sputnic news ባለፈው ህዳር ላይ ነው ርክክቡ መፈፀሙን ዘግቦት የነበረው። ከሩሲያ ጋር በተደረጉ ዘርፈ ብዙ ስምምነቶች ነው Pantisar S1 ለኢትዮጵያ የተሠጠው። sputnic በራሺያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ጋርም ቆይታ ማድረጉ ይታወሳል። እሳቸውም “ኢትዮጵያ ከራሺያ ጋር የመሰረተችው ወታደራዊ ትብብር የተሳካና” በርካታ ሁለትዮሾች መፈረማቸውንም ገልፀዋል።
መሳሪያው አውርፕላኖችን ፣ የጦር ጀቶችን ፣ ሄሌኮፕተር፣ ከጦር ጀቶች ላይ የሚተኮሱ ቦምቦችን፣ ሚሳየሎችን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በፍጥነት ማውደም የሚችል የዘመነ የአየር መቃወሚያ ሲስተም መሆኑ ይታወቃል።
ይሁንና በጣም ውጤታማ የሚሆነው ሰው አልባ አይሮፕላኖችና ምድር ለምድር ተምዘግዝገው የሚመጡ የጠላት መሳሪያዎችን ማውደም ላይ ነው። ሶሪያ ላይ መሳሪያው በተግባር ተፈትኗል። እነሱ ያደረጉት pantasir s 1 ሲስተሙን ውድና አሜሪካንም የሚያስፈራት ከሆነው S 400 ጋር በማጣመር ነበር። patasir ሲስተሙ የምድር ለምድርና ድሮኖችን እንዲሁም S 400 ው የርቀት ተምዘግዛጊዎችን በማምከን ስኬታማ ነበሩ። በሶሪያ እንደተጠመደም በአንድ ሌሊት ከአሜሪካ ጦር መርከብ 127 tamhawk ሚሳይሎች ተተኩሰው ከ 95 በመቶዎቹን አየር ላይ ማምከን አስችሏል። ከዚህ መሳሪያ በኋላም ነው አሳድ የአየር ጥቃቱ ቀሎለት በወንበር ላይ የመቀጠሉ ተስፋ መለምለም የጀመረው።
patasir መሳሪያው ከ S 400 ወይም S 300 ጋር እንዲጣመር እየተሠራ እንደሆነ ያየሁት መረጃ አለ። የምስራቅ አፍሪካ የጋራ ጦርም S 400 የሚታጠቅ ስለመሆኑ መዘገቡ ይታወሳል።
via፦ Military watch magazine, Sputnik News, business insider
https://sputniknews.com/africa/202001271078148343-ethiopia-wants-to-modernise-army-in-cooperation-with-russia–ambassador/
https://www.google.com/amp/s/www.businessinsider.com/pantsir-s1-makes-russian-air-defenses-stronger-2018-2%3famp
https://militarywatchmagazine.com/article/ethiopia-strengthens-air-defences-with-high-end-russian-hardware-pantsir-combat-vehicles-and-more