ዓባይ እና የአፍሪካ ህብረት ዳግም መወለድ

African solutions to Africa’s problems addis lissan newspaper

‹ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ African solutions to Africa’s problems’ የሚለውን የህብረቱ መርሆ መተግበር እንዲጀምር የምትጠቁመው ይህች ፅሁፍ “ነገረ-አፍሪካ ሕብረት ” በሚል ርዕስ ሰኔ 11 ገደማ ያዘጋጀኋት ነች። በሰኔ 18 ላይም አዲስ ልሣን ጋዜጣ ላይ ወጣች።

የግድቡ የመጀመራያ ምዕራፍ ሙሊት ሐምሌ 12 ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ መጠናቀቁን አገራችን ለሶስቱ አገራት ተደራዳሪዎችና ተሳታፊ አደራዳዎች ይፋ ማድረጓን ተከትሎም የግብፅ የዘመናት ፈርኦናዊ አቋም ማክተም የተንፀባረቀበት geo-political ለውጥን ወለደ። ክስተቱ ከኢትዮጵያ ባሻገር ለአፍሪካም ተረፈ። ህብረቱ ሚናውን ባለመጫወቱም ነበር በፅሁፌ “እያንቀላፋ ነው” ስል የገለፅኩት። ከሙሊቱ ማግስት ጀምሮ ግን ኢትዮጵያዊው አባይ እንደ በአድዋው ድል የተወለደውን ፓን-አፍሪካኒዝም ዳግም ወልዶታል። ሙሊቱን አስመልክቶ ምንስትሩ ኢ.ር ስለሺ በቀለ ” ‘ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ’ የሚለው መርህ ጆሮ አገኘ” ማለታቸውም ይህንኑ አስረገጠ።

ዓባይ ዛሬ ለአፍሪካ ህብረት ዳግም ልደት ከሆነ፣ ከአባይ ማህፀን ዳግም የተወለደው አፍሪካዊ ወኔ አድጎ እንዲጎለምስ ምን መደረግ አለበት የሚለው ጥያቄ ደግሞ የፈጠነ ተግባር ሊመልሰው የሚሻ ትኩስ አጀንዳ ነው። በዚህ ርምጃ ውስጥም ግምባር-ቀደሙ ሚናም ሆነ ዋነኛ ተጠቃሚ አገራችን መሆኗ አስማሚ ነው። ስራው አሁኑኑ ይጀመር!

  • ነገረ-አፍሪካ ሕብረት
    june, 18, 2020

‹ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ›—African solutions to Africa’s problems’ በሚል ከሚታወቀው አፍሪካ ህብረት መርሆ ውስጥ ተከታዩን መርጠን እንይ

👉የአባላት ሀገር ብሔራዊ ነፃነት እና ሉዓላዊነት የሚጋፉ ድርጊቶችን መመርመርና እርምጃ መውሰድ ፡፡

👉የአፍሪካ አገራት ሉዓላዊነት እኩልነት ላይ አፅንኦት ተሰቶቷል።

👉በአፍሪካ የቅኝ ግዛት የበላይነትንና የሚወልዳቸውን ተፅዕኖዎች ማስቆም ፣ የአፍሪካን አንድነት ማስፋት ፣

ህብረቱ በነዚህ መርሆች ቢቋቋምም መስራቿና መቀመጫዋ ኢትዮጵያ የራሷን የውሃ ሀብት እንዳትጠቀም ከመቸውም በባሰ በግብፅ እየተሴረባትና በተለይም ግብፅ ወታደራዊ እርምጃን እስከመጠቀም በዘለለ ድንፋታ ስታስፈራራ እንኳን የመፍትሔው አካል መሆን አልቻለም።
የአረብ ሊግ የግብፅን ሴራ ደግፎ አቋም ሲይዝም ድምፅ አላሰማም። አፍሪካዊ ያልሆኑት እንደ ሩሲያ ቻይና አውሮፓና መሠል ተዋናዮች በግድቡ ድርድሮች ውስጥ የበኩላቸውን ሀሳብ ሲያንፀባርቁ ህብረቱ ሀላፊነቱንም መወጣት የሚችል ሆኖ አልቀረበም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አለመግባባቱን ለመፍታት የህብረቱ የ 2020 ሊቀመንበር ለሆኑት የደ.አፍሪካ ፕሬዘዳንት ሲረል ራምፎሳ በቅርቡ ጥሪ ማድረጋቸውን ስናስታውስ ጥሩ ርምጃ ቢሆንም ህብረቱ የሚጠበቁበትን ተግባራት ግን ሲፈፅም አልታየም።
ባለፈው ግምቦት ወር የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበሩ እና የጠ.ሚ አቢይ አድናቂ የሆኑት ሙሳ ፋኪ የ 2015 ቱን ሰነድ በማክበር ሶስቱ አገራት በጋራ መግባባት፣ በግልፅነትና በቅን መተማመን እንዲስማሙ እንደሚያበረታቱ ገልፀዋል፡፡

ይሁን እንጂ ‹ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ› ከሚለው የህብረቱ መርህ አንፃር በመሰል አለመግባባቶች ላይ እንቅልፋም እንደሆነ የሚገልፁት የደህንነት ጥናቶች ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የምርምር ባልደረባ አንድሪወስ ታና-አሳሞአ “ህብረቱ በመሰል አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ ሀላፊነቱን የመወጣት ታሪክ የለውም፡፡ አባል አገራቱ አስቸጋሪ ርዕሰ ጉዳዮችን አጀንዳ ከማድረግ ይቆጠባሉ።” ያሉ ሲሆን “ህብረቱ ግን አለመግባባቶችን ለመፍታት አስቻይ የሆኑ ድጋፎች የማድረግ አቅም አለው፡” ባይ ናቸው።

የህብረቱ ማንቀላፋት የተመቻቸው ባዕዳንም አህጉሪቷን አሿንጉሊት አድርገዋት ይገኛሉ። ትላንትና የአሜሪካ National security counsil አድሏዊ መግለጫም አገሪቱ ከአፍሪካዊ አገራት ጓዳ እጇን እንደማታወጣ አሳይቷል።

በነገራችን ላይ ምክር ቤቱ በፕሬዘደንቱ የሚመራ ሲሆን ይህ ነው የተባለ የህግ ስርዓት የሌለው ነው። ውሳኔዎቹ በፕሬዘዳንቱና በሾማቸው አባላቱ ነው የሚደመደመው። ከዛም እንዳስፈላጊነቱ CIA ወይም ጦሩ ለዚህ አቋም የቤት ስራ ይሰጠዋል። ምክር ቤቱ ውስጥ ራሱ ከፍተኛ ትችትና ውዝግብ የፈጠሩ የትራምፕ አቋሞች መከሰታቸው በአገሪቱ መሪዎች ታሪክ ያልታየ ነው ቢባልም የትራምፕ አቋም ገዢ ይሆን ዘንድ በግልፅ ባልተፃፈ ህግ መመራቱ ምቹ አድርጎለታል።

ታዲያ የምክር ቤቱ ጫና በአፍሪካዊት ኢትዮጵያ ላይ የሚያርፈው የአፍሪካ ጉዳዮች ፀሀፊው አድርጎ በአፍሪካ ህብረትና በህብረቱ የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት ቸልተኝነት በኩል ነው። የወቅቱ የ american national security council የአፍሪካ ጉዳዮች ፀሀፊ Tibor Nagy ናቸው። ባለፈው አመት ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ጉብኝት አድርገዋል። ከአዲስአበባ በተጨማሪ ወደ መቀሌም አቅንተው ነበር። በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት ንግግርም ከዩኒቨርሲቲው የክብር ዲግሪ እንደሰጣቸው አውስተዋል።

በደቡብ አፍሪካ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይም ከኛ አገር የኢዜአ ጋዜጠኛ መታደሟና ስለ አሜሪካና ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ትብብር ጠይቃው ነበር። ግብፅና ኢትዮጵያን አስመልክቶ የጠየቃቸው የኦል አፍሪካ ግሎባል ሚዲያው ጋዜጠኛ ነበር። በወቅቱ ሩሲያ ልታደራድራቸው ነውና የአሜሪካን አቋም ነበር የጠየቀው። ፀሀፊውም ዝርዝር እውነታዎችን ሳያስቀምጡ ነገር ግን በድርድሩ ጥሩ ውጤትን እንደሚጠብቁና አሜሪካም ገለልተኛ ትሆናለች በማለት የተለመደ የዲፕሎማሲ ተረካቸውን ነበር ያሰሙት።

የሆነስ ሆነና 11 የአፍሪካ አገራትን በሚያቋርጥ የአፍሪካዊያን ወንዝ ጉዳይ ባዕዳን ከትላንት እስከዛሬ እጃቸውን ሲያስገቡ አፍሪካ ህብረት እንቅልፍ ላይ ነው የሚገኘው። ይህን ለመለወጥ ስራ መጀመር አለብን። የህብረቱ ሊቀመንበር፣ ቻይና አውሮፓ ህብረት ጀርመንና ሌሎች ተዋናዮች የ 2015 ሰነዱ እንዲከበር ነው የጠየቁት። ይህን እኛና ሱዳን አክብረናል። የረገጠችው ግብፅ ናት። የግብፅ አካሄድ ከአፍሪካ ህብረት ዋነኛ መርሆዎች ውስጥ “በአፍሪካ የቅኝ ግዛት የበላይነትንና የሚወልዳቸውን ተፅዕኖዎች ማስቆም” ከሚለው አንፃር እንኳን ብንመለከተው የቅኚ ግዛት ውሎች አይነኩብኝ የሚለው አቋሟ ህብረቱን የናቀና የተፃረረ ያደርገዋል።

ይህ ሁሉ ሲሆን ዝም ያለው ህብረቱ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት ቢያወግዝ መቶ በመቶ የህግ መሠረት ላይ ሆኖ ነው። አረብ ሊግ ግብፅን ሲደግፍኮ ምንም የህግ መሠረት ሳይኖረው ነው። ህብረቱ አሜሪካን ያውግዝ። ህብረቱ ስራ ሲጀምር እነ አውሮፓ ህብረትና መሰል ተቋማት የጀመሩት የድርድር ሀሳብ ወደ መሬት መውረድ ይችላል።

ይሄ ሁሉ ግን አላስፈላጊ መስዋእትነት ላለመክፈል እንጂ ግድባችን በማንም አይስተጓጎልም።

ዓባይ እና ታላቁ የህዳሴ ግድባችን አፍሪካ ህብረትን ከእንቅልፉ ቀስቅሷል ወይም ዳግም ወልዶታል። ህብረቱ በሁለት እግሩ መቆም የሚጀምረው ደግሞ በቀጣይ በአፍሪካ ጥላ ስር በሚካሄደው የግድቡ ድርድር ላይ መርሆው የሆነውን African solutions to Africa’s problems በተጨባጭ ማሳየት ሲችል ነው።

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories