ኢቲዮ-ቴሌኮም እስካሁን ድረስ ስለ ስኬቱ የሚነግረን፤ ህብረተሰቡም ሲያደንቀው የሚስተዋለው በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ገቢ ማግኘቱን በመግለፅ ነው።
በአንፃሩ፣ ጠ/ሚ አብይ ባንድ ወቅት “ቴሌ ውጤታማ ሆነ የሚባለው የዜጎችን ኑሮ፣ የገበሬውን ምርታማነት፣ ግብይቱን፣ የመንግስትን አገልግሎት አሰጣጦችን፣ የዲጂታል የስራ እድል ወዘተ.. አውቶሜት አድርጎ ኑሮን ማሻሻልና የዜጎችን ስኬት ማቃለል ከቻለ ብቻ ነው” ማለታቸውን ልብ በሉ።
ልክ ነው። ኢቲዮ-ቴሌኮም በሞኖፖሊ በያዘው አገልግሎት 120 ሚሊዮን ዜጋ በሚኖርባት ሀገር ተጠቃሚውም አማራጭ ሳይኖረው አንድ ለናቱ ከሆነው ኩባንያ ደንበኛ በሆነባት ሀገር ላይ፣ ትርፍ እና የደምበኛ ቁጥር እንደ ስኬት በዬአመቱ ማቅረብ ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ ነው።
ጠቅላይ ምኒስትሩ በጠቀሱት የዘርፉ መለኪያ ኢትዮ ቴሌኮም ከአለም የያዘው ደረጃ ወደ መጨረሻ ላይ ነው የሚገኘው። ከስድስት ያልበለጡ ሀገራትን ነው የምንበልጠው። “ግሎባል ሬዲነስ ኢንዴክስ” ከ 120 ሀገራት አንፃር 2019 ላይ ያወጣውን ሪፖርት እንመልከት። የኢትዮ ቴሌኮም ደረጃ የሚከተለው ነው።
▪️መለኪያ ▪️ነጥብ ▪️ደረጃ
- በኢንተኔት ግብይት… …………….. 0 115
- ከዘመኑ ዲጅታል አሰራር መጣጣም.. 31 94
- የዜጎች ዲጂታል ተሳትፎ ………. 51 91
- የዜጎችን ሶሺዮ ኢኮኖሚያዊ gap … 19 115
- ዌብሳይት ያላቸው ድርጅቶች ….. 21 92
- ዲጂታል ክፍያ ………….. 50 95
- የኢንተርኔት ተጠቃሚ ከማድረግ …. – – 113
9, የሞባይል ብሮድባንድ ተጠቃሚ…. 4.86 115 - (ሀገራዊ ይዘት በኢንተርኔት፣
Local content፡
eg; የቢዝነስ-ቱሪዝም መስኮችን
ለአለም ተደራሽ ማድረግ ——– 24 102 - Use of virtual social networks 2.9 111
- E-commerce legislation…….. 50 100
- ICT regulatory
environment……. 20 119 - Secured internet service ………….. o 115
በአጠቃላይም እነ የመንን የመሳሰሉ ሀገራትን ስንበልጥ ሶማሊያን አይነቶቹ በብዙ መለኪያ ወደ ላይ ተቀምጠው ይገኛሉ።
Source , Global readiness Index – 2019 👇
https://www.google.com/url?sa=t&source=web&rct=j&url=https://www.cisco.com/c/m/en_us/about/corporate-social-responsibility/research-resources/digital-readiness-index.html&ved=2ahUKEwiM0_DkmOz6AhVPXvEDHRLWCH8QFnoECAkQAQ&usg=AOvVaw1r7F8sqcJJfWtAtoPNcOED