
ሁሉም ቢሸነፍም ቀድሞ የሚሸነፈው ማን ይሆናል ?!!
አለማችን አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ነች !!!!
(ወንድወሰን ሰይፉ ቅድስ )
ባልተለመደ መንገድ ስድስት የአቶሚክ ቦምብ ማስተኮሻ ያላቸውና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የሚሊተሪ ማሽነሪዎች የእንግሊዝን ሁለተኛ ትልቅ ከተማን ግላስጎን በለሊት ማቋረጣቸው ግላስጎ ላይቭ አጋልጧል።
ይኸ የሚያሳየው የሩሲያ የዩክሬን ጦርነት ወዴት እያመራ መሆኑን ነው።
ወደዚህ አደገኛ ጨዋታ እየገቡ ያሉት እነ UK ቀደም ሲል ዩክሬንን ከበው ፣ ሩሲያን ገፍተው ያቀጣጠሉት ጦርነት ከዩክሬን አልፎ እነሱንም ሊፈጃቸው መቃረቡን በእርግጠኘነት የተረድበት የጣራቸው ጊዜ ለይ ለመገኘታቸው ይኸ በሚሲጥር በጨለማ እያጓጓዙ ያሉት የኒውክለር ዊገን ማረጋገጫ ነው።
እንደ ኔቶ ብቻ ሳይሆን አሜሪካና እንግሊዝ እንደገና በተለየ ሚናና ጥምረት በሚስጥርም በግልጽም ለኒውክለር ጦርነት እየተዘጋጅ ለመሆኑ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከመጀመሩ ቀደም ብሎም እየታየ ነበር።
ይኸ ዝግጅት ግን ከጦርነቱ ሁለተኛ ሳምንት በኋላ ተጠናክሮ ሲታይ ከርሟል።
ሰሞኑን የ US F 35 የአቶሚክ ተዋጊ በእንግሊዝ አየር ለይ ሲቀዝፍ ታይቷል። ይኸ ጄትም የኢላማ ልምምድ ሲያደርግም ከሳተላይት የተገኙ የኢንተለጀንሲ መረጃዎች አጋልጠውም ነበር።
የአሜሪካ የጨለማው ቀናት አውሮፕላን (doomsday plane ) ለአቶሚክ ቦምብ ልምምድ በአሜሪካ አየር ለይ ሲንቆራረጥ ነበር።
የአቶሚክ ቦምብ ተዋጊው የአሜሪካው አዲሱ B 21 አየር ለይ የታየውም ሰሞኑን ነበር።
በዚህ መሀል የአሜሪካ CIA የልዩ ተልእኮ የረቀቀ የስለላ አውሮፕላን እንግሊዝ ለይ እጅግ ሚስጥራዊ (mysterious secreat ) ጉዳይ ተገኘቶ ነበር።
አድማስ ተሻግረው የኮሪያን ፔንሱሉና የወረሩ የአሜሪካ የስለላ ጄቶችም የዚሁ ዝግጅት አካል ናቸው።……….
++++++++++++
በእርግጥ ይኸ የነ ኔቶ የኒውክለር ጦርነት ዝግጅት በሩሲያ ለይ የበላይነትን ይሰጣቸው ይሆንን ?!
በጦርነቱ ማንም አሸናፊ ባይኖርም ቀድሞ የሚሞት ግን አለ።
ከዚህ አንጻር ባለፈው ባጋራኋችሁ መረጃ የሩሲያ ሱፐር ዊፐንስ አካል የሆነው የአቶሚክ ቦምብ ተዋጊ ከብራሰልስ ሰማይ 42 ማይልስ ለይ ሲፈነዳ ከለንደን እስከ ፓላንድ የሚገኘውን የኤሌክትሪክ ሀይል ከጥቅም ውጭ በማድረግ እነዚህን በሚስጢር የሚጓጓዙና የሚጠመድ የኒውክለር ዊፐኖች ከጥቅም ውጭ ያደርጋል (paralize ያደርጋል። ) ስራ ለይ እንዳይውሉ ያደርጋል።
ከዚህም በላይ የጠላት ዊፐኖችን ሳያወድሙ በሚረጩት የኤሌክትሪክ ሞገድ ሽባ paralize የሚያደርጉ እስካሁን በጦርነት ለይ ያልዋሉ የሩሲያ ሚስጥራዊ ዊገኖች ስራ ለይ ይውላሉ።
ይኸም የቀድሞ መውደምን እድል ለአውሮፓ ያደርገውና ቀሪውን ሞት ሩሲያም አለምም የሚጋሩበት መራር እውነት ይቀጥላል።
ስለሰፋብኝ ቆረጥኩት እንጂ የሩሲያው ትራይፓን ባሕር ሰርጓጅም ጨዋታውን በ30 ደቂቆች ውስጥ ይለውጣል። የሌሎችን አገራት ሚናም አለ። እመለሳለሁ።
(ወንድወሰን ሰይፉ ቅድስ )