የሁሉም ነገር ግን የማንም … ፓቬል ዱሮቭ

የሁሉም ነገር ግን የማንም ... ፓቬል ዱሮቭ

▪️በሁሉም ጉልበተኛ ወገኖች የተፈተነ ሩሲያዊ

ቴሌግራም በሀገረ ሩሲያ ቀዳሚ እና ተመራጩ የመልዕክት መለዋወጫ ይሆን ዘንድ ሞስኮ ኢንስታግራም እና ፌስቡክን ማገዷ እንደ ዋነኛ ምክንያት ይጠቀሳል። ታዲያ ይህ ተፅዕኖ የራሱን ጣጣ ማምጣቱ አልቀረም ነበር። የመጀመሪያው ውዝግብ ከራሱ ሀገር ነበር የገጠመው። በመቀጠልም የራሱ ሀገር ባላንጣ ሀገራትና ጠላት የሆኑ መንግስታት ተከታታይ የጭቃ ጅራፎችን አሳርፈውበታል።

ቴሌግራም በ2018 የተጠቃሚዎችን መረጃ እንዲሰጥ ተጠይቆ ፍቃደኛ ባለመሆኑ በሩስያ ባለስልጣናት ለሁለት ዓመታት ታግዶ የነበር ሲሆን ከሁለት አመት በኋላ 2020 ላይ እንደተነሳለት ይታወሳል። በድርጅቱ ላይ የሚደርሰው ጫና ከሁሉም አቅጣጫ ነበር ማለት ይቻላል። ዩክሬይ፣ አሜሪካ በጥቅሉ ምዕራባዊ ሀገራትና ተቋማት በየፈርጁ ሲያዋከክቡት ነበር።

የሩሲያ ዩክሬይን ጦርነት በተቀሰቀሰበት ወቅትም ቴሌግራም የዩክሬን ተጠቃሚዎቹን መረጃ ለሩስያ ያቀብላል ተብሎ ስሙ ሲነሳ ነበር።
የኩባንያው መስራች በትውልድ ሩስያዊ፤ በእናቱ ደግሞ ዩክሬናዊ ሲሆን፤ መኖሪያውን ያደረገው ደግሞ በ UAE ዱባይ ነው። በወቅቱ ፓቨል ዱሮቭ ኩባንያው የዩክሬን ተጠቃሚዎችን መረጃ አሳልፎ እንዳልሰጠ፤ ይህንንም እንደማያደርግ በምንም ሁኔታ ለተጠቃሚዎቹ መብት እንደሚቆምም ነው የገለፀው።

የቴሌግራም መስራቹ ፤ በእናቱ በኩል ቤተሰቦቹ ከኪየቭ እንደሆኑ ጠቁሞ እስከ አሁን ድረስም በዩክሬን የሚኖሩ ብዙ ዘመዶች እንዳሉት ገልጿል። አሁን ያለው አሳዛኝ ግጭት “ለእኔም ሆነ ለቴሌግራም ግላዊ ነው” ሲል ነበር ሁኔታውን የገለፀው።

ምዕራባዊያኑ በተለያዩ የጫና ዘዴዎች ሲያደርሱበት የነበረ ሲሆን በተለይም “ከሩሲያ የሆኑ አካውንቶችን ለምንድነው ማትዘጋልን?” የሚለው ተጠቃሽ ነው – ፓቬል ዱሮቭ የሀገሩ ባለስልጣናት ስላሳደዱት፣ ኑሮውን በዱባይ ለማድረግ ሲገደድ እና የክረምሊን አገዛዝ ከጀርባው ሲያሯሩጠው በመታዘባቸው ሀገሩን የሚከዳ መስሏቸው ነበር – ምዕራባዊያኑ። ፓቬል ግን ተከታዩን ነበር የመለሰላቸው፤
   “ሰዎች ምርጫ የሚያደርጓቸውን መረጃዎች ያገኙ፤ ምንም እንኳ እየወደመ ያለው የእናቴ እትብት የተቀበረበት ቦታ ቢሆንም፤ ለመረጃ ነፃነት ስል የከፈልኩትን ዋጋ እኔው ራሴ ተመሳሳዩን ስህተት በመድገም አላበላሸውም፤ ዜጎች መብታቸው ነው” ሲል ነበር እነሱ ያልለመዱትን አስደንጋጭ ምላሽ የጋታቸው። ይህ ወጣት ሩሲያዊ የቴክኖሎጂ ልሂቅ ፈተናዎች ከሁሉም አቅጣጫ ይሰነዘሩበት ዘንድ [እሱ] ወገንተኛ አለመሆኑ እና፤ በሌላ በኩል ደግሞ ሀገሩን የሚያስክድ ስሜት-ወለድ ባንዳ ከመሆን የነፃ ስለነበር ነው ያስብላል።

ከሰሞኑ እንደሰማነው ደግሞ አሜሪካ ቴሌግራምን ለመቆጣጠር በርካታ ጥረቶች ስለማድረጓ እና ድርጅቱ ህግ የሚፈቅደው ስራውን ወደ አሜሪካ የማሳደግ እቅዱ በዋሽንግተን ባለስልጣናት የአፈና ቅድመ ሁኔታዎች ሳቢያ እክል እንደተፈጠረበት መስራቹ ፓቬል ዱሮቭ አስታውቋል።
በዚህም የቴሌግራም ማህበራዊ ድረ ገጽ መስራቹ በአሜሪካ ቢሮ ለመክፈት ያደረገው ጥረት አሜሪካ የተጠቀሚዎችን መረጃ ለመቆጣጠር ቅድመ ሁኔታን በማስቀመጧ አለመሳካቱን ነው የገለፀው…።
  አንዳንዴ እንዲህ ነው፤ [አንተ] የሁሉም ስትሆን የማንም እንዳትሆን ከሁሉም በኩል የሚወረወሩ ጋሬጣዎች ጉዞህን ፈታኝ ያደርጉብሃል  —- #የዓባይልጅ  Esleman Abay

Share:

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on pinterest

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

On Key

Related Posts

VK Russian online social media and social networking service

© 2022 Esleman Abay. All rights reserved.

Follow Us

Categories