ወደ ጠፈር የተላከው የዓባይ ውኃ ጉዳይ


▪️የዓባ፡ይልጅ ✍️

“አልሞትኩም ብዬ እዋሻለሁ” የሚለው የካይሮ ተከታታይ ትያትር ቀጥሏል። ትእይንቱ ያልተከፈተበት ቀጣና የለም ማለት ይቻላል። ካርቱም ኮንጎ አፍሪካ ህብረት አረብ ሊግ ዋሽንግተን ወዘተ እያለ እስከ ፀጥታው ምክር ቤት ያልረገጠበት አልነበረም። ይህን ሁሉ ስትፈፅም ግብፅ የዓባይ ልጆችን ቅምባ የመድፋት ያህል በቸልታ እና በንቀት እንጂ የተከባበረ ምክክርን አሻፈረኝ እንዳለች ነበር።

የዓባይ ውሃ ጉዳይ አሁንም የምንጩ መገኛ ለሆኑ ህዝቦች ጀርባውን እንደሰጠ ዛሬ ላይ በ NASA በኩል ወደ ጠፈር ተልኳል። ማምጠቂያ መንኮራኩሩ በውል ባይታወቅም ለመገመት ግን አይከብድም። ይኸውም Shameless 101 ፣ Hypocrisy 360 ወይም Greed A-Z ከተሰኙት ‘መንኮራኩሮች’ ውስጥ ስለመሆኑ ‘አያጠራጥርም’።

ግማሽ ያህሉ ኢትዮጵያዊ ኤሌክትሪክ ያገኛል።” ሲል ይጀምራል NASA ዛሬ ያስነበበው ይፋዊ መረጃ። እንዴት ያለ ሰበብ ይሆን እንዲህ አይነት መጨነቅ ውስጥ የከተታቸው? 85 በመቶ ውሃ ከሚለግሰው ኢትዮጵያዊ 60 በመቶው ኤሌክትሪክ እንደሌለው እየታወቀ፤ “..ያገኛል” ከሚለው ከቅጥፈት በላይ ከሆነው “የጨነቀ ለት” ገለፃ ጋር 40 በመቶው እንዴት ቢጠጋጋ ነው “about half of ethiopians have access to electricity” የሚያስብል ሀተታ ለመፃፍ የደፈሩት?
(በምስሉ ላይ ያካተትኩት አሜሪካን የተመለከ አሃዝ የያዘ ሲሆን 45 በመቶ አሜሪካዊያን የሚለውን እንዳለ ተቀምጦ ያስመለክተናል። 45 በመቶው ግማሹ አሜሪካዊ የሚባልበት ገለፃ ባልተለመደበት ተጨባጭ 40በመቶውን ኢትዮጵያዊ ግማሽ ያህሉ ሲሉ ደፍረውታል።)
ይገርማል። የሚገርመው ነገር ታዲያ አሜሪካ በሞቱ ፋይሎች ላይ እንዲህ ስትጋጋጥ መታየቷ ጭምር ነው።
ሲቀጥል ደግሞ ግድቡ ባለፈው መስከረም 23 በመቶ በውሃ ተሞልቶ ነበር ይላል። ለዚህም የ NASA ተቋምና Satellite ONE ለዚሁ መረጃ ግብአት ማቅረባቸውን ይጠቅሳል። በጥናቱ ከተሳተፉ ውስጥ በማለት ዋቢ ያደረገው ምሁርም አለ። ሰውየውን የቻፕማን ዩኒቨርሲቲ ምሁር ነው በማለት ሂሻም አል አክሳሪ መሆናቸውን ጠቅሶ ያልፋል። ሒሻም ግብፃዊ መሆናቸውን ግን መግለፅ አልፈለገም።
ስለ ግድቡ ጉዳት ለመናገር የሞከረው NASA 95 በመቶው ግብፃዊ ህልውና በናይል ውሃ ላይ የተመሰረተ መሆኑን እንደማሳያ ሊያቀርብ ሞክሯል። ዋው ኢትዮጵያ…! 95 በመቶው ግብፃዊ ከኢትዮጵያ ምድር በሚሄድለት ውሃ የተመሰረተ ህይወት ካለው፤ እነሱም ስራ ሰርተውበታል እንበልላለው ግዴለም…፤ ከዘመናት በኋላ መብራት እናድርግ ስንል ምላሹ ዛቻ መሆን ነበረበት?

እንደ መጠቅለያ፦ ይህ የግድቡ ጉዳይ ቀናትን እየጠበቀ በዋሽንግተን ሰዎች ሲነሳ የምናየው ሀገሪቱ ኢትዮጵያ ላይ ለጀመረችው የጫና deterrence ስትራቴጂ አንዱ አካል በመሆኑ ነው። ይሁንና ካይሮ የቀጠረቻቸው ሎቢስቶች “የጠላት ገንዘብ ነው” በሚል ጉዳዩን እሰከ ናሳ አድርሰውት ስንታዘብ ወዲህ እኛ የተለገሰንን ፀጋ ብሎም ይዞብን የሚመጣውን ጦስ ምን ያህል ቸል እንዳልነው ያመላክተናል።

የዓባይን ጉዳይ ስትራቴጂካዊ ብናደርገው ሀገራችን በማንም የማትሸነፍ እንዲያውም መጪውን ዘመን የምታሸንፈዋ የተስፋ ምድር ያደርጋታል🇪🇹

 ▪️የዓባይልጅ ▪️Esleman Abay

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories