር መፃኢ ስትራቴጂዋን በራሷ የጥሞና ጥበብ እያዋዛች ትነድፍ ጀምራለች፤ ወቅቱ በ 1960ዎቹ መጀመሪያ..። ይህ ወቅት በአሜሪካ ሰራሹ የጃፓን ኢምፔሪያሊዝም 20 አመታት ወደኃላ ላይ የደረሰባት የወረራና ጭፍጨፋ ጥባሳ ገና አልሻረላትም ነበር። ቻይናዊያን በወቅቱ፣ “ስታድጉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ?” ሲባሉ “ጃፓናዊ መሆን” ይሉ ነበር ተብሎ ይሾፍባቸውም ነበር ይባላል።

የዘመናዊነት አባቷ ማኦ ዚ ዶንግ፣ ይህን ፈለግ ባገናዘበ ጉዞ ቻይናን እየመሩ ነው። ራእያቸው ደግሞ ለጃፓንም ሆነ ለአሜሪካ ጣልቃገባዊ እብሪት ማርከሻ የሆነች፣ በአንድነቷ የበረታች፤ በዘመናዊ ጦር የፈረጠመች፣ ሐብታምና ዳግም የማትደፈር ቻይናን መፍጠር…። “የአለም ህዝቦች ፀረ-ኢምፔሪያሊስት ትግል ያሸንፋል!” የማዖ ንግር ከመሬት የሚወድቅ የለውም ያስብላል፤ እየሆነ ያለውን ለታዘበ።
ቤይጂንግ፣ የራሷን እና የአለምን ታሪክ አጤነች፤ አለምን የሚያዳርስ የስልጣኔ ጎዳናዋን ቀየሰች። በዚህም የጭቆና ሰለባ የሆኑ ህዝቦች ጋር የተስማማ አካሄድ በአንድ ደንጋይ ሁለት ወፍ ሆኖ አገኘችው። አህጉረ አፍሪካን ደግሞ “ጨዋታ ቀያሪዋ ምድር” ስትል ከድምዳሜ ደረሰች። ጊዜው ደግሞ በሺ ዘጠኝ መቶ ስልሳዎቹ ከ 60 አመታት በፊት።

“አፍሪካ” አሉ ማዖ፣ “አፍሪካ የምዕራቡ ዓለም ኃያልነት ድል የሚደረግባት እና የዓለም አብዮት ጅማሮ የጦር አውድማ ትሆናለች” አሉ፤ ማዖ ቀጠሉ፤ “የፍልሚያ ሜዳውን በአፍሪካ ለሚያደርገው የወደፊቱ ታሪካዊ ትግል መሪ ቻይና እንደምትሆን እርግጠኛ ነኝ” ሲሉ ደመደሙ።

በዓለም አብዮት ውስጥ የመሪነት ቦታዋን ለማስከበር ቻይና በጦር መሣሪያ፣ በምግብ፣ መድኃኒት እና ሎሪዎች ድጋፍ ማድረግ ጀመረች። ናንጂንግ በሚሰኘው ወታደራዊ አካዳሚዋም ታላላቅ የሚባሉ ወታደራዊ ሥልጠናዎች የሽምቅ ውጊያ ኮርሶችን ድረስ መስጠት ጀመረች። እ.ኤ.አ. በ 1963 መገባደጃ ላይ Zhou Enlai ከቼን ዪ ጋር በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን ጎብኝተው አብዮቱን አስፋፉ።
በዚሁ ጊዜ ጀምሮ ቻይናዊያን ከጭቁን የጥቁርም ሆነ ቢጫ ቀለም ህዝቦች ጋር ከፖስተር እሰከ ፖለቲካዊ አውዶች ተሰናስሎ ይታይ ጀመረ።
ቻይና አፍሪካን መመልከት የጀመረችው የኮቪድ ወረርሽኙን ወይም ከቻይና-አሜሪካ የንግድ ጦርነት ወዲህ ተፀንሶ የተወለደ የትላንትና ክስተት አይደለም።
በአሁናዊ ገፅታው የቻይናን አካሄድ ባግባቡ ለተጠቀመበት የአፍሪካ ህዝብና መንግስት ድርብ አድቫንቴጅ የሚያስገኝ ነው። የቤይጂንግ የልዕለ ሃያልነት ጉዞ የአፍሪካን የበደል ታሪክ የሚያክም፤ የምዕራባዊያንን ዕብሪት የሚያስተነፍስ ስትራጂ በመሆኑ..። “..አሞራ እና አሞራ ሲጣለፉ ሙዳ ስጋ ይተፉ..” እንደሚባለው።

“ቻይና ነገም ከነገ ወዲያም እንዲህ በትሩፋት በተሞላው ፖሊሲዋ ብቻ ትቀጥላለች” ብሎ መተማመን “የዋህ” ከሚለውም በላይ ስም ቢያሰጥ አይገርምም። የነገውን ስለመመከት ማስላት የአፍሪካ መሪዎች እንጂ የቤይጂንግ ጣጣ አይሆንም። አፍሪካ የምትሻው ከቤይጂንግ አብዮት የሚገኘውን ትሩፋት አሟጠው የሚጠቀሙ ብልጥ መሪዎችን ብቻ አይደለም፤ የነገውንም የጎንዮሽ ጉዳት አሻግረው የሚመለከቱ ጥቋቁር ማኦ ዚዶንጎች ጭምር እንጂ..።

የኔ ግላዊ አቋም፣ አሜሪካን የምጠላበት ወይም ቻይናን የማወድስበት ግላዊ አጀንዳ ያራምድ ዘንድ ለህሊናየ አለመፍቀድ የሚል ነው። አንድ አፍሪካዊ ከግል ጥቅሙ ተነስቶ ከሆነ ቢፈልግ ከቻይና ካልሆነም ከምእራባዊያን ሊወግን ይችላል። በአሁናዊ ስትራቴጂ የቻይናን ጠቃሚነት ክዶ ወገኑን ለማጨናበር መሞከር አይበጅም፤ እንደውም ጎጂ ነው እላለሁ፤ #የዓባይልጅ እንደ ግለሰብ የሚያራምደው በዚህ የተቃኘውን እሳቤ ነው።

ማዖ ዚዶንግ፣ ከስልሳ አመታት በፊት “የአለም ህዝቦች ፀረ-ኢምፔሪያሊስት ትግል ያሸንፋል!” ያሉለት አብዮት ዛሬ እውን ሆኗል፤ አብዮቱ ለጣልቃ ገብነት ላለመንበርከክ በዬዘመኑ ሌላ አብዮትን እያሳካ በጠላት ሙሉ አይን የማይታይ አስፈሪነትን ጨብጠዋል። ያኔ አሜሪካ ሰራሽ ርእዮት የቁሳዊ ሀብት ባለፀጋ የነበሩት እነ ጃፓን ቻይናን በድለው ነበር። ቻይና በ Made in China አብዮት ዛሬ አውራ ሆናለች። ኮሪያ እና ጃፓን በተቃራኒው ሀብታም ግን ልፍስፍስ ሀገረ መንግስት የሚባሉ ሆነዋል። በአለም ፖለቲካ የአሜሪካን ቃልና አይምሮ አክብረው ካልሆነ በስተቀር ትንፍሽ አይሉም። ከአሜሪካ ቢኳረፉ ከዙሪያቸው የሚመጣባቸውን ጣጣ የማይመክቱ ስልቦች ሆነዋል ሲሉ በርካቶች የሚደመጡትም ለዚህ ነው።

“አፍሪካ የምዕራባዊያኑ ኃያልነት ለሚቀበርበት የዓለማቀፍ ትግል አብዮት ጅማሮ አውድማ ትሆናለች” ሲሉ ማዖ ከስድስት አስርት አመታት በፊት የደሰኮሩት በተጨባጭ መታየት ጀምሯል።
“ፀረ-ምዕራባዊው ዓለም አቀፍ ትግል አፍሪካን አውድማው ሲያደርግ ይህን ታሪካዊ ተጋድሎ ቻይና ትመራዋለች” ሲሉ ርግጠኛ የሆኑበት ንግር አሁን በምንመለከታቸው ድርጊትና ሁነቶች የተገለጠ ይመስላል።
“አፍሪካ እንዴት ልሁንልሽ?” በሚል ምዕራባዊያን የለቀቁት የቅምጥል ነጠላ ዜማ ቻይና-መራሹ ታሪካዊው አብዮት አፍሪካ ይካሄድ የመጀመሩ አንደኛው ማስረገጫ ይሆናል!
#thistimeforafrica
✍️ እስሌማን ዓባይ – የዓባይ፡ልጅ

Ethiopia Horn Of Africa pan africanism Belt and Road Initiative china Africa Esleman Abay Mao Zedong red book communism New World Order

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories