ከሊቢያው ጠባሳ….

ታላቋ ሊብያ በ1951 እኤኣ የአለማችን የድሃ ድሃ ሃገር ነበረች። ፕረዚዳንት ሞሃመድ ጋዛፊ ወደስልጣን ከወጣ በኋላ ሃገሪቱ አመታዊ ጂዲፒዋ 150 ቢሊዮን ዶላር ሆነ። ከአለም የተበደረችውን ገንዘብ መልሳ እዳዋ O የሆነ የሆነችና የአላማችን ተጽእኖ ፈጣሪ ሃገር ሆነች። የአፍሪካን ከድህነት መውጣት የማይወዱት ፈረንጆች ሃገሪቱን ለማፈራረስ ከፍተኛ ገንዘብ መደቡ በሰፊው መከሩ በምን እና እንዴት ማፈራረስ እንዳለባቸው የረጂም ጊዜ እቅድ አወጡ መክፈል ያለባቸውን መስዋዕትነት ከፈሉ። ሊብያ ውስጥ የእርስ በርስ ጦርነት አስነሱ አሜሪካና ፈረንሳይ ከሃዲ ሊብያውያንን ሃገራቸው ወስደው አሰለጠኑ። በአንባገናዊነት ሰበብ ራሳቸው ጣልቃ ገቡ ለዜጎቿ ምቹ ለጎብኝዎቿ የመንፈስ እርካታ ትሰጥ የነበረችው ባለጋዟ ሃገር ሊብያ ሃብቷ ተዘረፈ ፈራረሰች። በመጨረሻም ለዜጎቿ ሲኦል ሆና ቀረች።
ኢትዮጵያውያን ሆይ እባካችሁ እኛ ከአለም ቀድመን የሰለጠንን የመቻቻል የመከባበርና የመረዳዳት ተምሳሌት ሃገር ነበረን ምንም ያክል የገንዘብ ድሃ ብንሆኖም ለዛሬ ጽንፈኞች በቀደዱልን ቦይ ገብተን ለጊዜው ገንዘብ አግኝተን ፍላጎታችን ቢሳካም; ለጊዜው ጽንፈኛና ከሃዲ ባለስልጣናት ሽፋን ቢሰጡንም; ፈጣሪ ያከበረውን ደም አፍሰን መንግስት ሰማያትን ወራሽ እንደሆንን በጭፍን የሃይማኖት ሰባኪያን ቃል ቢገባልንም; ወ.ዘ.ተ.. ተቸግራ በድህነት አንጀቷ አዝና ያሳደገችንን እናት ሃገር እያፈረስን መሆኑን እንድንገነዘው በሰውኛ ቋንቋ ለመግለጽ እወዳለሁ። ለኛ ከፈረሰችው ብርቱ ሃገር ሊብያ በላይ ገላጭ የለንም። ብልጥ ከሌላው ውድቀት ይማራል!!
ሱልጣን አህመድ

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories