ኢትዮጵያ የታጠቀችው ቻይና-ሰራሽ ኃያል መሳሪያ

#ENDF #EthioChina #PCL_181

✍️ Esleman Abay የዓባይ፡ልጅ

ቻይና ከአሜሪካ ብሎም ከመላው ምዕራባዊ ባላንጣዎቿ በተፋጠጠችባቸው ግምባሮች ያሰማራችው፤ በብዙ መለኪያዎችም የዓለማችን ቁጥር አንድ እያሉት የሚገኝ ‘ሐውዜር’ ነው። ከዘመናዊ መድፎች ‘Self Propelled Howitzer’ መድፎች ውስጥ ዝነኛ የነበረው ፈረንሳይ ሰራሹ ‘ቄሳር’ Caezar ነበር። በያዝነው አመት ግን ዝናውን ለቻይናው ሐውዜር መድፍ ለ PCL-181 በማስረከብ ላይ ይገኛል።
የቻይናው ነፃ አውጪ ጦር PLA, ናንሲ ፔሎሲ በታይፔ ያደረገችውን ጉብኝት ተከትሎ ታይዋንን ቀለበት ውስጥ ያስገባችበት፤ አስፈላጊ ሲሆንም ከአሜሪካ መንጋጋ ነጥቃ ወደ ነባር ግዛትነቷ ከመመለስ ባለፈ ወታደራዊ ልዕለ ኃያልነቷንም አለም ይመለከት ዘንድ ከደቀነቻቸው የጠበብቶቿ ውጤቶች መካከል ነው።
የቻይና ጦር (PLA) የእግረኛ ክፍሎቹን በተለይም የመድፈኛ ብርጌዶችን ብቃትና ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለ ሲሆን፣ ከአራት ወራት በፊት በወርሃ ነሀሴ 2022 ላይ የ77ኛው መድፈኛ ብርጌድን ታክቲካዊ አፈፃፀም ለማስረገጥ ይህንኑ መሳሪያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተኩስ ልምምድ አድርጋበታለች።

PCL-181 በቻይና በጭነት ተሽከርካሪ ላይ የተገጠመ፣ የግዙፍ ሕንፃ ወፍራም ኮለን ያህል የወፈረ (155mm) ተተኳሾችን የሚያስወነጭፍ፣ በቅልጥፍናው፣ በሚያካልለው ርቀት፣ ከመሰሎቹ ላይ ያልነበረ ከእይታ ውጭ ሆኖ አነፍናፊ ተተኳሽ የሚያምዘገዝግ፣ ከሳቴላይትና ዘመናዊ የኢላማ አመላካች ድርኖች ጋር አስተሳስረው የሚያዘምቱት መድፍ ነው።

PCL-181 የዘመቻ ጓዙን በራሱ ሸካፊ መድፍ ለእይታ ሲበቃ ሁለት አመቱ ሲሆን ቤይጂንግ 70ኛውን ብሄራዊ ቀኗን ስታከብር ነበር አደባባይ ላይ የገለጠችው። PCL-181 በዋነኛነት ከዝነኛው የፈረንሳይ መድፍ CAESAR ሲስተም ጋር ተመሳሳይነት አለው። ይሁንና ከፈረንሳዩ የተሻለ የሚያደርጉትን አቅሞች የተላበሰ ነው PCL-181..።

አውቶማቲክ የእሳት መቆጣጠሪያ ቴክኖ የተገጠመለት፤ በኦፕሬተሩ የዒላማ መረጃ ግብአትነት ተሽከርካሪው ላይ የተገጠመው ኮምፒዩተር የመድፉን የኢላማ አንግልና አቅጣጫ ያሰላል፤ ተተኳሹንም በራሱ አመቻችቶ ያስቀምጣል።
ከፈረንሣዩ ቄሳር – 155mm የመኪና ላይ መድፍ ጋር ከሚሻልበት አንደኛው ሲወዳደር የቻይናው መድፍ የተኩስ አቅጣጫ እንዳስፈላጊነቱ ሙሉ 360° መሆኑ ነው። የቻይናው PCL-181 በ 30 ዲግሪ ጠባብ አንግል ላይ በፊትና በግራ በኩል በካቢኑ እንዲሁም ከ 20 እስከ 70 ዲግሪ አንግሎች ውስጥ ከፍተኛ እና መለስተኛ ተተኳሾችን ወደ ኢላማው ለመተኮስ እንዲችል የሆነ ነው።

PCL-181 አስቸጋሪ መልክአ ምድር ላይ በቅልጥፍና ማለፍ ይችል ዘንደ ከፍ ያለ ብርታት የተላበሰ ጠንካራ 6X6 ተሽከርካሪ ላይ የተገጠመ ሲሆን መንገድ አልባ ለሆነ ጉዞውም ዲዛይን የተደረገለት ተሽከርካሪ ያለው ነው። በውስብስብ ገደላ ገደል ላይ ተጉዞ በታሰበበት ቦታ ለመገኘት 25 ቶን ሆኖ ቀለል ማለቱ ተጨማሪ አቅም ሆኖለታል። በቦታው ደርሶ ለተኩስ ዝግጁ ለማድረግ የሚወስድበት 3 ደቂቃ ብቻ ነው። እንዳስፈላጊነቱም Shaanxi Y-9 ታክቲካል አይሮፕላን ጭነው ሊወስዱት የተመቸ ጭምር ነው።
የረዥም ርቀት ባለቤት መሆን የቻለው PCL-18 መድፍ ከቻይናው 71ኛ ክፍለ ጦር የመድፈኛ ብርጌድ ጋር በቅርቡ ተጠምዶ አዳዲስ የተኩስ ቴክኒኮች ተግባራዊ የሆኑበት ሲሆን፣ በዚህም ከተለመደው ፊት ለፊት ከመሰለፍ በተለዬ ከእይታ ውጭ እና [ከተዘጋጉ ቦታዎች መሽጎ ረጂሙን የተኩስ ሪከርድ መያዝ ችሏል። የቻይና ጦር በነሐሴ 2022 በቻይና ባሕር የታይዋን ኢላማዎች ላይ ባደረገው ልምምድ ወቅት ይኸው PCL-181 መድፉ (ከነተሽከርካሪው) ከእይታ ውጭ በሆነ ምድር ላይ ርቆ ከግድብ ጀርባ ተጠምዶ የደሴት ላይ ኢላማዎችን በትክክል ለማሰስና በአንድ ተተኳሽ ብቻ መምታት ይችል ዘንድ አሰው አልባ አውሮፕላን (Drines- ጋር አቀናጅተውት ታይቷል። በዚህም PCL-181 ከድሮኑ በተቀበለው መረጃ ተመርኩዞ የተኩስ አቅጣጫውን በትክክል ማስላትና ሁሉንም ኢላማዎች አንድ ባንድ ሲደመስስ በቪዲዮ ታይቷል።
ተንቀሳቃሽ ኢላማዎችን ለመምታት በሌሎች ዘመናዊ መድፎች ካለባቸው ውስንነት በተለዬ ቻይናዊው PCL-181 መድፍ ይህን መፈፀም የሚያስችል ቴክኖሎጂን የያዘ ሆኗል። ለዚህም የተገጠመለት የጨረር አነፍናፊ ቴክኖሎጂ Laser sensor ከድሮን እና ከሳቴላይት ጋር ተቀናጅቶ የሚጠመድ ተደርጎ ነው የተሰራው።

ዘመነኛውን PCL-181 መድፍ ከባለቤቷ ቻይና በተጨማሪ በፓኪስታን ምድር የታየው ከወራት በፊት ሲሆን ሁለተኛው ሀገር የሆነችው የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች መታጠቁ የታወቀው በዛሬ ዕለት ይፋ ሲያደርግ ነው።

#የዓባይልጅ

ቪዲዮ ?
https://vm.tiktok.com/ZMYdy3XQc/
https://youtube.com/shorts/I2MRtBJCisQ?feature=share

#PLA #eslemanabay

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories