ኢትዮጵያዊት ናዝራዊት አበራ በሀገረ ቻይና በዕፅ ዝውውር እንድትከሰስ ያደረገች (ጓደኛዋ) ስምረት ካህሳይ አንተሀቡ

ውሳኔውን ያሳለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የካቲት 25/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት ነው። ስምረት በ15 ዓመት እስራትና በ1 መቶ ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት እንድትቀጣ ነው የተወሰነው። ስምረት ካህሳይ በአሁን ሰዓት #ተሰውራ እንደምትገኝ የተገለፀ ሲሆን ፍ/ቤት የኢሚግሬሽን ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጄንሲ ወደ ውጭ ሀገር ስትወጣ ወይም ሀገር ውስጥ ስትገባ ተከታትሎ በመድረስ ለፌደራል ፖሊስ አሳልፎ እንዲሰጥና የፌደራል ፖሊስ ተከሳሿን አፈላልጎ ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የፍትህ ሚኒስቴር ተከሳሽ ስምረት ያለችበትን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ከፍትህ ጎን በመቆም ለፌዴራል ፖሊስ ጥቆማ እንደያደርግ አሳስቧል።

ናዝናዊት ላይ የሆነው ምንድነው ?

ናዝራዊት አበራ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ ትምህርት ዘርፍ ምሩቅ ናት። ኮንትራክተር ነች። የኮንስትራክሽን እቃዎች ከተለያዩ ሃገራት በማስመጣት ትተዳደራለች።

ጓደኛዋ ስምረት ህዳር 2011 ወደ ሀገር ያስገባችውን 5 በሻምፖ እቃ የታሸገ ኮኬን ዕፅ ለናዝራዊት ወደ ቻይና አብረን እንሂድ ብላ በማግባባት ቪዛ እና የአየር ትኬት ካስጨረሰች በኋላ ታህሳስ 11/2011ዓ.ም ለናዝራዊት አበራ የሂውማን ሄር ማጠቢያ ነው ቻይና ውሰጅልኝ ብላ ከላከቻት በኋላ እሷ የአባቷን ሞት ምክንያት በማድረግ ትቀራለች፡፡

ናዝራዊት ቻይና ደርሳ አውሮፕላን ማረፊያ በተደረገባት ፍተሻ የያዘችው 5 ሻምፖ መሰል 5 ኪ.ግ የሚመዝን የኮኬን ዕፅ መሆኑ ተደርሶበት ለእስር ተዳርጋለች።

በዚህም ነው ስምረት ክስ ተመስርቶባት ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ በ15 ዓመት እስራትና በ1 መቶ ሺ ብር ገንዘብ ቅጣት እንድትቀጣ የተወሰነው።

የፍትህ ሚንስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው ናዝራዊት አበራ በቻይና ሀገር ያለአግባብ ከዕፅ ዝውውር ጋር በተያያዘ እንድትከሰስና ለእስራት እንድትዳረግ ያረገቻት ጓደኛዋ ላይ ስምረት ካህሳይ በመጀመሪያ የተጠረጠረችበትን ወንጀል ክዳ ተከራክራ የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጥፋተኝነቷን አረጋግጦ የቅጣት ውሳኔ ከመስጠቱ አስቀድማ ራሷን እንደሰወረች አስታውቋል።

በጓደኛዋ ላይ በፈጸመችው በደልና ወንጀል ተከሳ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ተከሳሽ የቀረበችው ስምረት “በዐቃቤ ህግ የተመሰረተብኝን ክስ ተረድቸዋለሁ በተመሰረተብኝ ክስ ግን ጥፋተኛ አይደለሁም ምክንያቱም ለጓደኛዬ ለናዝራዊት አበራ የሰጠኋት የኮኬን ዕፅ ሳይሆን የፀጉር መታጠቢያ ሻምፖ ነው በዚህም ጥፋተኛ አይደለሁም” ስትል የእምነት ክህደት ቃሏን ሰጥታ እንደነበር የፍትሕ ሚንስቴር መረጃ ያስረዳል።

ዐቃቤ ህግ በበኩሉ የተከሳሽን ጥፋተኝነት የሚያስረዱ 8 (ስምንት) የሰው፣ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከኢሜግሬሽን ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጄንሲ የተገኙ ዝርዝር የሰነድ ማስረጃዎችን በማቅረብ ያሰማ ሲሆን ይህ ስጋት የገባት ስምረት ካህሳይም የማስረጃውን ሁኔታ ጥፋተኝነቷን በጉልህ ማሳየቱን ስትረዳ የሚቀጥለውን ቀጠሮ በመፍራት ከቅጣት እንደማታመልጥ ሲገባት ለጊዜው እንደተሰወረች ሚንስቴሩ አስታውቋል።

በከሳሽ ዐቃቤ ህግና በተከሳሽ ስምረት ካህሳይ መካከል የተደረገውን ክርክር ሲያዳምጥ የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎትም ዐቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ እና ማስረጃ መሰረት ተከሳሽ ጥፋተኛ መሆኗ በበቂ ሁኔታ የተረጋገጠ በመሆኑ በተከሳሽ ስምረት ካህሳይ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ በመሰጠት የካቲት 25/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ በ15 ዓመት እስራትና በመቶ ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንድትቀጣ መወሰኑን የሚንስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የኢሚግሬሽን ዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጄንሲ ስምረት ካህሳይን ወደ ውጭ ሀገር ስትወጣ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ስትገባ ተከታትሎ በመድረስ ለፌደራል ፖሊስ አሳልፎ እንዲሰጥና የፌደራል ፖሊስም ተከሳሿን አፈላልጎ ለማረሚያ ቤት እንዲያስረክብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በመስጠት መዝገቡን እንደዘጋ የሚንስቴሩ መረጃ ይገልጻል።

ጓደኛዋን ያለአግባብ እንድትታሰር ያደረገችውና የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባት ስምረት ካህሳይ ያለችበትን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው በመጠቆም ከፍትህ ጎን እንዲቆም የጠየቀው የፍትሕ ሚንስቴር ፤ በቻይና በእስር ላይ የምትገኘውን ናዝራዊት አበራን እንዲሁም በሁለት የቻይና እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተላልፈው እንዲሰጡ ለቻይና መንግስት ጥያቄ ማቅረቡን ገልጿል።

በቻይና ለሞት ፍርድ የሚያበቁ ወንጀሎች

▪️ሃገርን መክዳት (Treason)
▪️ለመገንጠል ማሴር (Separatism)
▪️ስለላ(spying)(በተለይ ለጠላት ሃገር “ሃገርን” መሰለል)
▪️አስገድዶ መድፈር(Rape)
▪️ነፍስ ማጥፋት(Murder)
▪️የህዝብና የመንግስትን ንብረትን ማቃጠል (Arson)
▪️ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን መፈፀም(Human trafficking) እና
▪️አደንዛዥ እፅን ማዘዋወር (Drug trafficking)

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories