አለም ባንክ ልማትን ከምዕራባዊያን ጥቅም ጋር አስተሳስሮ ያበድራል ይነፍጋልም። የህዳሴ ግድቡ በራስ አቅም እየተገነባ ሲሆን world bank ፈንድ አላደርግም ማለቱ ይታወቃል። አሁን ላይም ሌሎች ብድሮች ላይ ያንገራገረን ይገኛል።
ይህ ጫናው ለአገረ-ፓኪስታንም ደርሷል። አገሪቱ 4,500 MW ማመንጫ በኢንደስ ወንዝ ላይ ለመገንባት ከ 2 አመት በፊት ነበር እንቅስቃሴ የጀመረችው። አለም ባንክና አሜሪካ ቃላቸውን አጠፉና ፈንድ እንደማያደርጉ 2018 ላይ መርዶ አስደመጧት። ወዲያውም ለዜጎች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ይፋ ሆነ። የተሰበሰበው ግን ኢምንት ብቻ…።
በዚህ አመት ግምቦት ወር ላይ ግን ቻይና ፓኪስታንን አለሁ አለቻት። ብድር አቅርባ በራሷ ኩባንያ ልትገነባው ተስማምታለች።
ዲያመር ባሻ የተሰኘው ግድብ 14 ቢሊዮን ዶላር በጀት የጠየቀ ነው።
እንግሊዝ በቅኚ አገዛዝ ዘመኗ አወዛጋቢ አድርጋ ባካለለችው የካሽሚር አቅራቢያ የሚገነባው ግድብ ከህንድ ተቃውሞውና ሴራው ቀጥሎበታል። ዛሬ በወጣ ዘገባም ህንድ ገለልተኛ አደራዳሪ በአለም ባንክ እንዲቀርብ ጠይቃ የነበረ ቢሆንም ባንኩ ይህን ማድረግ የምችልበት ህጋዊ መሠረት የለኝም ብሏል። አገራቱ በራሳቸው ተደራድረው ይፍቱትም ነው ያለው።
https://m.timesofindia.com/india/cant-mediate-in-india-pak-water-dispute-world-bank/amp_articleshow/77437763.cms?__twitter_impression=true&s=09
https://www.google.com/amp/s/m.economictimes.com/news/defence/china-offers-to-build-dam-in-gilgit-baltistan-that-adb-world-bank-refused-to-fund/amp_articleshow/59234178.cms