
[ የህዳሴ ግድቡ የለወጠው የምስራቅ አፍሪካ ጂኦ-ፖለቲካ ]
Financial Times በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ከቀናት በፊት ካስነበበው ፅሁፍ ውስጥ “Ethiopia’s Nile mega-dam is shifting dynamics in Africa’s Horn” የሚለውን አርዕስት ከቁልፎች ተርታ እመድበዋለሁ። የሙሊቱ መጠናቀቅ ይፋ ከመደረጉ በፊት የወጣው የፅሁፉ የውስጥ ይዘት ግድቡን የገለፀበት መንገድ በግዙፍ የሀይል ምንጭነቱ ብቻ የተገደበ አልነበረም። የናይል ወንዝን ረጂም ታሪክ ያስቆጠረ ጉልበት በልጓም እየገታ እንደሆነም’እንጂ። ፅሁፉ የናይልን ጉልበት ይበል’ንጂ ‘በስመ-ሀዳሪያዊ’ ዘይቤው ግን ሌላ መሆኑ ግልፅ ነው። ኢትዮጵያ በልጓም እየገደበቻት ያለችው ፈርኦናዊት አገር ናትና።
የአፍሪካ ቀንድ ልብ ሲል የገለፃት ኢትዮጵያ ለበርካታ ፈርጣማ አገራት ትኩረት መግነጢስ መሆኗንም ጋዜጣው አልደበቀም። ጥንትም የትኩረት ነጥብ የነበረችው ኢትዮጵያ የዛሬውን መግነጢስነቷን ልዩ የሚያደርገው እንደ ፅሁፉ ሀተታ ‘እንደ ድሮው ከጣልቃ-ገብነት ይልቅ ትብብር ባመዘነበት መልኩ መሆኑ ነው። እነ ሳዑዲ፣ ኳታር፣ ዱባይ፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ቱርክ፣ ቻይና ወዘተ… ተጠቃሾች ናቸው።በተለያዩ መስኮችም የትብብር አቅርቦታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ። በተለይም ከጠቅላይ ምኒስትር አቢይ መምጣት ወዲህ በሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊላንድ የውጥረትና የመጠላለፍ ዘመኑ በእጅጉ መቀነሱንም ፅሁፉ ይገልፃል። የመተባበር አሊያም በአሉታ ሳይተያዩ የየራስ ግቦችን ማማተር እንደሰፈነም እንዲሁ። እነዚህ ሁሉ ለውጦች አዲስ አበባን ከቀጣናው አውራነት ባሻገር አድርጓታል። ሀያላኑ በተፋጠጥ በሰፈሩበት የባብ-ኤል-ማንዴብና የቀንዱ ከለላ ውስጥ ኢትዮጵያን ቁልፍ አጋር የማድረግ ጉጉታቸው ጨምሯልም።
የጂኦ ፖለቲክስ ለውጡ የነ ጂቡቲና ሶማሊያን የቀደመ ዲፕሎማሲያዊ ገፅታ በብዙው ገልብጦታል። ወደ ኢትዮጵያ። በቀደሙት ዘመናት በግብፅ ስፖንሰርነት ወደ አረብ ሊግ የገቡት አገራቱ፣ ለግብፅ የናይል ሴራ ድጋፍ ከመስጠት በቀር ምርጫ የላቸውም ነበር። በዘንድሮው መድረክ ግን ከግብፅ በተቃራኒ-ከኢትዮጵያ ደግሞ አጋር ሆነው ሲቆሙ ታዝበናል።
በተፃራሪው ደግሞ ግብፅ በሶማሊ ላንድ የጦር ሰፈር ለመገንባት እያሰበች ስለመሆኑ በዚህ ሳምንት በስፋት ተዘግቧል። የሶማሊያን ወደ ኢትዮጵያ ማድላት፣ ማድላት ባይሆንም ወደ ሀቁ መቅረቧ ዋነኛ መግፍኤው የተባለለት የግብፅ እንቅስቃሴ ወደ ሀርጌሳ እያማተረ ይገኛል።
በሰሜን-ምዕራብ የሶማሊ ላንድ ክፍል ወታደራዊ ጣቢያ ለማቋቋም ከቀናት በፊት በሀርጌሳ የተገኘው የግብፅ ልዑካን ቡድን ከፕሬዝዳንት ሙሳ ቡሂ አብዲ ጋር ፕሮፖዛል አቅርቧል ነው የተባለው፡፡ ከሶማሊላንድ በኩል ማረጋገጫ ባይሰጥበትም።
በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያና ሶማሊያ ቁልፍ የልማት አጋርነት ተግባራት ላይ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ናት ፡፡ በተለይም በባህር በርና የንግድ አውታሮች ዝርጋታ። ባህር የበርባ ወደብ ካለማው ከ DP World እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ(ዱባይ)፣ ጋር የወደቡን ድርሻ ተጋርተው ነው የሚገኙት። ዲፒ ወርልድ 51 በመቶ፣ ሶማሊላንድ 31 እና ኢትዮጵያ 19 በመቶ በሆነ ድርሻም ለረጂም አመት ሊዝ የበርበራ ወደብ ባለቤት ይሆናሉ።
በተያያዘም የግብፅ ልዑካን ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በነበሩት ቀናት ውስጥ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ወደ ሃርጌ ተጉዟል፡፡ ታዲያ ግብፅ የጦር ሰፈር በሶማሊላንድ ለመገንባት እየተንቀሳቀሰች ነው በሚሉት መረጃዎች ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ምኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ግን የኢትዮጵያ ልዑካን ጉብኝት በግብፅ ዕቅድ ዙሪያ በተፈጠረ ስጋት ስላለመሆኑ ነው ለአፍሪካዊ ሚዲያዎች ቃላቸውን ያስደመጡት። “በአገራቱ መካከል መደበኛ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለመወያየት መርሃግብር አካል ነው” ሲሉም ተደምጠዋል።” አያይዘውም “ግብፅ እንደ ሉዓላዊ አገር እንደመሆኗ ከሌላ አገር ጋር ግንኙነት መመሥረት ትችላለች” ያሉ ሲሆን “ይህ ግንኙነት ግን ለሌሎች አገሮች ስጋት የሚደቅን ሆኖ ከተገኘ ተቀባይነት አይኖረውም” በማለትም አክለዋል። የግብፅ ወደቀጠናው መምጣትም ከዚህ ያለፈ ሊሆን እንደማይችልም ነው አምባሳደር ዲና ለኬኒያው nation ዘጋቢ ጠቆም ያደረጉት።
የተነሳንበት የህዳሴ ግድቡ የአፍሪካ ቀንድ ጂኦ ፖለቲካ ለውጥ ማለትም ኢትዮጵያን በሚፈይድ ገፁ ነውና ማሳረጊያችን የሚሆነውም ‘ግብፅ በተበሉ ካርታዎች መባዘን ብትጀምርም ውሃውን መያዝ ተጀምሯልና ያልተገባ ባህርይ ስታሳይ ልጓማችን የአባይ ውሃችን ብቻውን የሚበቃት ይሆናል። በ financial times ፅሁፍ ውስጥ ‘Ethiopian Renaissance Dam, Africa’s largest hydroelectric power plant and the most ambitious attempt to harness the power of the Nile in history’ ተብሎ የተገለፀውም ይህንኑ የሚጠቁም ነው። ሠላም!
https://www.google.com/url?sa=t&source=web&rct=j&url=https://amp.ft.com/content/bdb2c384-2406-4f64-bde1-c2878ff520cd&ved=2ahUKEwiEr_PH3vDqAhWByaQKHfPJCwsQFjAAegQICBAB&usg=AOvVaw0e2AVMPPl7U9HywEJZ1xTD&cf=1
https://www.busiweek.com/egypt-proposes-to-set-up-a-military-base-in-somaliland/