በአገሪቱ ስላለው መጨካከን፣ ስለ ቤተ-እምነቶች መቃጠል፣ ስለ ምዕመኑ መገደል፣ ስለ ለማ መገርሳ መታገድ፣ ወዘተ ….ወይም ለውጡ እንዴ’ነው? የሚል ጥያቄ ቢቀርብ ከራስ አስተሳሰብና ዝንባሌ የተፋታ አስተያየትና ምላሽ የሚሰጠው በርግጠኝነት በጣም ጥቂቱ ነው ።
ታሪክ፣ ፣ ሀይማኖት፣ ባህል፣ ፖለቲካና ብሔር አንዱ ካንዱ የተዛንቀበት ስነ-ልቦናችን የውይይት አጀንዳዎቻችንን ያለሰገባው እየደነጎረብን ነውና፣ ለችግራችን መፍትሄ አይደለም_ ችግሩን ለመለየት አንኳን አስቸጋሪ አድርጎብናል።
ከዚህ በፊት በአእምሮው ያስቀመጠው አንድ መረጃ፣ እውነታ ወይም ግላዊ አተያይ ሁሌ “ትክክል ነው”፤ ተመሳሳዩን የሚያስቡት “ልክ ናቸው”፤ የተለየ ያሰቡት ግን “ስህተት” የሚል አስተሳሰብ በስነ-ልቡና ጠበብቱ Confirmation-bias ተብሎ ይበየናል። ይህ አይነት ችግር የተጠናወተው ሰው የጉዳዩ ጠበብት እንኳን ቢነግሩት አይሰማም፤ የምርምር ግኝት ብታቀርብለት መስሚያው cotton ነው። እሱና መሠሎቹ ብቻ ናቸው ለሱ ትክክለኛዎቹ። ይህን መሠል ማህበረሰባዊ ስነ-ልቡና ባገራችን ተንሰራፍቷል። በተለይ ደግሞ አገራዊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ…።
የዲጂታል ቴክኖሎጂው algorithm ደግሞ ችግሩን ያባብሳል። ፌስቡክም ሆነ ጎግል ከዚህ ቀደም ደጋግመህ ያነበብከውን፣ react ያደረክበትንና ሼር ያደረግከውን ይዘት ይመዘግባል። በቀጣይ መሠል ይዘት ከየትኛውም አለም ሲጫን ወዳንተ ያመጣልሃል። ለነ ፌስቡክ ትልቅ ገበያ፣ ላንተ ደሞ የ confirmation-bias በሽታህን የሚያተልቅ መዘዝ ሆኖ ይቀጥላል ማለት ነው።
የማህበራዊ ድረ-ገፅ ፖስቶችን፣ የግለሰብ ንግግር፣ አዲስ የሚወጡ የመንግስት አዋጅና ፖሊሲዎች …. የያዙትን አንድምታ ዘለነው፣ ከነባር አመለካከታችን ጋር በማፃረር እንተቻለን፤ ሲሠሳሰል እናወድሳለን። ይህ ችግር ደግሞ echo chamber የሚባለው ነው።
በጣም የገረመኝ ከ 71 በመቶ በላይ የሶሻል ሚዲያ አጀንዳዎችና ይዘቶን ከህዝቡ ችግር ጋር የማይገናኙ መሆናቸውን የሚያስረግጡ ጥናቶችን ስመለከት ነወ። የአጀንዳዎቹ ኢ-ፋይዳቢስነት መብዛት ሳያንስ ለምንሻው አገራዊ ለውጥ የምንከፍለው መስዋዕትነት ከዚህ ኢ-ምክንያታዊ የሶሻል ሚዲያ ኢኮ-ቻምበራዊ ጩኸት አለማለፉ ነው። ሶሻል ሚዲያ መረጃን ተደራሽ፣ የባለስልጣናትን ችግር አደባባይ ለማውጣትና ተገቢ የለውጥ ጥያቄ ለማንሳት ማስቻሉ ነው ጥቅሙ። ይህ ብቻ ግን ችግር አይቀርፍም ለውጥን እውን አያደርግም። ጥያቄዎች ወደ ለውጥ የሚያሻገሩት በመንግስትና በህዝቡ መካከል ያሉ ሲቪክ ተቋማት የዚሁ አካል ሆነው በሚያስቀምጧቸው ቀጣይ ተግባራት ላይ ዜጎች ከሶሻል ሚዲያ ተሻግረው መሬት ላይ የሚወርድ ሚና ከተጫወቱ ብቻ ነው። እኛጋ አጀንዳዎች ከህዝብ ጉዳይ ይልቅ ከኢሊት ግለሰቦች ፍላጎት ብቻ ይመነጩና፣ በጥቂት የፌስቡክ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እንደ አዋጅ ተደንግጎ ብዙሃኑም በዚህ ቀኖና ይነዳበታል ። ከዛማ…ቼ-በለው! ይጀመራል። የታገልን ይመስለናል። ግን እንደዛ ለውጥ አይመጣም። ይሄ “ክሊክቲቪዝም” የሚባለው ነው። በቃ…ላይክ፣ ሼርና በ confirmatin-bias የተጠለፈ ኮመንት በ echoe chamber ሮች ተቧድኖ መጮህ ብቻ። ለዚህም ነው ከ 75 በመቶ የሚበልጡ የሶሻል ሚዲያ የለውጥ እንቅስቃሴወቀች (ክሊክቲቪዝም) አላስፈላጊ ዋጋ አስፈሸለው ሳይሳኩ የሚቀሩት፤ እንደ ጥናቶች። አክቲቪዝም በአኖኒመስ አካላት አይነዳም። የምክክር መድረክ ያለው፣ በጥናትና ምርምር ግኝቶች የሚመራ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ባሉ አካላት የሚመራ ቢሆን’ንጂ።
ከዚህ ችግር ካልወጣን ምሁራን የመፍትሄ ሀሳብ ለመሰንዘር ይሸማቀቃሉ፤ ዴሞክራሲያዊ የውይይት ባህል አይኖርም፤ ሲቪክ ተቋማት የተልፈሰፈሱ ይሆናሉ፤ የማይጠቅመን የግለሰብ አጀንዳ በማራገብ የብዙሃኑ ድምፅ እንውጠዋለን፤ የማታዳምጠው ቡድን ደግሞ አንተንም አይሰማህም፤ በዚህ ስንደናቆር መንግስታት አክቲቪስቶችህን ይሸምታቸዋል። አንተ በተገዛ አክቲቪስት እየተነዳህ ዲክታተሮችን ታፈረጥማለህ ማለት ነው።
እና ፕሊስ! ከ echoe-chambers እንውጣ! confirmation-bias የስነ-ልቡና መናጋት ነውና መጀመሪያ ከዚህ እናገግም–ከዚህ ወጥተን ነው ስለ ለውጡ፣ ስለ ህጎች፣ አዋጅና ፖሊሲዎች እንዲሁም አገሌ ጥሩ! እገሌ ቀሽም! ማለት የምንችለው።
“echoe-chambers”ን እና “confirmation-bias”ን በጋራ እንዋጋቸው!