ከ ቢል ጌትስ-ጀርባ…፤ 50 የሚሆኑ የአፍሪካ ሕፃናትን ሽባ ያደረገው ክትባት

Bill gates in africa

የምርመራ ዘገባ ቅኝት Esleman Abay

አንድ ደም ቀጥ የሚያረግ ታሪክ ላውራችሁ፤ ከ 6 ዓመታት በፊት የተከሠተ ሲሆን… እሱም በአፍሪቃ 40 ሕፃናትን ሽባ ያደረገ ከባድ እንከን ያለበት ክትባት እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡

ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በምድር ላይ ያሉትን እያንዳንዱን ህፃን ለመከተብ ለአስርት ዓመታት በተከታታይ ዘመቻ ላይ ነው የሚገኙት፡፡ ግምባር ቀደም ተተኳሪ ከሆኑት መካከልም አህጉረ አፍሪካ አንዷ ናት። “በአፍሪካ ዝቅተኛ የንፅህና አጠባበቅ እና የንጹህ ውሃ እጥረት መኖር ለሽታዎችና ወረርሽኝ መፈጠር ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል” የሚለውም አፍሪካ ላይ እንዲያተኩሩ አደረጋቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህን መሠረታዊ አቅርቦቶች ለማሟላት ከመሞከር ይልቅ ብዙ ቢሊየነሮች እና አጋሮቻቸው ለአህጉሪቱን ተወላጆች ክትባት በብዙ ወጪ መስጠትን መረጡልን። ይህም በርካታ ህፃናትን ሽባ አደረገ፡፡

[ ይህ ታሪክ በአንዲት መንደር ስለተከሠተ የጤና አደጋ ብቻ ያወሳል። ነገርግን በቢልጌትስ ፋውንዴሽን ክትባት ተሠጥቷቸው መሀን ስለሆኑት በሺዎች ስለሚቆጠሩ ኬኒያውያን እንስቶች ሌላ ቀን እናወራለን። ተመሳሳይ አደጋ ስለገጠማቸው አስር ሺዎች አፍሪካዊ ሴቶች ለማውራትም ሌላ ጊዜ ያስፈልገናል። ለዛሬ ይችን እንካፈል… ]
………
የምርመራ ጋዜጠኛ የሆነችው ክሪስቲና ኢንግላንድ Vactruth.com ላይ እንዳሰፈረችው ፣ በሰሜናዊ ቻድ የሚገኘው የጎሩ ትንሽየ መንደር ፣ ቢያንስ 50 የሚሆኑ ታዳጊዎች ከክትባቱ በኋላ ለከፋ የጤና እክል ተዳርገዋል፡፡

በወቅቱ በቢልና ሜሊንዳ ጌትስ የሚደገፍ “ሜንአፍሪቫክ” የተባለና በተለይ ለአፍሪካ አዲስ የማጅራት ገትር በሽታ ክትባት ፕሮጀክት ተጀምሮ ነበር፡፡ ታዲያ ክትባቱ ሁለት የአጎት ልጆቹን ሽባ ያደረገበት ነዋሪ እንዳለው ክትባቱ ህመም ማምጣት የጀመረው ከመከተባቸው በ 24 ሰዓታት ውስጥ ነበር፡፡ በአደጋው ​​የተጠቁት ብዙ ልጆች ወዲያውኑ ራስ ምታትና ማስታወክ ታይቶባቸዋል፣ በኋላም ከአፋቸው አረፋማ ምራቅ እንዲሁም መዝለፍለፍና እብጠት ተከስቶባቸዋል።

ወላጆች ስለተፈጠረው ነገር ለባለ ሥልጣናት አሳውቀው አንድ እርምጃ እንዲወስዱ መወትወታቸውን ቀጠሉ። ነገርግን ጥያቄያቸው በቸልታ ታልፏል፡፡

እጅግ የሚያሳዝነው ነገር የቻድ መንግሥት ባለስልጣናት የተጎጂ ህፃናት ወላጆችን ዝም ለማስባል ጉቦ እስከ መስጠት መድረሳቸው ነበር።

ለመርማሪ ጋዜጠኛዋ ክርስቲና ኢንግላንድ ስሙ እንዳይጠቀስ ይሁን ያለውና እሷም በዘገባዋ “ሚስተር ኤም.” ብላ የጠቀሰችው የተጎጅ ህፃናት የአጎት ልጅ፤ አክሎም “የቻድ የጤና ሚኒስትር እና የማህቀራዊ ዋስትና ሚኒስትር ጎሮ ከተባለችው መንደር ሽባ የመሆን እክል የገጠማቸውን ህፃናት ከተረከቡ 300 ማይሎች ርቆ ወደሚገኝ ሆስፒታል አዛወሯቸው፡፡

MenAfriVac እንዲህ ዓይነቱ ከባድ ችግር ለምን ተከሰተ ብሎ ክትባቱን ከማስቆም ይልቅ ሥቃይና ጉዳት ለደረሰባቸው ወላጆች በጉቦ አፋቸውን ማዘጋት ላይ ነበር ሲሯሯጡ የነበረው፡፡
ሚስተር ኤም እንዳሉት የነዚህ ባለሥልጣናት የ”ሜንአፍሪቫክ” ክትባት አደጋዎችን መሸፋፈናቸው ክትባቱ ከፈጠረው ጉዳት በላይ ታላቅ በደል ነበር።” ሚስተር ኤም አክለውም ክስተቱን መንግስት እና መገናኛ ብዙሃን አላወሩትም” ፣ አሁንም ማብራሪያን የሚጠይቁ ተጨባጭ መረጃዎች አሉም ”ብለዋል፡፡ ይህን ትልቅ አደጋ ምንም ሚዲያ አለመዘገቡ የሚረብሸና ለወደፊቱም የከፋ መጥፎ ነገር ያመጡብናል ብለን እንድንፈራ አድርጎናል። ”

የጌትስ ፋውንዴሽን እና የ WHO ቅጥፈት

ከሁሉ የከፋው ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ፣ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እና የ “ማኔንጃይተስ ክትባት ፕሮጄክት (ኤም.ቪ.ፒ.) ቅጥፈት ነበር። በወቅቱ ሁሉም ተቋማት MenAfriVac ን በከፍተኛ ሁኔታ ሲያስተዋውቁ ነበር። ስለ ክትባቱ ደህንነትም በይፋ ይዋሹ ነበር። ድርጅቶቹ፣ መድሀኒቱ ያለ ማቀዝቀዣ ካገር አገር ለአራት ቀናት መጓጓዝ ይችላል ይላሉ። የክትባቱ ማሸጊያ ላይ ታዲያ “በማቀዝቀዣ ውስጥ መቀመጥ እና ከብርሃን የተጠበቀ መሆን አለበት” ተብሎ በግልጽ የፃፈበት።

ጋዜጠኛዋ ወሳኝ ጥያቄን ሠነዘረች፣ “ፕሮጄክቱ 571 ሚሊዮን ዶላር ለምን ለክትባቱ አውጥተውታል?
ለወረርሽኙ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥረው የንፅህና ጉድለት መሆኑን እናንተው ተናግራችሁ፤ የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ ለአፍሪካ ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ከ 3000 ዶላር በታች ነው ወጪ ያደረገው። ይህ ለምን ሆነ?” ስትል ነበር የጠየቀችው። ይህ የሁላችንም ጥያቄ ከመልስ ይልቅ ሌላ ጥያቄ እየወለደ እስካሁን ድረስ ዘልቋል።

የነዚህ ድርጅቶችን አረመኔያዊ ድርጊት ለመመከት መፍትሔ ሳናዘጅ አፍሪካ ውስጥ እንደምን ሊቀጥሉ ቻሉ? bill and melinda gates foundation እኮ በህንድ የነበረውን ቅርንጫፍ 2017 እንዲዘጋ ተደርጓል። የአገር ጥቅምና የዜጎች ጤና ላይ ስጋት ከመደቀኑ ባሻገር የህንድ የህክምና ደህንነት ተቋም የክትባቶቹን ሁኔታ መፈተሽ ይኖርብኛል ማለቱን እነ ቢልጌትስ አለመፍቀዳቸው ለመቆራረጣቸው ዋናው ምክንያት ነበር።

“ለምን?” እንበል። ግልፅ ምላሽም አያሳጣን…
BY
Esleman Abay ethiopia
[ ፎቶ ከምርመራ ዘገባው የምስል ማስረጃ የተወሰደ ]

የምርመራ ዘገባውን ከዚህ ያንብቡ?
https://vactruth.com/2013/01/06/paralyzed-after-meningitis-vaccine/

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories