ኦጋዴን፡ የህወሃት ጂኦ-ፖለቲካዊ መካነ-መቃብር?

     የዓባይ፡ልጅ✍️ 

የቻይናው ፓሊ-ጂሲኤል ኩባንያ በኦጋን የነዳጅ ልማት ላይ የፈጠረውን መጓተት ተከትሎ ወደ መቋጫው የተቃረበው የቤይጂንግ እና ዋሽንግተን ቀጣናዊ ትንቅንቅ መጠነ-ጡዘት ላይ በደረሰበት ሰሞን ነበር።

የማዕድን ሚኒስቴር “የነዳጅና ኦጋዴን የሚገኘው የተፈጥሮ ሀብቱ የምርመራና የምርት ሂደቱን አልፎ ለገበያ የሚቀርብበት ደረጃ ላይ ቢደርስም ኩባንያው ባጋጠመው ውስጣዊና ዓለምአቀፍ ቀውስ ምክንያት ምርቱን ወደ ገበያ ሳያቀርብ ረጂም ጊዜ አልፎታል።” በማለት ሲገልፅ ቆይቷል። ይህን ተከትሎም ባሳለፍነው የ 2014 በጀት አመት ላይ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ስምምነት ከሌላ አለም አቀፍ ኩባንያ ጋር ተፈርሟል።

የማዕድን ሚኒስቴር ስምምነቱን የተፈራረመው መሰረቱን አሜሪካ ካደረገው ኔዘርላንድስ ስዌል እና አሶሼት Netherlands Sewell & Associates ኩባንያ ጋር ሲሆን፤ ጊዜውም መጋቢት 13 ፣ 2014 ላይ…። በስምምነቱ የአሜሪካው ኩባንያ በኦጋዴን አካባቢ 3 ሺህ 500 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ የተሰሩ የፍለጋ እና የጥናት ውጤቶችን መነሻ በማድረግ በአካባቢው ያለውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት መጠን የማሳወቅና ኢኮኖሚያዊ ግምገማን የሚያሳይ ጥናት ለማካሄድ የሚያስችለው ነው። ይህን ተከትሎ ከቻይናው ፖሊጂሲኤል ጋር የነበረውን ውል ማቋረጡን የማእድን ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው በኢትዮጵያ አዲስ አመት ወርሃ መስከረም ላይ ነው።

ፖሊጂሲኤል GCPoly በሚለው ስሙ በስፋት ይታወቃል። ታዲያ ከአሜሪካ ጥርስ የከተተው አንድ ጉዳይ አለ። ይህ ግዙፍ ኩባንያ በተለይም ፖሊሲሊኮን በሚባሉ የሶላር መሳሪያዎች በማምረት በግዝፈቱ ከአለም ሁለተኛ ነው። አሜሪካ ምርቱን በገፍ ትሸምተዋለች። ሻጯ ደግሞ ቻይና ናት። በዘመነ ትራምፕ በነበረው የንግድ ጦርነት ወቅት ምርቱ ለዋሽንግተን አስላጊ ስለሆነ ፖሊሲሊኮን ለሚያመርቱ የቻይና ኩባንያዎች የታክስ ጫና ርምጃው በተለየ እንዲነሳላቸው ለማድረግ ተገደው ነበር። ምክንያቱም ቻይና የአለማችንን 90 በመቶ ፖሊሲሊኮን የምርት ሂደት value chain የተቆጣጠረች ናት። በምርት ረገድ ደግሞ 50 በመቶው በቻይና ፋብሪካዎች የሚቀርብ ነው። አሜሪካ ከቻይና ጥገኝነት ለመላቀቅ በሰፊው ኢንቨስት ለማድረግ ብትሞክርም በሶላር ምርቶች በኩል ያሳካችው 40 በመቶ እንኳን በወጉ ያልደረሰ ነው። በዚህ ላይ የቻይና መንግስት ለዘርፉ ባመቻቸው ልዩ ህግ በሀገሪቱ ውስጥ ምርቱ በርካሽ እንዲመረት ሆኗል። በአለማቀፍ ገበያም እስከ 40 በመቶ የዋጋ ቅናሽ አለው። በዚህ የተነሳም አሜሪካ ቻይናን መገዳደርም ሆነ ከጥገኝነት ለመላቀቅ አልተቻላትም።

ይሁንና የባይደን አስተዳደር Xinjiang Production & Construction Corps ወይም XPCC የተባለ ኩባንያን ከማዕቀብ ዝርዝር ውስጥ አስገብተውታል። ኩባንያው ጨርቃጨርቅ ላይ የተሰማራ ሲሆን “ጉልበት ብዝበዛ” በሚል ነው ዋሽንግተን ለርምጃዋ መነሾ ነው ያለችው። ታዲያ የዚህ ኩባንያ ከፍተኛ ድርሻ የ GCL-Poly ነው። ጉዳዩ ከዛህ ይጀምራል ማለት ነው…።
በሌላ በኩል ፖሊጂሲኤል በኦጋዴን ከተሰማራ ጀምሮ ሶማሊላንድ ስትቃወመው ቆይታለች። ለአብነትም የጤና ጉዳት አመጣብን፣ ቻይና አላግባብ እየተስፋፋች ነው የሚሉ ዘመቻዎቿን መጥቀስ ይቻላል። የሶማሊላንድ ዋነኛ ምክንያቷ ግን ከሶማሊያ ጋር ካለባት ሽኩቻ የመነጨ ነው። በቻይና አካሄድ ስትበሳጭ ለታይዋን እውቅና በመስጠት ለቤይጂንግ ምላሿን አሳይታለች።

ከወራት ወዲህ በተለይም ከ2014 ሰኔ ጀምሮ በርካታ ምዕራባዊ የፖሊሲ ጥናት ተቋማት ሶማሊላንድ እውቅና ይሰጣት በማለት ተደጋጋሚ ጥናት ሲያቀርቡ ይታወሳል፤ በወቅቱ የፋርማጆ ሶማሊያን ለመጫን የታቀደ መግለጫ ነበር። አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ያጣችውን ቦታ በዚህ በኩል ማሳካት ትችላለች የሚለው ነጥብ በተቋማቱ ጥናቶች ዋነኛው ፋይዳ ሆኖ ሲጠቀስም ተስተውሏል።
ባሳለፍነው ጥር እና የካቲት ጀምሮ ደግሞ አሜሪካ ለሶማሊላንድ ሉአላዊነት አውቅና ለመስጠትና ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ህግ አርቅቃ ስትመክር አሳልፋለች። የእንግሊዝ ምክር ቤትም ሉአላዊነቷን ለመቀበል ውይይት ሲያደርግ ነበር። ይሁንና ፕሬዝደንት ፋርማጆ በሐሰን ሼክ ከተተኩ በኋላ የሶማሊላንድ ጉዳይ እንደተረሳ ነው የሚገኘው።

“በሶማሌ ክልል የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ያዘገየው የፖሊጂሲኤል ኩባንያ 2 ቢሊዮን ዶላር ማስተማመኛ እንዲያቀርብ የታዘዘው በ 2013 ጥቅምት ነበር። ይህንን ተከትሎ ኩባንያው የተፈጥሮ ጋዙን ለማልማት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የሚገልጽ ዝርዝር ለማዕድን ሚኒስቴር ማስገባቱ በወቅቱ የተዘገበ ሲሆን፣ ባቀረበው መረጃ ላይ ግን ማዕድን ሚኒስቴርና ኩባንያው መተማመን እንዳልቻሉ ነበር በወቅቱ ሪፖርተር ጋዜጣ ያስነበበው።

በፖሊ-ጂሲኤል ኩባንያ የተፈጠረው መጓተት አሳሳቢነት እንደተጠበቀ ሆኖ የጂኦፖለቲካ ጥልፍልፍ ዙሪያውን እያንዣበበ መሆኑ ሲጨመርበት በርግጥም ቆም ማለትን የሚጠይቅ ፈታኝ የሚባል ነበር። ኩባንያው ለቻይናም ለአለምም ግዙፍ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በቤይጂንግ እና ዋሽንግተን የንግድ ጦርነት ዝርዝር ውስጥ የሚገኝ መሆኑም በተመሳሳይ..።
በመጨረሻም፣ የቻይናው ፖሊ-ጂሲኤል በኦጋዴን የነበረው ውል የተሰረዘው፤ የአሜሪካው ኩባንያ ኢትዮጵያ በኦጋዴን ያላትን የተፈጥሮ ጋዝ ሐብት መጠን ገልፆ አለም አቀፍ ሰርተፍኬት የሰጠው፤ የህወሃትን ሶስተኛ ዙር ወረራ እንዲሁም ምእራባዊያኑ በአፍሪካ ቀንድ፣ በተለይም በኢትዮጵያ የፖሊሲ አማራጮችን እያከታተሉ በነበረበት ወቅት መሆኑን እዚጋ ልብ ይሏል። ይህን ተከትሎም ምእራባዊያን ከህወሃት የነበራቸው ትያትር አንድ ጊዜ ኮሜዲ፣ ሌላ ጊዜ ወለፈንዲ በቅርቡ ደግሞ ወደ ኤልሳቤታዊ መሪር ትራጄዲ እያደረገ መልኩን ሲለዋውጥ ታዝበናቸዋል።
የኦጋዴን ምድርም የህወሃት ጂኦ-ፖለቲካል መካነ-መቃብር ለመባል የሚበቃ ሆኗል።

Esleman Abay #የዓባይልጅ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

1 thought on “ኦጋዴን፡ የህወሃት ጂኦ-ፖለቲካዊ መካነ-መቃብር?”

  1. ለምትጽፋቸው ማናቸውም ታሪካዊ ይዘት ያላቸው በተለይ ምስራቅ አፍሪቃ ላይ ጂኦ ፖለቲክስ ይዘት ያላቸው መጣጥፎች እጅግ አይን ገላጭ እና ለምንንኖርባት የተወሳሰበች አለም እንደ library ሆኖ አግኝቼዋለው ::ደክመኝ ወይም ሰለቸኝ ሳትል ያወቅክውን ለሰዎች ለማካፈል የሄድክበት እርቀት ምስጋና በራሱ ብቻ በቂ ባለመሆኑ አንድ ቀን በክብር የሚያስሸልምህ መሆናቸው ስራዎችህ በቂ ማሳያ ናቸው:: ዘወትር ለምታሳየው ብርታት እና ጥንካሬህ ፈጣሪ እርዳታው አይለይህ መልካም ምኞቴ ሲሆን ብእርህ አይንጠፍ የሚለው ምርቃቴ ነው::

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories