“ውኃ” የዘመናችን ፈርዖን ታላቅ ፒራሚድ!

መግቢያ
በዓለማችን ካሉት ድንቅ ሥልጣኔዎች አንዱ የግብፅ ሥልጣኔ ነው፡ ይኽ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነው የግብፅ ሥልጣኔ ከተጀመረበት ከክርሰቶሰ ልደት ዘመን ጀምሮ ያም ማለት ከ3100 በፊት እሰካሁን ዓለምን ያስደመመ፣ የመሰጠ፣ በቅናት ያቃጠለ፣ በራሱ የአካዳሚክ ጥናት እና ምርምር መስክ ያለው ሥልጣኔ ነው:

የዛሬው ሥልጡን ምዕራባዊያን የጥንቱ አረመኔ ነጮችን በቅናት የሚያብሰከሰካቸው በአፍሪካ ምድር የበቀለ የአፍሪካዊኖች ሥልጣኔ አንዱ እና አንጋፋው የሆነው ይኸው የግብፆች ሥልጣኔ ነው: ዛሬ በአውሮፓ አንጋፋ ሙዜሞች ከግብፅ በተዘረፉ ታሪካዊ ቅርሶች የተሞላ ነው፡፡ ከዛም ልፎ ከግብፅ የተዘረፉ ቅርሶች (እንደ አኩሱም ሐውልት የመሳሰሉ) በለንደን እና በፓሪሰ አደባባዮች ተተክለው ይገኛሉ፡፡ (መጽሐ ታሪክ ዘኢትዮጵያ ከኑቢያ እስክ እስያ 7ፅ 111 ተመልከቱ) የዚህም ጽሑፍ አቅራቢ በፓሪሰ እና በለንደን ያሉትን ሙዚየሞች በጎበኘበት ወቅት ይኽን እውነታ አሰተውሏል፡
ይኽ ሁሉ የግብፅ ሥልጣኔ እና ገናናነት ያረፈው እኛ ለዘመናት በቸልተኝነት በተመለከትነው በአባይ ወንዝ ምክንያት ነው፡፡ ለእዚህም ነው ግብፅ የአባይ ስጦታ ነች የሚሉት፡፡

ምንም አንኳን ግብፅ የታላቅ ሥልጣኔ ባለቤት ብትሆንም እራሷን ከውስጥ እና ከውጭ ጠላት አልተከላከለችም፡፡ ከግብፅ ሥልጣኔ በኋላ ገኖ ለመጣው የሮማን ኢምፓየር አንድም በፍቅር ተጠልፋ አንድም በሥልጣን ሽሚያ ሉዓላዊነቷን ለሮማኖች አስረክባለች፡፡ የ20 ዓመቷ ኪሊዮፓትራ ከታናሽ ወንድሟ ሥልጣኑን ለመቀማት ባዳረግቸው ሴራ የ52 ዓመቱን የሮማኑን ጀነራል ጁሊያስ ቄሳርን በፍቅር አጥምዳ ዙፋን ላይ ብትቀመጥም ከጁሊየሰ ቄሳር ሞት በኋላ ከሮማን ጀነራል ኦክቶቢያ ጋር በተፈጠረው የሥልጣን ሽኩቻ ተጠልፋ ስትገደል እና ወደ ኢትዮጵያ ለጥገኝነት የላከችውን የ17 ዓመቱ የበኩር ልጇ ሲዛሪያን ጁሊየስ ሲሳር ኢትዮጵያ ሳይደርስ በሮማ ወታደሮች ተጠልፎ ከተገደለ በኋላ ግብፅ ሙሉ በሙሉ በሮማኖች እጅ ወደቀች

ኪሊዮፓተራ በሴራ ከተወገደች በኋላ ግብፅ የውጭ ኃያላን ገበጣ ሆና ለዘመናት ኖራለች፡ በዘመኑ የኦቶማን ኢምፓየር ደጋፊ የነበረችው እንግሊዝ ግብፅን ከፈረንሳይ መንጋጋ አላቃ የራሷ ቀኝ አደረገቻት British decisiveness and speed of actions which consistently outwitted and out manoeuvred the French and brought Egypt under Imperial British control HD እንግሊዝም ግብፅን ቅኝ ለማድረግ ሁለት አበይት ምክንያቶች ነበሯት፡፡ አንድም በአሜሪካ የእርስ እበርስ ጦርነት ምክንያት በተቋረጠው የጥጥ ምርት ለተጎዱት የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች አባይን ተጠቀማ ጥጥ ለማብቀል በመወስኗ እና ሁለትም ወደ የሲዊዝ ካናል በመከፈቱ ምክንያት ወደ ሕንድ የሚደረገው የመርከብ ጉዞ እጅግ በመቀነሱ ሲዊዝ ካናል ለእንግሊዝ አኮኖሚያዊም ሆነ ወታደራዊ ከፍተኛ ጥቅም በመሥጠቱ እንግሊዝ ካናሉን ለመቆጣጠር በማስቧ ነበር፡ እነዚህን ሁኔታዎች የብሪቲሽ ኢምፓየር የሚባለው ድረገጽ እንደሚከተለው ይገለፀዋል፦

1. British mills were starved of cotton. Alternative sources had to be found and one such source was to be Egypt whose cotton was actually a particularly good quality product. British companies began investing heavily in the production of cotton in Egypt.

2. British strategic interest in Egypt was captured in 1869 when the Suez Canal was officially opened. The sailing times from London to Bombay were dramatically cut

ምንም እንኳን ከአርባ ዓመታት የቅኝ አገዛዝ በኋላ በ1922 እንግሊዝ የግብፅን ሉአላዊነት እውቅና ብትሰጥም እiከ 1954 ድረሰ እንግሊዝ ከግብፅ ንቃ ላይ አልወረደችም ነበር። The UK unilaterally declared Egyptian independence on 28

February 1922, abolishing the protectorate and establishing an independent Kingdom of Egypt. Sarwat Pasha became prime minister. The history of Egypt under the British lasts from 1882, when it was occupied by British forces during the Anglo-Egyptian War, until 1956 after the Suez Crisis, when the last British forces withdrew in accordance with the Anglo Egyptian agreement of 1954.

ዛሬ ሱዳን ኢትዮጵያን ካልወረርኩኝ፣ የሕዳሴን ግድብ አልቀበልም ቤንሻጉል እና ጋምቤላ የኔ ነበር ያልች እምቡር እምቡር ሰትል ከበሥተጀርባዋም ግብፅ የአይዞሽ ባይነት ከበሮ ስትደልቅ ዱባይ ደግሞ በገላጋይነት ስትገባ የእዚህ ሁሉ ችግር መነሻው የአሜሪካ ሲቪል ጦርነት ነው ብሎ መገመት ይቻላል፡ የአሜሪካን የሲቪል ጦርነትን ተከትሎ እንግሊዝ የጥጥ እጥረት ባያጋጥማት ኖሮ ግብፅ ባልመጣች ሱዳንንም ባልያዘች ነበር። እንግሊዚም በማታውቀው አኅጉር እና አገር የድንበር ላካልል ባላለች ነበር። (ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንዲሉ ትናንት ያልነበረችን ሱዳን ከየአቅጣጫው መሬት ገምሳ የዛሬይቷን ሱዳን ፈጠረች) አንግሊዝ እግሯ የረገጠውን መሬት ሁሉ እንዳሻት እየሸነሸነች አገር አፍርሳ አገር ፈጥራ ዛሬ በዓለም ዙሪያ ላሉት ጦርነቶች ሁሉ ምክንያት ሆናለች፡ ለዚህም አንዱ ማሳያ የሕንድ እና የፓኪሰታን የካሽሚር ግዛት የይገባኛል ጥያቄ ነው. ያልነበረች ኩዌትንም ፈጥረውም ለኢራን መራስ እና ለሳዳም ሁሴን ሞት ምክንያት ሆነዋል።

ጥቅማቸውን በተመለከት ምእራብዊያን አንቀላፍተው አያውቁም፡ ሲያስኛቸው የሰይጣን ወይም የአምላክ መልዕክተኛ ሆነው ይመጣሉ (ወይ ጦር ወይ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው) እንሆ ከዐሥር ዓመታት በኋላ ወደ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ያቀናው የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን፡ ሱዳን እና ግብፅን እሸመግላለሁ እያለ ነው፡ የእንግሊዝ ዲፕሎማሲ በሁለት ጎኑ የተሳለ ሴንጢ መሆንኑ አንርሳ፡ ዜናው እንዲህ ይላል፡- “We have a longstanding friendship with Sudan and likewise a strong partnership with Ethiopia. Our message is, let’s not at this precarious moment for the region see an escalation of tension,” said Dominic Raab, adding that he would reiterate the same message to the Ethiopians during his visit there.

ዛሬም እንግሊዞች እና ብዙ አገራት ወደ ሱዳን ጎራ ያሉት ከዚህ ቀደም የሰሩትን ሰህትት ለማረም ሳይሆን የኢኮኖሚ ጥቅማቸውን ለማሰጠበቅ ነው፡ እንደተለመደው እኛንም ለግብፅ እና ሱዳን መደራደሪያ ካርድ ሊያደርጉን መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። ይኽንን በተመለከት ወደፊት አመለስበታለሁ፡፡ ለአሁኑ ወደ ዘመናችን የፈርኦን ፒራሚዶች እና ከሕዳሴ ግድብ ጋር ያለውን ትስሰር እንመልከት፡፡

የበርሃዋ እንጉዳይ፣ አዲሲቷ ካይሮ

እኛ (ኢትዮጵያዊያን) ደረጃቸውን ያልጠበቁ ለሰው መኖሪያነት ብቃት የሌላቸው ኮንዶሚኒየም ገንብተን

የበርሃዋ እንጉዳይ፣ አዲሲቷ ካይሮ

እኛ (ኢትዮጵያዊያን) ደረጃቸውን ያልጠበቁ ለሰው መኖሪያነት ብቃት የሌላቸው ኮንዶሚኒየም ገንብተን ግማሹም በጉቦ፣ ቀሪውን ለፖለቲካ ጥቅም ሌላውንም በሽያጭ ሰንሸነሽን ድሃ አሰለቅሰን ገር በድለን እርስ በእርሳችን ሰንባላ (ውሻ በአጥንት እንደሚጣላው ማለት ነው) ጠላት የምንላት ግብፅ የአባይን ውሃ ተማምና ሁለተኛውን ካይሮ ዓይናችን ሥር እየገነባች ትገኛለች፡ የእኛ ፖለቲካኞች በኮንደሚኒየም ሌብነት ፋታ ሲያጡ እና የግብፅ አዲስ አበባን የሚያህልና የሚያስንቅ አዲስ ካይሮ እየገነባች ነው (Smart City)። ልብ ያለው ልብ ይበል!

ግብፅ ለ5 ሚሊዮን ሕዝቦች መኖሪያ የሚሆነው አዲሷን የአስተዳደር Xና የንግድ ማዕከል የምትሆነዋን ካይሮ በ700 ሰኩዌር ኪ.ሜ ላይ በመገንባት ላይ ትገኛለች፡፡ ይኽም አሁን አዲስ አበባ ካላት የቆዳ ስፋት 143 ስኩዌር ኪ.ሜ ይበልጣል። ይኽን በተመለከተ የእንግሊዙ ጋርዲያን ጋዜጣ የሚከተለውን ያሰነብበባል፡

The alternative capital will span 700 sq. km, making it almost as large as Singapore, and is intended to house a total of five million people. The plan shows an expanse of high-rises and residential buildings as well as a “government district” all stationed around a central “green river”, a combination of open water and planted greenery twice the size of

New York’s Central Park.

ግብፅ አዲስቱን ካይሮ ስትገንባ በአንጻሩ የብልፅግና አሰተዳደር አዲሰ አበባን እያጠበበና እያቀጨጨ ባለበት ሰዓት ላይ መሆኑ ይሰመርበት በግብፅ ሰለሚገነባው አዲሱ ከተማ ሁሉንም በዚህ ጽሑፍ ማቅረብ አይቻልም፡ ስታስቲካዊ መረጃ ለመስጠት ያህል የሚከተለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ፡፡

1. ከ5 እስከ 6 ሚሊዮን ነዋሪዎችን የሚይዙ 21 የመኖሪያ ክፍለ ከተሞች እና 25 ልዩ ክፍለ ከተሞች ጠቅላላ 46 ክፍለ ከተማ፤

2. ማዕከላዊ ፓርክ እና ሰው ሰራሽ ሐይቅ፤ 3.200ዐ የትምህርት ተቋማት፤

4. 663 ሆስፒታል እና ክሊኒክ፤

5, 1250 የእምነት እቋማት (መስጊድ እና ቤተክርስቲያን)፤

6. 9ዐ ሺህ ተመልካች የሚይዝ ስታዲየም፤

7. 40 ሺህ የሆቴል ክፍሎች (ከመቶ በላይ ሆቴሎች ነው)፤

8. የአሜሪካኑን ዲዚ ላንድ የሚያህል የመዝናኛ ፓርክ፤

9. አዲስ አየር ማረፊያ፤

10. 450 ኪ.ሜ ባቡር መስመር ከዛም 1750 ፈጣን የባቡር መስመር፤

11. ከአፍሪካ ትልቁ ሰማይ ጠቀስ ፎቅና ሌሎችም…

እኛ እንጠማለን እነሱ ይጠጣሉ!

ይኽ ከተማ (የዘመናችን ፒራሚድ) ይኽ ሕይወት እንዲኖረው ውሃ ያስፈለገዋል። ለመሆኑ ግን ይኽ ከተማ

ግብፅ አዲሰቱን ካይሮ ሰትገንባ በአንጻሩ የብልፅግና አሰተዳደር አዲስ አበባን እያጠበበና እያቀጨጨ ባለበት ሰዓት ላይ መሆኑ ይሰመርበት፡ በግብፅ ሰለሚገነባው አዲሱ ከተማ ሁሉንም በዚህ ጽሑፍ ማቅረብ አይቻልም፡፡ ስታሰቲካዊ መረጃ ለመስጠት ያህል የሚከተለውን ሰንጠረዥ ይመልከቱ፡

1. ከ5 እስከ 6 ሚሊዮን ነዋሪዎችን የሚይዙ 21 የመኖሪያ ክፍለ ከተሞች እና 25 ልዩ ክፍለ ከተሞች ጠቅላላ 46 ክፍለ ከተማ፤

2. ማዕከላዊ ፓርክ እና ሰው ሰራሽ ሐይቅ፤

3. 200ዐ የትምህርት ተቋማት፤ 4. 663 ሆስፒታል እና ክሊኒክ፤

5. 1250 የእምነት እቋማት (መስጊድ እና ቤተክርስቲያን)፤

6. 90 ሺህ ተመልካች የሚይዝ ስታዲየም፤ 7, 40 ሺህ የሆቴል ክፍሎች (ከመቶ በላይ ሆቴሎች ነው)፤

8. የአሜሪካኑን ዲዚ ላንድ የሚያህል የመዝናኛ ፓርክ፤

9. አዲስ አየር ማረፊያ፤

10. 450 ኪ.ሜ ባቡር መስመር ከዛም 1750 ፈጣን የባቡር መስመር፤

11. ከአፍሪካ ትልቁ ሰማይ ጠቀስ ፎቅና ሌሎችም…

እኛ እንጠማለን እነሱ ይጠጣሉ!

ይኽ ከተማ (የዘመናችን ፒራሚድ) ይኽ ሕይ® እንዲኖረው ውሃ ያሰፈለገዋል። ለመሆኑ ግን ይ ከተማ ምን ያኽል ውሃ ያስፈለገዋል? አሁንም መልሼ ወደ

ጋርዲያን ዘገባ ልውሰዳችሁ፡ እንደ ዘገባው ከተማው ከተጠናቀቀ በኋላ ለከተማው 1.5 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር ውኃ በቀን ያስፈልጋል፡ ይኽን በዓመት (365 ቀናት) ብናሰላው 547.5 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር ውኃ ለአዲሱ ከተማ ያስፈለጋል ማለት ነው:: አንድ ኩቢክ ውሃ 1000 ሊትር ነው: ይኽ ውሃ የሚገኘው ከየት እንደሆነ መገመት ይቻላል፤ ከአባይ ነው

የግብፅ አዲሱ ከተማ የውሃ ፍላኀት እና የአዲስ አበባን ከተማ የውሃ ፍጆታ በአንፅራዊነት ለመመልክት ኢጂነር ሰይፈሚካኤል ሞላ ለማስተርሰ ፕሮግራም ካቀረበው የመመረቂያ ጽሑፍ ከተወሰደው መረጃ በመጥቀሰ እናመሳከር፡- The current average supply of 460,000 m3/ day is not sufficient to cover the city’s needs and supply interruptions are necessary. The city is receiving only 49% of its demand with an average supply time of 14.8 hours per day. ከዚህም በተጨማሪ ባለፈው ክረምት በአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሸ አገልግሎት ባለሥልጣን የቀረበው ሰነድ እንደሚያሳየው የአዲስ Aበባ የውሃ ፍላጎት 930,000 ኪቢክ/ሜ ሲሆን ወደፊት የአቅርቦቱ መጠን 575,000 ኪቢክ/ሜ እንደሚደርስ ጠቁሟል። ይኽ ወደፊት ለአ.አ ሕዝብ ይቀርባል የተባለው የውሃ መጠን ግብፅ ለአዲሱ ከተማ አቀርበዋለሁ ካለችው የውሃ መጠን 200% ያነሰ ነው:

ከዚህ መረጃ እንደምንረዳው አዲሱ የግብፅ ከተማ የውሃ አቅርቦት የአዲሰ አበባን ውሃ አቅርቦት ↑ በ326.087% በላይ ይበልጣል። እዚህ ላይ 49% የሚሆነው የአዲስ አበባ ውሃ በተለያየ ምክንያት

ከዚህ መረጃ እንደምንረዳው አዲሱ የግብፅ ከተማ የውሃ አቅርቦት የአዲሰ አበባን ውሃ አቅርቦት በ326.087% በላይ ይበልጣል እዚህ ላይ 49% የሚሆነው የአዲስ አበባ ውሃ በተለያየ ምክንያት ለተጠቃሚው እንደማይደርስ ጥናቱ አመልክቷል፡ ያ ማለት ለአዲሰ አበባ ሕዝብ የሚጠቀመው ውሃ 230 ሺህ ኪቢክ/ሜ ውሃ ብቻ ነው፡፡ ይኽ የሚያስደነግጥ አኀዝ የሚያሳየን ከአዲስ አበባ ጋር ሲነፃፀር አዲሱ የግብፅ ከተማ 652% የተሻለ የውሃ አቅርቦት አለው ማለት ነው፡ ይኽን አኀዝ በሌላ መልኩ ብንመለከተው በሁለቱ ከተሞች መካከል ሰላለው የውሃ አቅርቦት የተሻለ ስዕል ይሰጠናል፡ በሁለቱም ከተሞች አምሰት ሚሊዮን ነዋሪዎች አሉ ብለን ብንውሰድ እና እያንዳንዱ ነዋሪ ምን ያህል የውሃ አቅርቦት አለው ብለን ብናሰላ የምናገኘው የሚከተለውን Uኀዝ ነው፡፡ በአዲሱ የግብፅ ከተማ እያንዳንዱ ሰው በቀን 300 ሊትር የውሃ አቅርቦት ሲኖረው በአዲስ አበባ የሚባክነውን ውሃ እንደ ባከነ ሳንቆጥር ለአዲሰ አበባ ከተማ ነዋሪ የሚደርሰው የውሃ አቅርቦት 92 ሊትር ሲሆን የሚባክነውን የውሃ መጠን ከቀነሰነው (መቀነስም አለበት) ለእያንዳንዱ አ.አ ነዋሪ በቀን የሚቀርበው የውሃ መጠን 46 ሊትር ብቻ ነው: የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው ማለት አሁን ነው፡ ይኽን አኀዝ ከሃይጂን (የግል ንፅህና)፣ ከጤና እና ከምግብ ጋር አዛምደን ትንታኔ ቢሰጥበት የሚሰጠን ምሥል እጅግ በጣም አሰደንጋጭ፣ አሳፋሪ፣ እና አስቀያሚ ሊሆን ይችላል፡ ይኽን ግምት Aአንባቢ እተወዋለሁ:

በመገንባት ላይ ያለው አዲሱ የፈርኦኖቹ ሰማርት Hመናዊ የአሰተዳደር ከተማ

በመገንባት ላይ ያለው አዲሱ የፈርኦኖቹ ሰማርት ዘመናዊ የአሰተዳደር ከተማ

እኛም “አባይ አባይ” እንላለን፡ እነሱም ከላይ በተቀመጠው ግጥም “አባይ አባይ” ይላሉ፡ በእርግጥ ግብፅ የአባይ ስጦታ ነች የሚባለው አባባል ከእውነት የራቀ ባይሆንም የሳሃራ ንዳድ በርሃ ግን የአባይ ሰጦታ ሊሆን አይችለም፡፡ ነገር ግን ደም አፍሰሶም ሆነ አሰፈሰሶ ወደ ሥልጣን የመጣ አፍሪካዊ መሪ ሁሉ እንደ ወንበሩ/ ዙፋኑ ተፈጥሮንም የሚያሽከረክርና የሚቆጣጠር ይመስለዋል። ለዚህም ማሳያ የደርጉን/መንግሥቱን “ተፈጥሮን በቁጥጥር ሥር እናደርጋልን” የሚለውን መሪ ቃል ማሰታወሱ በቂ ነው፡ እንደ ደርጉም የግብፅ መሪዎች የራሳቸውን ሕልም እና ቅዠት አላቸው᎓: ግብፅ አስዋን ግድብን እውን ካዳረገችበት ዘመን ጀምሮ በግድቡ ምክንያት የተጠራቀመውን ውሃ በመጠቀም የግብፅ መሪዎች በሀሩር የነደደውን የሳሃራን በረሃ ገነት ለማድረግ በሕዝባቸው ፊት ማሉ፡ የዚህ ሕልም እና ቅዠት አንዱ ማሳያ የቶሽካ ሸለቆ የመሰኖ ፕሮጀክት ነው

የቶሽካ የመሰኖ ፕሮጀክት ከናስር ሐይቅ ከሚገኝ ውሃ በቦይ በመጥለፍ የግብፅን ምዕራባዊ በረሃ ማልማት ነው፡፡ ይኽም ክፍል የሳሃራ በረሃ አካል ነው: በአማካኝ የሙቅቱ መጠን 41 ዲግሪ ሴንትግሬድ ነው፡፡ የናሰር ሐይቅ የተፈጠረው በአስዋን ግድብ ምክንያት ሲሆን የሐይቁም ርዝመት 479 ኪ/ሜ ሲሆን የጎን ሰፋቱም 16 ኪ.ሜ ነው፡፡ የናሰር ገደብ ከተገነባ በኋላ በተ ጠረው ሰው ሰራሽ ሐይቅ የኀመጁት የግብፅ መሪዎች ቶሽካን ፕሮጀክት አቀዱ፡፡ የግብጽን በረሃ የማልማት እቅድ በመሾመሪየ የወጣው 1960ዎቹ ወም 1950 እን?

በመጀመሪያ የወጣው 1960ዎቹ ወይም 1950 እንደ ኢትዮጵያን አቆጣጠር በጀማል አብዱል ናስር ነበር

ግብፆች በዚህ ፕሮጀክት 540ሺህ ፊዳን መሬት በማልማት ለወጣቱ ትውልድ ሥራ በመፈጠር እና አዲስ መንደር ለመሥጠት አስበዋል: አንድ ፈዲያ 0.42 ሄክታር ነው፡፡ በአጠቃላይ ሊለማ የታሰበው መሬት 226ሺህ 800 ሄክታር ነው፡፡ ይኽ 226ሺህ 800 ሄክታር መሬት ዝም ብሎ አይለማም፡ ለልማቱ ከፍተኛ የውሃ መጠን ያስፈለጋል፡ እንዲያውም ግብፅ ባቀደችው ፕሮጀክት መሠረት በቂ ውሃ ላታገኝም ትችላለች አንድ ሰነድ ይኽን ያሳያል፡ Egypt could even run short of water if other Nile basin countries to the south should build dams and divert some of the flow. የግብፅ ይኽንን የቅዝት ሕልም ለማስፈጸም ብላ ነው የአባይ ተፋሳሽ አገራት ግድብ አንገድባለን ሲሉ ኡኡታ ያዙኝ ለቀቁኝ የምታሰማው፡፡ ይኽ ደግሞ እኛን ይበልጥ ይመለከተናል፡

ለማናቸውም ግብፅ ለማልማት ላሰበችው መስኖ እና አካባቢ ለሚመሠረተው መንደር የሚያሰፈልገው የውሃ መጠን ምን ያሀል ነው? ይኽን በተመለከተ ንጂነር በኃይሉ አሰፋ ካስነበቡን ሰነድ የሚከተለውን እንመልክት፡- The estimated required water discharge is about 5.5 BCM/year taken at 265 km upstream of the High Aswan Dam (HAD). በድምሩ የቶሽካ ፕሮጀkት 5.5 ቢሊዮን ኪቢክ ሜትር ውሃ ያሰፈልጋል ማለት ነው ተመሳሳይ ሰድ በኤu.ኤም አብዲ ሰላም (N. M. Abdel Salam) እና ባልደረቦቹ በ Twelfth International Water

ባልደረቦቹ በ Twelfth International Water Technology Conference, IWTC12 2008 Alexandria, Egypt ቀርቧል

በሌላም በኩል በቀረበ በዩቲዩብ ዘጋባ መሠረት ግብፅ በሰራችው የውሃ መስመር በዓመት ሊፈስ የሚችለው የውሃ መጠን 380 ቢሊዮን ኪቢክ ጫማ ወይም 10.74 ቢሊዮን ኪቢክ ሜትር ነው በተጨማሪም ለፕሮጀክቱ የሚሠራው ሰው ሰራሽ ሃይቅ 1665 ቢሊዮን ኪቢክ ጫማ ወይም 47.148 ቢሊዮን ኪቢክ ሜትር ውሃ መቁጠር ይችላል፡ እዚህ ላይ በዓለም አቀፍ የውሃ ቴክኖሎጂ ኮንፍረንሰ ላይ የቀረበው አኀዝ 5.5 ቢሊዮን ኪቢክ ሜትር ውሃ ብቻ እንደምትጠቀም ቢያሳይም የተዘረጋው የውሃ መሰመር ከዛ እጥፍ ውሃ ሊያስተላልፍ እንደሚችል በዩቲዩብ ከቀረበው ዘገባ መረዳት ይቻላል።

     በኢያሱ ኤፍሬም
       First published, in February 2021 at gion magazine website

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories