እስሌማን ዓባይ Esleman abay
ሶስተኛውን ሙሌት ዓባይን በጭልፋ ያስባለው የአስዋን ነጥበ-ሙሌት
የዘንድሮው ዓባይ ከምናውቀውኔ ከተነገረን በላይ መሆኑን የሚያመላክት እውነታ ከስቷል። ይህ አመት በአውሮፓ አሜሪካ እስያ ወንዞች ደርቀው ከአቅመ መጓጓዣ እና ከአቅመ ኤሌክትሪክ የተናጠቡበት ነው። በርግጥ የናይል ተፋሰስ በመጪዎቹ ጊዜያት ብዙ ዝናብ ነገር ግን የውሃ እጥረት የሚታይበት እንደሆነ አንድን ጥናት አካፍያችሁ ነበር። የተቀረው አለም ሲደርቅ ተፋሰሱ ውሃ ይበዛዋል፤ ነገር ግን የህዝብ ቁጥርና የውሃ ፍላጎት መናር እጥረቱን ይፈጥሩታል ይላል ጥናቱ።
ዓባይ ላይ ህልውናውን ያደረገው አሰዋን Aswan High Dam ባልተጠበቀበት ቀን ነው ዘንድሮ የሞላው። ይህ ጉዳይ በዓባይ የውሃ አቅርቦት በናይል ተፋሰስ የውሃ ሃብት እንዲሁም በነባር አሃዞች ላይ ታላቅ አንድምታ ያለው ነው። የግድቡ ሶስተኛ ሙሌት ዓባይን በጭልፋ ነው ያስባለው፤ አስዋን ከአምናው አንፃር የሞላበትን ፈጣን ጊዜ ስናስበው ነው። ከአምናው በ12 ቀናት ቀድሞ ነው ሞሎቶ የፈሰሰው። (ከትላንት በስቲያ ነሐሴ 17እኤአ)።
ይህ ማለት አስዋን ዘንድሮ የደረሰው የውሃ መጠን ከአምናው የ33 በመቶ ገደማ ጭማሪ አለው፤ ሌሎች ተለዋዋጮችን እንዳሉ ሆነው በአስዋን የሙሌት ቀናት ስናሰላው)። ታዲያ የባለፈው አመት ዓባይ በግብፅ ስንት ነበር? ጉዳዩ ከዚህ ይጀምራል።
▪️ዓባይ በአስዋን ግድብ – 2021
ግብፅ በአመት ውስጥ ከምታገኘው የዓባይ ውሃ 53 በመቶውን በክረምቱ ሶስት ወራት ይደርሳታል(በሐምሌ ነሐሴ እና መስከረም)። ይህ በ 3 ወራት ብቻ የሚያገኙት የውሃ መጠን 85 አመታት የዘለቀ አማካይ ነው። (ግብፃዊው የውሃና ምህንድስና ፕሮፌሰር ሞሐመድ ሐፊዝ እንዳሰፈሩት። ቀሪው በ 9 ወራት የሚደርሳቸው ነው።
እንደ ግብፃዊው ፕሮፌሰር ሐፌዝ ጥናታዊ መረጃ ባለፈው ወርሐ ሀምሌ 6 BCM ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር፤ በነሐሴ 25 BCM, በመስከረም 19BCM, ሄዶላቸው ነበር = 50 ቢሊዮን ኪዩቢክ)።
ከዚህ የተረፈው ማለትም ከነሐሴ 29 ቀጥሎ በነበሩ ቀናት የሄደው ዓባይ ወደ ሜዲትራኒያን የፈሰሰው ነው።(ለዚህ ይሆን አውሮፓውያን ዘንድሮ ከካይሮ ጋር ሽር ጉድ ያበዙት?)
በዚያው የ2021 ክረምት ግብፅ በየቀኑ ያገኘችው የዓባይ ውሃ ከ900-1.1 ቢሊዮን BCM ሲሆን = አማካዩ አንድ ቢሊዮን በቀን መሆኑ ነው።
▪️ዓባይ በአስዋን – 2022
አስዋን ዘንድሮ አስራ ሁለት ቀናት ቀድሞ ከሞላ፤ የሰህም ከአምናው የአንድ ሶስተኛ ጭማሪ ከተሰላ፤ ካለፈው አመት የክረምት አማካይ 1 ቢሊዮን BCM ዘንድሮ 1.3 BCM በዬቀኑ ሲደርሳቸው ነበር ማለት ነው። ግብፆች ባመኑት መሰረት ዘንድሮ 25 BCM ይዘናል ብለዋል። የአራት አመት ሪዘርቭ ነውም ብለዋል። ይህ ውሃ አስዋን ሞልቶ ቶሽካ ጠጥቶ አዲሷ ካይሮ በውሃ ከተንበሸበሸች በኋላ ነው በግድባቸው አናት የፈሰሰው። ከዚያ እለት ጀምሮ ውሃው ወደ ሜዲትራኒያን እየፈሰሰ ነው ማለት ነው። ይህ የሜዲትራኒያን ሲሳይ መጠኑ ስንት ነው?
ከላይ በተገለሰው የግብፃዊው ፕሮፌሰር አሀዝ መሰረት ባለፈው ነሐሴ 25 በመስከረም 19BCM ደርሷታል። ይህ አሃዝ በዘንድሮው የውሃ መጠን በአንድ ሶስተኛ ከፍ ያለ ነው። የመስከረሙ 19BCM እና ከነሐሴ 17 እስከ 30 ባሉት 12 ቀናት አስራ ሁለት ቢሊዮን በድምሩ 31BCM ሲሆን፤ ከዘንድሮው ጭማሪ ጋር ሲሰላ በትንሹ 41BCM ማለት ነው። ይህ በሁለቱ ወራት ብቻ ወደ ሜዲትራኒያን እየፈሰሰ ያለ ውሃ ነው።
ይገርማል። ከዚህ በመነሳት የግብፅን ውሃ ያንሰኛል ጩኸት በአግባቡ ያለመጠቀም ልግመኝነቷን ሲያስረግጥ፤ በሌላ በኩል የህዳሴ ግድቡ ድፍን የ78BCM ሙሌት ማንንም ሳይጎዳ በመጪው ሁለት አመት ሊሆን እንደሚችል ያስገነዝባል። የሁለት ታላላቅ ግድቦች ወግ ከዚህ እውነታ ይቀዳል ማለት ነው – የአስዋን ጥጋብ እና የጉባው ለጋስ ግድብ።
▪️ሌላው ጉዳይ እናንተም ያሰባችሁት ይመስለኛል፤ እሱም በዘንድሮው ድርቅ የውሃ ያለሽ ያለው ድፍን አውሮፓ በሜዲትራኒያን በኩል ከዓባይ የመጨለፍ ድብቅ እቅድ አይኖራቸው ይሆን?
ውኃ ብቻ አይደለም – ዓባይ የሚባለው ለዚህ ነው
የዓባይልጅ #eslemanabay
#GERD #Nile