ዓለም ያከበረው መከታ

ኮንጎ ሪፐብሊክ ነፃ መንግሥትነቷን ባወጀች ማግስት ነበር እጅግ አሳዛኝ የታሪኳን ምዕራፍ ‘ሀ’ ብላ የጀመረችው።

በወቅቱ ካታንጋ የተባለው የኮንጎ ግዛት መሪ የነበሩት ሞይሲ ሾምቤ በማዕድን የበለፀገችዋን ግዛት እገነጥላለሁ በማለት ጦርነት አወጁ፡፡ በዚህ ጊዜ አሥር ሺሕ ያህል ሠራዊት የነበራት ቤልጄም ዜጎቼንና ሠራዊቴን አድናለሁ በሚል በኮንጎ የውስጥ ግጭት ጣልቃ ገባች፡፡ የኮንጎ ኪንሻሳ መንግሥት ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካሳቩቡና ጠቅላይ ሚኒስትር ፓትሪስ ሉሙምባም አገራቸው እንዳትከፋፈል ለተባበሩት መንግሥታት የድጋፍ ጥሪ ወዲያውኑ አቀረቡ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ወታደራዊ እገዛ ለማድረግ ጥሪውን ተቀብሎ የቤልጀም ጦር ከኮንጎ ኪንሻሳ ጠቅልሎ ቢወጣም የርስ በርስ ጦርነቱ ግን ቀጠለ። ጠቅላዩ ፓትሪስ ሉሙምባ በካታንጋ ተገደሉ፡፡ ወዲያውኑም 11 ሺሕ የተባበሩት መንግሥታት ወታደሮች በካታንጋ ደረሱ፡፡

በዚያ የኮንጎ አሰቃቂ ጥቁር ጊዜ ኢትዮጵያ ከ 1952 እስከ 1956 ድረስ 3,000 ወታደሮቿን ልካ ሰላም ያስከበረች ሲሆን፣ ኢትዮጵያዊው ጠቅል ብርጌድ በዘመቻው ተሰማርቶ ትልቅ ገድል ከሰሩት ውስጥ ዋነኛው ሆኗል።

ጦሩ ከፈፀማቸው በርካታ ጀብዱዎች መካከል ፦

የኢትዮጵያው 8 ኛ ጠቅል ሻለቃ ዋና ማዘዣውን በስታንቪል ነበር ያደረገው፡፡ በጥቅምት 10 1961 ግጭት ወደ ተባባሰበት ሊዮፖልድቪል እንዲያመራ ታዘዘ፣ ከባዱን ተልዕኮ ከ 3 ባነሱ ቀናት ውስጥ በታህሳስ 14 1961 በድል ፈፀመ።

በዚያው ቀን ታዲያ ሻለቃው ለሌላ ዘመቻ ታዘዘ፡፡ በኤሊሳቤትቪል ሲደርስ ምንም እንኳን ለአስቸኳይ ኦፕሬሽን ፋታ በማይሰጥ ሁኔታ ጦሩ ከአየር ማረፊያው ደርሶ ወደ ከተማው ሲያመራ ከዬ ዛፍ ቅርንጫፎች ይርከፈከፍ የነበረውን አውቶማቲክ ተኩስ በመመከት በታክቲካዊ የውጊያ ስልት የተለያዩ በጠላት የተያዙ አከባቢዎችን የማፅዳት ተልዕኮውን በብቃት ፈፀመ። ከዚህ ባሻገር የጠላት ከባድ ይዞታ የነበረውን ሊዶ ሆቴል በታህሳስ 15 ነፃ ማድረግ ችሏል። ይህን ለመፈፀም በ 4:30 ሰዓት (በአካባቢው ሰዓት) አንድ riffle አንድ heavy coy ጠመንጃ ብቻ በመጠቀም ሲሆን ኦፕሬሽኑ በ 1:30 ጊዜ ውስጥ 6:00 ሰዓት ላይ ነበር መቋጫ የሰጠው።

በተጨማሪም 1 ኛ ጠቅል ብርጌድ በ 25 ኛ ጠቅል ተተካና በካባሎ ዋና ማዘዣውን አቋቋመ፡፡ ግራ በሚያጋባው የግጭቱና የአካባቢው ሁኔታ ውስጥ ሻለቃው ነገሮችኝ በድንቅ ብቃት ፈፀመ፡፡ ቡሉባስ ከሚባለው የአገሬው ብርጌድ ጋር የፈጠረው ጠንካራ ቅንጅትና ተግባቦት አሰሰደናቂ ነበር፣ አገሬው የቡባ ብርጌድ ጠቅል ሻለቃ ወደ ሌላኛው ኮንጎ ክፍል ሲዘዋወር ፍፁም ከፍቷቸው ነበር።

በማኖኖ እና ሚትዋባ ጠንካራ ምሽግ ከያዙ የጠላት ሃይሎች ከባድ ጥቃት የገጠማቸው ብርጌዶችን እንዲያግዝ በተሰጠው ትዕዛዝም ለተከታታይ ሶስት ቀናት ከባድ ውጊያ አድርጎ ድልን ተጎናፅፏል።

ያኔ በኮንጎ የጭንቅ ጊዜያት ወ ታ ደ ራችን የፈፀመውን አይነት ጀብዱ የሌላ የየትኛውም አገር ሰራዊት አልሞከረውም፤ የሚስተካከለውም ሊገኝ አልቻለም ነበር። ስለ ጀግንነቱ ድፍን አፍሪካ ከቸረችው አክብሮትና ፍቅር ባሻገር መላውን አለም ያዳረሰ ዝና መጨበጥም ቻለ …..??

ዘንድሮ በታሪክ የማይረሳው በወገን የመወጋት ጭካኔን ማስተናገዱ ልብን ቢያደማም ለብረት ፅናቱ ግን ሌላኛው መስፈንጠሪያ ይሆነዋል ??

   ~ የዓባይ ልጅ  Esleman Abay

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories